ከኢትዮጵያ የተባረረችው ጋዜጠኛ16 ሰኔ 2002ረቡዕ፣ ሰኔ 16 2002ከኢትዮጵያ በአስቸኳይ እንድትወጣ የተደረገችው የአሜሪካ ድምፅ ራድዮ ጋዜጠኛ አንዳችም ጥፋት እንዳልፈፀመች አስታወቀች ። የምርጫ እና ሌሎች የኢትዮጵያ ዜናዎችን ለመዘገብ ከምርጫው ቀደም ብላ ኢትዮጵያ የገባችው ጋዜጠኛ ሂተር ሞርዶክ ለዶይቼቬለ እንደተናገረችው ለስራዋ አስፈላጊ የሆኑ ፈቃዶችን አግኝታለች ።ማገናኛዉን ኮፒ አድርግምስል DWማስታወቂያሆኖም ዘገባ ለማጠናቀር ወደ ሐረር በሄደችበት አጋጣሚ በአካባቢው ግጭት ስለመኖሩ የሰማችውን መረጃ ካጣራች በኃላ በፖሊስ ተይዛ ሰኔ 10 ,2002 ዓም ከኢትዮጵያ መባረሯን አስታውቃለች ። የዋሽንግተን ዲሲው ወኪላችን አበበ ፈለቀ ካይሮ ግብፅ የምትገኘዋን ጋዜጠኛ ሞርዶክን በስልክ አነጋግሮ ተከታዩን ዘገባ አጠናቅሯል ። አበበ ፈለቀ ፣ ሂሩት መለሰ አርያም ተክሌ