1. ወደ ይዘቱ እለፍ
  2. ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ

ከባድ ዝናብ በዋግኽምራ በሰብል ላይ ጉዳት አደረሰ

ዓለምነው መኮንን
ዓርብ፣ መስከረም 9 2018

የዳሀና ወረዳ ም/አስተዳዳሪና የግብርና ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ዘነበ ማሞ እንዳሉት በክረምቱ ከባድ ዝናብ በወረዳው በ11ሺህ 366 ሄክታር ማሳ ላይ የነበረ ስብል ወድሟል ፡፡ 80,178 ሠዎች ለችግር ተዳርገዋል፡፡ ለሰዉ እርዳታ እንዲደርሰው ለብሔረሰብ አስተዳደሩ አደጋ መከላከልና ምግብ ዋስተና ጽ/ቤት ተደጋጋሚ ጥያቄ ቢቀርብም ምልሽ አለሰጠም፡፡

በከባዱ ዝናብ የጓሮና የመስክ ሰብል በሙሉ ወድሟል፣ በ5 የእርሻ ማሳ ላይ የነበረ ገብስ፣ ጤፍ፣ ማሽላና ምስር በሙሉ በከባድ ዝናብ ወድሟል።
በከባዱ ዝናብ የጓሮና የመስክ ሰብል በሙሉ ወድሟል፣ በ5 የእርሻ ማሳ ላይ የነበረ ገብስ፣ ጤፍ፣ ማሽላና ምስር በሙሉ በከባድ ዝናብ ወድሟል። ምስል፦ Dahana Woreda Communication

ከባድ ዝናብ በዋግኽምራ በሰብል ላይ ጉዳት አደረሰ

This browser does not support the audio element.

“ዝናቡ ስብሉን ሙሉ በሙሉ አውድሞታል” አርሶ አደሮች

በአማራ ክልል ዋግኽምራ በብሔረስብ አስተዳደሩ ዳሀና ወረዳ የአዚላ ቀበሌ አርሶ አደር አቶ ሰለሞን ንጉስ ለዶይቼ ቬሌ በስልክ እንደተናገሩት ትናንት መስከረም 8/2018 ዓ ም በረዶ ቀላቅሎ የጣለ ከባድ ዝናብ በሰብላቸው ላይ ከፍተኛ ጉዳት አድርሷል፡፡
እንደ አርሶ አደሩ የዘሩት የጓሮና የመስክ ሰብል በሙሉ ወድሟል፣ በ5 የእርሻ ማሳ ላይ የነበረ ገብስ፣ ጤፍ፣ ማሽላና ምስር በሙሉ በከባድ ዝናብ መውደሙን ነው ያስረዱት፡፡
ሌላዋ የቀበሌ ነዋሪ ወ/ሮ መርጫሽ ክብረት በቀበሌ የጣለው ከባድ ዝናብ ምንም ያስተረፈው የሰብል ዓይነት እንደሌለ ነው የገለፁልን፡፡
“... እንደዚህ ያለ መዓት ወርዶብን አያውቅም፣ ዓይተንም ሠምተንም አናውቅም፣ ቀበሌዋ በሙሉ ወድማለች” ብለዋል፡፡ እስከ 9 ጥማድ ስብልም እንደወደመባቸው ነው ወ/ሮ መርጫሽ በቁጭት የገለፁልን፡፡ ዋሴራ (የገብስና ስንዴ ድብልቀ)፣ ገብስ፣ ምስር በበረዶው ጉዳት ድርሶበታል፡፡

“ትናንት በጣለው ከባድ ዝናብ በ206 ሄክታር ላይ የነበረ ስብል ወድሟል” የወረዳው ግብርና ጽ/ቤት

የአዚላ ቀበሌ የሰብል ልማት ባለሙያ አቶ ሐብታሙ ሰንደቄ ትናንት ከሰዓት በኋላ በጣለው ክባድ ዝናብ በቀበሌው አትክልትና ፍራፍሬና የንብ ሐብትን ጨምሮ፣ በሠፊ ሔክታር ማሳ ላይ የነበረ ሰብል ወድሟል ብለዋል፡፡ አሁን ባለው መረጃ መሰረት በ206 ሄክታር ላይ የነበረ ሰብል የወደመ ሲሆን 3ሺህ 920 አባዎራዎችና ቤተሰቦቻቸው ለችግር መጋለጣቸውን አስረድተዋል፡፡ እስካሁን ያለው መረጃ ጎብኚ ቡድን የደረሰብት ብቻ መሆኑን አመልክተው ጉዳቱ ከዚያም ሊያልፍ እንደሚችል ተናግረዋል፡፡

የአዚላ ቀበሌ የሰብል ልማት ባለሙያ አቶ ሐብታሙ ሰንደቄ ትናንት ከሰዓት በኋላ በጣለው ክባድ ዝናብ በቀበሌው አትክልትና ፍራፍሬና የንብ ሐብትን ጨምሮ፣ በሠፊ ሔክታር ማሳ ላይ የነበረ ሰብል ወድሟል ብለዋል፡፡ ምስል፦ Dahana Woreda Communication

“ከ80ሺህ በላይ አረሶአደሮችና ቤተሰቦቻቸው ለጉዳት ተዳርገዋል” የዳሀና ወረዳ አስተዳደር

የዳሀና ወረዳ ምክትል አስተዳዳሪና የግብርና ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ዘነበ ማሞ በበኩልቸው በክረምቱ ወቅት በደረሰ ከባድ ዝናብ በወረዳው በአጠቃላይ በ11ሺህ 366 ሄክታር ማሳ ላይ የነበረ ስብል ወድሟል ነው ያሉት፡፡ 80ሺህ 178 ሠዎች ደግሞ ለችግር ተዳርገዋል ብለዋል፡፡


ለአርሶ አደሮቹ እርዳታ እንዲደርሳቸውለብሔረሰብ አስተዳደሩአደጋ መከላከልና ምግብ ዋስተና ጽ/ቤት ተደጋጋሚ ጥያቄ ቢቀርብለትም ምልሽ አለሰጠም ሲሉ ቅሬታቸውን አሰምተዋል፡፡
በወረዳው የሙዛባ ቀበሌ የሰብል ባለሙያ አቶ አረጋ ማሞ በቀረዳው ሙዛባና ጭላ በተባሉ አካባቢዎች ነሐሴ ወር ላይ በጣለው ከባድ ዝናብ ጉዳት የደረሰባቸ አርሶ አደሮች ማሳቸውን ገልብጠው ለማረስ ቢሞክሩም የዘርም ሆነ የእለት እርዳታ ማግኜት እንዳልቻሉ ተናግረዋል፡፡

የዋግኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር አደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ምህረት መላኩ ጉዳቱ ለማወቅ ጥናት እየተደረግ መሆኑን ጠቅሰው፣ ሲጠናቅቀ እርዳታ ይሰጣል ብለዋል፡፡ ምስል፦ Dahana Woreda Communication

“በጥናት ላይ የተመሠረተ እርዳታ ይደረጋል” የብሔረሰብ አስተዳደሩ አደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ጽ/ቤት

የዋግኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደርአደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ምህርት መላኩ የደረሰውን ጉዳት ለማወቅ ጥናት እየተደረግ መሆኑን ጠቅሰው፣ ጥናቱ ሲጠናቅቀ እርዳታ ይሰጣል ነው ያሉት፡፡ የብሔረሰብ አስተዳደሩ የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት የዜናና ህትመት ባለሙያ አቶ የሻምበል አራጋው ጉዳት ወደደረሰበት የአዚላ ቀበሌ ከተለያዩ የወረዳው ጽ/ቤት የተወጣጣ ቡድን ተዋቅሮ ዛሬ ምልከታ ማድረጉን ጠቅሰው ቡድኑ እንደተመለከተው ዝናቡ በአካባቢው በሰብል ላይ ከባድ ጉዳት አድርሷል ብለዋል፡፡

ዓለምነው  መኮንን
ኂሩት መለሰ
ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር
 

ቀጣዩን ክፍል እለፈው ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ
ቀጣዩን ክፍል እለፈው የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል እለፈው ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW