1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ከጀርመኑ የብራንድንቡርግ ፌደራዊ ግዛት ምርጫ ምን ይጠበቃል?

ሐሙስ፣ መስከረም 9 2017

AFD ግዛቲቱን ለ34 ዓመታት የመራውን SPDን ሊያሸንፍ ይችላል የሚል ሰፊ ግምት አለ። ምሥራቅና ምዕራብ ጀርመን ከተዋሀዱአንስቶ ግዛቲቱን ሲመራ የቆየው የሶሻል ዴሞክራቶቹ ፓርቲ SPD በእሁዱ ምርጫ ለመጀመሪያ ጊዜ ስልጣኑን ሊለቅ ይችላል ተብሏል። የግዛቲቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ዲትማር ቮይድከ ይህ እንዳይሆን የምችለውን ሁለ አደርጋለሁ ብለዋል።

ዲትማር ቮልድከ የብራንድንቡርግ ፌደራዊ ግዛት ጠቅላይ ሚኒስትር
ዲትማር ቮልድከ የብራንድንቡርግ ፌደራዊ ግዛት ጠቅላይ ሚኒስትር ምስል IMAGO/Eberhard Thonfeld

ከጀርመኑ የብራንድንቡርግ ፌደራዊ ግዛት ምርጫ ምን ይጠበቃል?

This browser does not support the audio element.

የብራንድንቡርግ የ34 ዓመት መሪ SPD እጣ ፈንታ

 

ምሥራቅ ጀርመን በሚገኙት ትዩሪንገንና ዛክሰን አንሀልት በተባሉት ሁለት ፌደራዊ ክፍለ ግዛቶች በቅርቡ በተካሄደ አካባቢያዊ ምርጫ አማራጭ ለጀርመን በጀርመንኛው ምህጻር AFD የተባለው የጀርመን ቀፅ ጽንፈኛ ፓርቲ ከተጠበቀው በላይ ውጤት አግኝቶ አንጋፋዎቹን ፓርቲዎች ወደ ጎን መግፋቱ ተሳክቶለታል። የፊታችን እሁድ በሌላው የምሥራቅ ጀርመን ፌደራዊ ግዛት በብራንድንቡርግ የፊታችን እሁድ በሚካሄደው ምርጫም AFD ጥንካሬውን ያሳያል ተብሎ ተገምቷል።በጀርመኖቹ በዛክሰን አንሀልት እና ቱሪንገን ፌደራዊ ግዛቶች የተካሄደው ምርጫ ውጤትና መዘዙ

በአንዳንድ የጀርመን ፌደራዊ ግዛቶች፣ በግልጽ ቀኝ ጽንፈኛ ተብሎ የተፈረጀው እና በአሁኑ ጊዜም የጀርመን የሀገር ውስጥ ደኅንነት መሥሪያ ቤት በዓይነ ቁራኛ የሚከታተለው AFD ግዛቲቱን ለ34 ዓመታት የመራውን የመራኄ መንግሥት ኦላፍ ሾልዝ ፓርቲ SPDን ሊያሸንፍ ይችላል የሚል ሰፊ ግምት አለ። ምሥራቅና ምዕራብ ጀርመን ከተዋሀዱበት ጊዜ አንስቶ ግዛቲቱን ሲመራ የቆየው የሶሻል ዴሞክራቶቹ ፓርቲ SPD በእሁዱ ምርጫ ለመጀመሪያ ጊዜ ስልጣኑን ሊለቅ ይችላል ተብሏል። የግዛቲቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ዲትማር ቮይድከ ታዋቂ ቢሆኑም በቀኝ ጽንፈኛው AFD ሊሸነፉ የመቻላቸው ምልክቶች እየታዩ ነው ተብሏል። ቮይድከ ይህ እንዳይሆን የምችለውን ሁለ አደርጋለሁ ብለዋል።
«ይህ የሁለት ወገኖች ፉክክር ነው። እናም በስፋትና በግልጽ በቀኝ ጽንፈኝነት የሚንቀሳቀስ ፓርቲን እዚህ ብራንድንቡርግ የሚካሄደውን ምርጫ እንዳያሸንፍ ሁሉንም ነገር አደርጋለሁ።ይህ የኔ ተግዳሮት ነው፤ በፖለቲካ ህይወቴ ውስጥ ትልቁ ተግዳሮት።» የዛክሰን አንሀልት ምርጫ አንድምታና አስተምህሮቱ 

AFD በብራንድንቡርግ ተጠናክሮ ይወጣል መባሉ

አማራጭ ለጀርመን በብራንድንቡርግ ድሉ የርሱ እንደሚሆን ከወዲሁ እየተናገረ ነው። ፀረ ስደተኞች አቋም የሚያራምደው የፓርቲው መሪ አሊስ ቫይድል ፓርቲያቸው መንግሥት ሲሆን እስከዛሬ በህዝብ ላይ በደል የፈጸሙ ያሏቸውን እናባርራለን ሲሉ ዝተዋል።
«በጀርመን ህዝብ ላይ የሚካሄድ የእምነት  ጦርነት አለ። ለዚህም ነው እኛ መንግሥት ስንሆን እነዚህን በየመንገዶቹ ወንጀል የሚፈጽሙትን ያለ ርህራኄ የምንወረውራቸው። »
በቅርቡ የተካሄደ የዳሰሳ ጥናት AFD እና SPD አንገት ለአንገት ተያይዘው ትንንቅ ላይ መሆናቸውን አመልክቷል። ከአንድ ሳምንት በፊት በተካሄደ የዳሰሳ ጥናት SPD 26 በመቶ ድምጽ እንደሚያገኝ ሲገመት AFD ደግሞ በ29 በመቶ ይመራል ተብሎ ነበር። በሌላ በኩል የክርስቲያን ዴሞክራት ኅብረት ፓርቲ 15 በመቶ አረንጓዴዎቹ እና የግራዎቹ ፓርቲ ፖትስዳም በሚገኘው የግዛቲቱ ፓርላማ ውስጥ መቀመጫ ለማግኘት የሚያስችላቸውን 5 በመቶ ድምጽ እንኳን ማግኘታቸው አጠራጥሯል። 

የAFD ፓርቲ መሪ አሊስ ቫይድል በጀርመን ፓርላማ ሲናገሩ ምስል Ebrahim Noroozi/AP/picture alliance

ስለብራንድንቡርጉ ምርጫ የግዛቲቱ ነዋሪዎች አስተያየት


«በምርጫው AFD በጣም ተጠናክሮ ሊወጣ ይችላል ብዬ እገምታለሁ።የተቀሩት ፓርቲዎች ደግሞ እቅዳቸውን ለማስተዋወቅ ህዝቡን በትክክል ማሳመን የሚችሉ በቂ ጉዳዮችን አላቀረቡለትም»

«አዳዲሶቹ ፌደራል ግዛቶች ስለፍልሰት ምንም ዓይነት በጎ ጎን ልምድ ያላቸው አይመስለኝም። ማናቸውንም የውጭ የሆነ ነገር ወይ ያባርራሉ አለያም ይዋጋሉ ።ይህን ነው የሚያውቁት። እዚ በአንድ ጉዳይ ላይ ልምድ ከሌለህ መከላከል  ነው የተለመደው ።»

የSPD የበብራንድንቡርግ ምርጫ ዘመቻ ምስል IMAGO/Martin Müller

«እውነት ለመናገር በፍርሀትና ባለመረጋጋት ስራችንን እንደቀድሞው እያከናወን አይደለም። ሆኖም እውነት ለመናገር ለችግሮቹ መንስኤዎች የተሳሳቱ ቦታዎችን ነው የምናየው። ሌላው ደግሞ ባለመደሰት ብቻ ወዲያውኑ በሌሎች ፓርቲዎች ተጽእኖ ስር መውደቅ አስቸጋሪ ነው። አብዛኛዎቹን መራጮች ስታናግር የየፓርቲዎቹን ማንፌስቶ እንኳን በቅጡ አያውቁም።ይህም በጣም ያሳዝነኛል።»መጤ ጠሉ አ.ኤፍ.ዴ የገዘፈበት ምርጫ
በጉጉት የሚጠበቀው የእሁዱ የብራንድንቡርግ ምርጫ ውጤት ከሳምንታት በፊት እንደተካሄደው AFD ተጠናክሮ እንደወጣበት የትዩሪንገንና የዛክሰን አንሀልት ምርጫ ውጤት  በሚቀጥለው ዓመት የሚካሄደው የጀርመን ብሔራዊ ምርጫ ውጤት መስታወት ተደርጎ የሚወሰድ ነው ።


ኂሩት መለሰ

ፀሐይ ፍላቱ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW