ማስታወቂያ
በናይጄሪያ በማሕበራዊ ንቅናቄ ሰልፈኞች ላይ ፖሊስ የወሰደው የጭካኔ ተግባር ከተከናወነ 2 ዓመታት አልፈዋል። ነገር ግን ለአንዳንድ ወጣት ናይጄሪያውያን አደጋው ህያው ነው ። እንዲያውም አንዳንዶች አስደንጋጭ ፣ አደገኛ ወይም አስፈሪ ከአስከፊ ውጥረት ወይም ጥቃት በኋላ የሚፈጠር የአዕምሮ መታወክ ተይዘው ቆይተዋል ። በዚህ የጤና መታወክ ወቅት ዶክተር ቺኖንሶ ኤግምባ ከአሰቃቂ ሁኔታ በኋላ በሚከሰት ውጥረት ምክንያት ከሚመጣ የአዕምሮ ጤና እክል ካዳጠመው ወጣት ጋር ቆይታ አድርገዋል ።
