1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ከጋምቤላ ታፍነው ተወስደው የነበሩ 10 ህጻናት ተመለሱ

ዓርብ፣ ግንቦት 2 2016

በጋምቤላ ክልል ከወር በፊት ጆር በተባለ ወረዳ ውስጥ ከደቡብ ሱዳን የተሻገሩ ታጣቂዎች ባደረሱት ጥቃት ታፍነው ተወስደው ከነበሩት ህጻናት መካከል እስካሁን 10 ህጻናት መመለሳቸውን የክልሉ መንግስት ገልጸዋል፡፡

Äthiopien | Stadt Gambella
ምስል Negassa Desalegn/DW

በጋምቤላ ታፍነው ተወስደው የነበሩ 10 ህጻናት ተመለሱ

This browser does not support the audio element.

በጋምቤላ ክልል በታጣቂዎች ታፍነው ተወስደው የነበሩ 10 ህጻናት ተመልሷል

በጋምቤላ ክልል ከወር በፊት ጆር በተባለ ወረዳ ውስጥ ከደቡብ ሱዳን የተሻገሩ ታጣቂዎች ባደረሱት ጥቃት ታፍነው ተወስደው ከነበሩት ህጻናት መካከል እስካሁን 10 ህጻናት መመለሳቸውን የክልሉ መንግስት ገልጸዋል፡፡ በወቅቱ በክልሉ ውስጥ ከሚንቀሳቀሱ ጸረ ሠላም ከተባሉ ሀይሎች ጋር በመተባበበር ድምበር ተሻግሮ ጥቃት የፈጸሙት የደቡብ ሱዳን ታጣቂዎችበሰው ላይ ካደረሱት ጥቃት በተጨማሪ በመቶዎች የሚቆጠሩ የቁም እንስሳትም መውዳቸውም ተገልጸዋል፡፡ በጆር ወረዳ በወቅቱ በነበረው ጥቃት 6100 የሚሆኑት ነዋሪዎቹ ደግሞ እስካሁን ከቤት ንብረታቸው ተፈናቅለው ይገኛሉ ተብሏል፡፡

በጆር ወረዳ 11 ህጻናት በታጣቂዎች ተወሰደው ቆይተዋል

በአኙዋ ብሔረሰብ ዞን ጆር ወረዳ ከወር በፊት መጋቢት 26/2016 ዓ.ም የደቡብ ሱዳን ታጣቂዎች ወደ አካባቢው በመዝለቅ በነዋሪው ላይ ጥቃት በማድረስ 738 መኖሪያ ቤቶችን ማቃጠላቸውን የዞኑ አስተዳደር መረጃ ያመለክታል፡፡ በወቅቱ በክልሉ ውስጥ ይንቀሳቀሳሉ ከተባሉ ሀይሎች ጋር በመተባበር ጥቃቱ መፈጸሙንና 11 የሚሆኑ ህጻናት ደግሞ ተወስደው እንደነበር ተገልተዋል፡፡ እስካሁን 10 ህጻናት መመለሳቸውን የአኙዋ ብሔረሰብ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ኡቶው ኡኮት ለዶይቸቬለ ተናግረዋል፡፡

በመጋቢት ወር መጨረሻ በዞኑ ጆር ወረዳ ውስጥ በደረሰው ጥቃት ከፍተኛ ወድመት መድረሱን የተናገሩት አቶ ኡቶው የቁም እንስሳት መወሰዳቸውን፣ የሰው ህይወት ማለፉንና የመቁሰል አደጋም መድረሱንም ጠቁመዋል፡፡ በጥቃቱ በሰው ላይ የደረሰው ጉዳት ግን በዝርዝር አልገለጹም፡፡ ታጣቂዎቹ ወደ አኙዋ ብሔረሰብ ዞን ጆር ወረዳ የተሻገሩትን አጎራባች ዞን እና የወረዳው አመራሮች በክልሉ መንግስት በቁጥጥር ስር ውለው ጉዳያቸው እየታየ እንደሚገኝ ገልጸዋል፡፡

ሰብአዊ ድጋፍ እየቀረበ ነው

የጋምቤላ ክልል የአደጋ ስጋት አመራር አገልግሎት ኃላፊ አቶ ጋት ቤል ሙን በበኩላቸው በጆር ወረዳ ለተፈናቀሉ 6100 ዜጎች የዕለት ደራሽ ድጋፎችን ማድረሳቸውን ተናግረዋል፡፡ ከ8 መቶ ኩንል በላይ ምግብ ነክ ድጋፎች በፌደራል መንግስትና ከክልሉ ድጋፍ መደረጉን ጠቁመዋል፡፡ በጆር ወረዳ 2 ከሚደርሱት መንደሮች መሉ በመሉ ሰዎች መፈናቃላቸውን አክለዋል፡፡ በአካባቢው የኔትዎርክ አገልግሎት ባለመኖሩ የተፈናቀሉ ዜጎች የሚገኙበትን ሁኔታና ሀሳባቸውን ለማካተት አልቻለም፡፡

ፎቶ ማህደር፤ ጋምቤላ ከተማ ምስል Negassa Desalegn/DW

በጋምቤላ ክልል መጋቢት 26/2016 ዓ.ም የተከተሰውን የጸጥታ ችግር ጋር ተያይዞ ኃላፈኑታቸውን አልተወጡም የተባሉ 14 የዞንና ወረዳ አመራሮች በቁጥጥር ስር መዋቸውን የሚታወስ ነው፡፡ በቁጥጥር ስር የዋሉት አመራሮች የጸጥታ ችግር ለማስቆም ኃለፊነታቸውን አልተወጡም ወይም በችግሩ ውስጥ እጃቸው አለበት ተብሎ የተጠረጠሩ ናቸው ተብሏል፡፡

ነጋሳ ደሳለኝ

አዜብ ታደሰ

ዮሃንስ ገብረእግዚአብሔር

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW