1. ወደ ይዘቱ እለፍ
  2. ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ

ከፍተኛ የህክምና ባለሙያዉ ባሕርዳር ውስጥ ተገደሉ

ዓለምነው መኮንን
ሰኞ፣ ጥር 26 2017

በባሕርዳር ዩኒቨርሲቲ ህክምና ሳይንስ ኮሌጅ ጥበበ ግዮን ሐኪምና ተመራማሪ የነበሩት ዶ/ር አንዷልም ዳኜ ባለፈው ቅዳሜ አመሻሽ ከሥራ ቦታ ወደ ቤታቸው ሲመለሱ ባልታወቁ ታጣቂዎች መንገድ ላይ በጥይት መገደላቸውን የባሕርዳር ዩኒቨርሲቲ አስታውቋል፣ የባለሙያው መገደል ዩኒቨርሲቲውንና የባህርዳር ከተማ ነዋሪዎችን በእጅጉ አሳዝኗል።

ከፍተኛ የህክምና ባለሙያዉ ባሕርዳር ውስጥ ተገደሉ
የባህርዳር ዩንቨርስቲምስል፦ Alemnew Mekonnen/DW

ከፍተኛ የህክምና ባለሙያዉ ባሕርዳር ውስጥ ተገደሉ

This browser does not support the audio element.

አንድ ከፍተኛ የህክምና ባለሙያ ባሕርዳር ውስጥ ተገደሉ
በባሕርዳር ዩኒቨርሲቲ ህክምና ሳይንስ ኮሌጅ ጥበበ ግዮን ሐኪምና ተመራማሪ የነበሩት ዶ/ር አንዷልም ዳኜ ባለፈው ቅዳሜ አመሻሽ ከሥራ ቦታ ወደ ቤታቸው ሲመለሱ ባልታወቁታጣቂዎች መንገድ ላይ በጥይት መገደላቸውን የባሕርዳር ዩኒቨርሲቲ አስታውቋል፣ የባለሙያው መገደል ዩኒቨርሲቲውንና የባህርዳር ከተማ ነዋሪዎችን በእጅጉ አሳዝኗል።
 
የዩኒቨርሲቲው የውስጥ ግኙነትና ኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ግርማው አሸብር ለዶይቼ ቬሌ በሰጡት መግለጫ ዶ/ር አንዷለም ዳኜ በጥይት ተመትተው የተገደሉት በተደጋጋሚ እገታና ግድያ ከሚፈፀምበት “ቆሼ” ከተባለ አካባቢ ባልታወቁ ታጣቂዎች በእለቱ ምሽት 1 ሰዓት አካባቢ  ነው፡፡ አክለውም “ባለሙያው የቀዶ ህክምና ስፔሻሊስት፣ የጉበት፣ የቆሽትና የሐሞትመስመር ሰብ ስፔሻሊስት፣ ተመራማሪና መምህር ነበሩ” ብለዋል፡፡


በ37 ዓመታቸው አንቱ የተባሉት ሐኪምና መምህር ሞት 

ዶ/ር አንዷለም ከዚህ በተጨማሪም በጥበበ ግዮን ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የቀዶ ህክምና አገልግሎት ክፍል ዳይሬክተርም እንደነበሩና ገና በ37 ዓመታቸው “አንቱ” የተባሉ ታላቅ ባለሙያ እንደነበሩ አቶ ግርማው ተናግረዋል። የዶክተር አንዷለም ዳኜ የቀብር ሥነ ሥርዓት የባሕርዳር ዩኒቨርሲቲ ፕረዚደንት፣ የዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ፣ ተማሪዎችና በርካታ የባሕርዳር ከተማ ነዋሪዎች በተገኙበት በባሕረዳር በዓለ እግዚአብሔር ቤተክርስቲያን ስርዓት ፍትሀትና ፀሎት ተደርጎ፣ በድባንቄ መድኃኔያለም ቤተክርስቲያን ሥርዓት ቀብራቸው ትናንት ተፈጽሟል።

የባህርዳር ዩንቨርስቲምስል፦ Alemnew Mekonnen/DW


ታላላቅ ባለሙያዎች እየለቀቁ ነው


ለሚሊዮኖች ፈውስ የሰጡና ወደፊትም ለብዙዎች አለኝታ የነበሩትን ማጣት ብዙዎችን ማሳዘኑን የነገሩን አቶ ግርማው፣ ከዚህ በፊትም ተመሳሳይ ወንጀሎች በሐኪሞችና በሌሎችም የሆስፒታሉ ሠራተኞች ሲፈፀም እንደነበር ገልጠዋል። በዚህ ምክንያት ብዙዎቹ ታላላቅ ባለሙያዎች እየለቀቁወደ ሌላ ቦታ ለመሄድ ተገድደዋል ነው ያሉት፡፡ እንቁ ባለሙያዎችን እንደዚህ ባሉ ወንጀሎች ማጣት ህብረተሰቡን ለጉዳት ማጋለጥ እንደሆነ ነው የተናገሩት፡፡ የህክምና ዶክተር የሆኑና ስማቸው እንዲጠቀስ ያልፈለጉ የማቹ ዶክተር የቅርብ ሠው፣  በበኩላቸው ዶ/ር አንዷለም ዳኜ ጅማ ዩኒቨርሲቲ ሲማሩ በከፍተኛ ማዕረግ እንደተመርቁና እስካሁንም ያን ውጤት የደገመ ተማሪ የለም ብለዋል።


ተማሪ እያሉ አገር እየወከሉ ወደ የተለያዩ አገሮችን ጎብኝተዋል
ተማሪ በነበሩበት ወቅት በጣም ፈጣንና ጎበዝ ተማሪ ስለነበሩ፣ ከኢትዮጵያ እየተወከሉ ወደ በርካታ የዓለም አገራት መጓዛቸውንም ተናግረዋል፡፡ ወደ ባሕር ዳር ከተዛወሩ በኋላም አንድ ዓመት ካስተማሩ በኋላ የቀዶ ህክምና ትምህርት ተከታትለው እስካሁንም በባሕርዳር ዩኒቨርሲቲ የድህረ ምረቃ ታሪክ ከፍተኛ የሚባለውን ውጤት ይዘው ተመርቀዋል ነው ያሉት። የድህረ ምረቃ ተማሪ ሆነውም ለልምድ ልውውጥ አየርላንድ፣ ህንድ፣ ሌሎች አገሮች ተጉዘዋል ብለዋል፡፡ ሆድ ሳይከፈት የሐሞት ህክምና የሚሰጡ በአማራ ክልል ብቸኛ ባለሙያ ነበሩ። ሆድ ሳይከፈት የሐሞት ህክምና መስጠት የሚያስችል ትምህርት የወሰዱና በዘርፉ በአማራ ክልል ብቸኛው ሐኪም እንደነበሩም እኚሁ አስተያየት ስጪ ነግረውናል።

የባህርዳር ዩንቨርስቲምስል፦ Alemnew Mekonnen/DW


አስተያየት ሰጪው ቁጭታቸውን ሲገልፁም “እንደሀገር እኔን ጨምሮ 15 ነባር ሐኪሞች ሞተን እርሱ ቢተርፍ ለአገር ጥቅም ነበር” ነው ያሉት።
ለባህርዳር ከተማ አስተዳደር ፖሊስ መምሪያና  ለአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን  ተደጋጋሚ የስልክ ጥሪ ባደርግም ስልክ ባለመንሳቱ ሀሳባቸውን ማካተት አልቻልኩም፣ ሆኖም የአማራ ክልል የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ የባሕርዳር ፖሊስ መምሪያ ኃላፊን ኮማንደር ዋለልኝ ቢምረውን ጠቅሶ እንደዘገበው “ፖሊስ ድርጊቱን ማን ፈፀመው? እንዴት ተፈፀም? የሚለውን ለመለየት እየተሰራ ነው”
ድርጊቱ እንደተፈፀመ ፖሊስ ወደ ቦይታው በመንቀሳቀስ የተገኙ የቴክኒክ ማስረጃዎችን የማንሳትና ሌሎች ተግባራት መከናዎናቸውን ፖሊስ መግለፁንም ቢሮው አመልክቷል።


ዓለምነው መኮንን

አዜብ ታደሰ

ነጋሽ መሐመድ

ቀጣዩን ክፍል እለፈው የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል እለፈው ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW