ከአምባሳደር ሙሉ ሰለሞን ጋር የተደረገ ቃለ መጠይቅ
ሐሙስ፣ ነሐሴ 26 2014ማስታወቂያ
የኢትዮጵያ መንግስትና ሕወሓት ባለፈዉ ሳምንት ሮብ (ነሐሴ 18) የጀመሩት ዉጊያ ዛሬም እንደቀጠለ ነዉ። የሁለቱ ወገኖች ባለስልጣናት ለአዲሱ ዉጊያ መጀመር አንዳቸዉ ሌላቸዉን ከመዉቀስ ባለፍ ዉጊያዉን አቁመዉ እንዲደራደሩ የተለያዩ ወገኖች የሚያቀርቡትን ጥሪ እስካሁን የተቀበሉት አይመስልም።ዶቸ ቬለ የተፋላሚ ኃይላት ባለስልጣናትን ለማነጋገር በተደጋጋሚ ቢሞክርም እስከ ዛሬ ድረስ አልተሳካለትም ነበር።ዛሬ ግን መቀመጫቸዉን በርሊን አድርገዉ በጀርመን፣ በቼክ፣በስሎቫክና በፖላንድ ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ሙሉ ሰለሞን ብዙን በስልክ አነጋግረናል።አምባሳደሯ እንደሚሉት የኢትዮጵያ መንግስት አሁንም ቢሆን ለሰላማዊ መፍትሔና ድርድር ዝግጁ ነዉ።አምባሳደር ሙሉን ነጋሽ መሐመድ አነጋግሯቸዋል።
ነጋሽ መሐመድ
ኂሩት መለሰ