1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ከእስር የተፈቱት የሳዑዲ ልዑል ተናገሩ

ረቡዕ፣ መጋቢት 12 2010

በሳዑዲ ዓረቢያ የጸረ ሙስና ኮሚሽን ተጠርጥረው ለ83 ቀኖች  በቁጥጥር ስር የሰነበቱት የሳዑዲ ታላቁ ባለሀብት አል ወሊድ ቢን ጥላል ለአጎታቸው ንጉስ ሰልማንም ሆነ ለአልጋወራሽ መሀመድ ቢን ሰልማን በየትኛውም መንገድ ድጋፋቸውን እንደሚሰጡ አስታወቁ።

Prinz Walid Ibn Talal
ምስል AP

የሳዑዲ ዓረቢያ ታላቁ ባለሀብት አል ወሊድ ቢን ጥላል

This browser does not support the audio element.

 ልዑሉ ከእስር ከተፈቱ ወዲህ ለመጀመሪያ ጊዜ ከብሉምበርግ ቴሌቪዥን ጋር ባደረጉት ቃለ መጠይቅ በደረሰባቸዉ የያዙትም ቂም እንደሌለ እና ለንጉሱም ሆነ ለአልጋ ወራሹ ይቅርታ ማድረጋቸውን ተናግረዋል። ዎል ስትሬት ጆርናልን ጨምሮ በርካታ መገናኛ ብዙሃን ስድስት ሚሊየን ዶላር ከፍለው ነው የተለቀቁት ብለው ቢዘግቡም እሳቸዉ ግን ምንም የከፈሉት እንደሌለ አጽንኦት ሰጥተዋል። በግላቸው ከንጉሱም ሆነ ከአልጋ ወራሹ ጋር ሚስጢራዊ ስምምነት ማድረጋቸውን ይፋ ያደረጉት ልዑል ወሊድ ቢንጥላል ዝርዝር ሁኔታዎችን ለማብራራት ግን እንደማይፈልጉ ነዉ ያሳወቁት። ከሪያድ ስለሺ ሽብሩ ከሪያድ ተከታዩን ዘገባ ልኮልናል።

ስለሺ ሽብሩ

ሸዋዬ ለገሠ

ኂሩት መለሰ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW