ከፋኖ ቃል አቀባይ ጋር የተደረገ ቃለ መጠይቅ
ዓርብ፣ መስከረም 11 2016![Äthiopien | Kämpfer der Fano-Miliz in Lalibela in der nördlichen Amhara-Region](https://static.dw.com/image/66530579_800.webp)
ማስታወቂያ
በአማራ ክልል የሸመቀዉ ራሱን የአማራ ሕዝባዊ ኃይል ፋኖ ብሎ የሚጠራዉ ቡድን ከኢትዮጵያ መከላከያ ጦር ጋር በገጠመዉ ዉጊያ ሽንፈት እንዳልገጠመዉ አስታወቀ።የጦርነት ቀናት ውጥረት እና ሥጋት ፣ የዓይን ምስክር ከደብረ ታቦር ባጭሩ ፋኖ በሚል ስያሜ የሚጠራዉ ቡድን ቃል አቀባይ እንደሆኑ የነገሩን ግለሰብ በተለይ ከዶቼ ቬለ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ ታጣቂዎቹ በህዝብ ላይ ያደርሱታል የሚባለዉን ዘረፋና በደል ሙሉ በሙሉ አስተባብለዋል።ስማቸዉ እንዲሸሸግላቸዉ የጠየቁት ቃል አቀባይ፣ ቡድናቸዉ የጠቅላይ ሚንስትር ዓብይ አሕመድን መንግስት በትጥቅ ትግል አስወግዶ የመንግስትነት ሥልጣኑን ለሕዝብ የማስረከብ አላማ እንዳለዉ አስታዉቀዋል።ጅምላ እስር፤ ተመድ፤ ብሪክስና የኑሮ ውድነትይሁንና ቡድኑ ያቀረበዉ አንድ ቅድመ ሁኔታ ከተሞላ ከመንግስት ጋር የመደራደርን ጉዳይ እንደሚያስብበት አስታዉቀዋል።ፋኖ የፖለቲካ ፓርቲ እንደሌለዉ አስታዉቀዋልም።ሙሉ ቃለ ምልልሱን ያድምጡ።በሰሜን ሸዋ ደራ የተከሰተው ግጭት
ነጋሽ መሐመድ
ማንተጋፍቶት ስለሺ