1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ከትግራይ የሚጎራበቱ የአማራ ክልል አካባቢዎች ይዞታ

ዓርብ፣ ነሐሴ 7 2013

ከያዝነው ነሐሴ ወር መጀመሪያ አንስቶ የህወሓት ኃይሎች በወግኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር ከፍተኛ ውድመት ማድረሳቸውን የብሔረሰብ አስተዳደሩ አስታወቀ።

Karte Äthiopien englisch

በአማራ ክልል ወቅታዊው ይዞታ

This browser does not support the audio element.

ከያዝነው ነሐሴ ወር መጀመሪያ አንስቶ የህወሓት ኃይሎች በወግኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር ከፍተኛ ውድመት ማድረሳቸውን የብሔረሰብ አስተዳደሩ አስታወቀ።፣ በደቡብ ጎንደር አንዳንድ አካባቢዎች ደግሞ ውጊያ እንደቀጠለ መሆኑን የዞኑ አስተዳደር ገልጿል፣ በምዕራብ አቅጣጫ ደግሞ ወጣቱ ሰልጥኖ አካባቢውን  እየጠበቀ እንደሆነ ተገልጧል። ጥቃቱ ከተከፈተባቸው አካባቢዎች መካከል አንዱ የዋግኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር ሲሆን ይህ ታጣቂ ኃይል በአበርገሌ ወረዳና በሰቆጣ ወረዳ ፀመራ፣ አቅመዮሐንስ፣ ማይሎሚ፣ አክተራና ሌሎች ቀበሌዎች ጉዳት አድርሶ በፀጥታ ኃሉና በወጣቱ ተጋድሎ መመለሱን የዋግኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር ምክትል አስተዳዳሪ አቶ ተስፋዬ ገብሬ ለዶይቼ ቬለ ተናግረዋል፡፡ በሰሜን ወሎ ዞን አንዳንድ አካባቢዎች የስልክ ግንኙነት ከተቋረጠ ቀናትን ያስቆጠረ በመሆኑ አሁን ያለውን ወቅታዊ ሁኔታ ለማጣራት አለመቻሉን የባሕር ዳር ዘጋቢያችን አክሎ ገልጿል።

ዓለምነው መኮንን

ሸዋዬ ለገሠ

ማንተጋፍቶት ስለሺ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW