ከታላቁ የኢትዮጵያ ኅዳሴ ግድብ ኢትዮጵያውን ምን ይጠብቃሉ?
ማክሰኞ፣ ጳጉሜን 4 2017
ማስታወቂያ
ኢትዮጵያ በአባይ ወንዝ ላይ የገነባችውን ታላቁን የኢትዮጵያ ኅዳሴ ግድብ በዛሬው ዕለት ስታስመርቅ ኢትዮጵያውን በተለያዩ የመገናኛ ብዙኀን አማራጮች በቀጥታ ተመልክተውታል። ዛሬ ከማለዳው ጀምሮ በርካታ ከተሞች ውስጥ የግድቡን መመረለቅ ብስራት ተከትሎ ሕዝብ ወጥቶ ደስታውን በስፋት ሲገልጽ የተስተዋለባቸው ቦታዎችም ጥቂት አይደሉም።
ለመጠናቀቅ ድፍን 14 ዓመታትን የፈጀው ታላቁ የኢትዮጵያ ኅዳሴ ግድብ ብዙ አከራካሪ የጂኦፖለቲካ እና የዲፕሎማሲ አውድ ፈተና ሜዳም ሆኖ ቆይቷል። ኢትዮጵያ በራሷ ዜጎች ተሳትፎ የገነባችው የ5 ቢሊየን ዶላር ግድም ፕሮጀክት ዛሬ ተጠናቆ ለምረቃ የበቃበት ምዕራፍ ላይ ከመድረሱ በፊት በርካታ ዲፕሎማሲያዊ ፈተናዎችን ሲያስተናግድም ዜጎችም በተለያየ መልኩ ተሳትፏቸውን ሲያረጋግጡ ነበር። አሁን ብዙ ተስፋ የተጣለበት ግድብ በይፋ ተመርቋል፤ ዜጎች ከግድቡ የትኞቹን ትሩፋቶች ይጠብቃሉ? ከኤሌክትሪክ አቅርቦት ጀምሮ አጠቃላይ ኢኮኖሚያዊ እመርታን ማግኘት ከግድቡ መጠናቀቅ የሚጠበቁ እንደሆነም ተመላክቷል።
ሥዩም ጌቱ
ሸዋዬ ለገሠ
ማንተጋፍቶት ስለሺ