1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ከ1300 በላይ የሱዳን ስደተኞች ከመጠለያ ጣቢያ ወጡ

ሐሙስ፣ ግንቦት 1 2016

በሱዳን ባለው ጦርነት ተሰድደው በኢትዮጵያ መተማ አካባቢ ከሚገኙ ስደተኞች መካከል በፀጥታን በምገብ አቅርቦት ችግር ምክንያት አንድ ሺህ ያክሉ ካሉባቸው የስደተኛ ማዕከላት መውጣታቸውን ተፈናቃዮች አመልክተዋል ።የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ችግሮችን ለመፍታት እየተሠራ እንደሆነ ባወጣው መግለጫ ገልጧል፡፡

 Sudan-Äthiopien Grenze
ምስል Nariman El-Mofty/AP/picture alliance

1300 ስደተኞች ከመጠለያው መውጣታቸው ገልጧል

This browser does not support the audio element.

በሱዳን ባለው ጦርነት ተሰድደው በኢትዮጵያ መተማ አካባቢ ከሚገኙ ስደተኞች መካከል በፀጥታን በምገብ አቅርቦት ችግር ምክንያት አንድ ሺህ ያክሉ ካሉባቸው የስደተኛ ማዕከላት መውጣታቸውን ተፈናቃዮች አመልክተዋል ። የስደተኞችና ተመላሾች አገልግሎት በበኩሉ ለስደተኞች አስፋላጊው ጥበቃ እየተደረገላቸው በመሆኑ ከመጠለያ ጣቢያዎች መውጣት አልነበረባቸውም ብሏል፡፡ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ችግሮችን ለመፍታት እየተሠራ እንደሆነ ባወጣው መግለጫ ገልጧል፡፡

በአማራ ክልል ምዕራብ ጎንደር ኩመርና አውላላ ከተጠለሉ 10ሺህ ያክል ስደተኞች መካከል አንድ ሺህ ያክሉ የአቅርቦትና የፀጥታ ችግር አጋጥሞናል በሚል ከመጠለያ ጣቢያዎቻቸው መውጣታቸውን አመልክተዋል፡፡

ከስደተኞች መካከለ በኩመር የስደተኞች ጣቢያ የሚገኝ ስደተኛ ሰዎቹ በተለያዩ ምክንያቶች ከመጠለያው ወጥተዋል፡፡ "ከተባበሩት መንግስታት ድርጅት የስደተኞች ከፍተኛ ኮሚሽን የምንፈልገው ነገር ነበር፣ አሁን ያለንበት አውላላ ሰው የሚሰፍርበት ኤደለም ለምን አሁን መፍትሔ አይፈለግለትም፣ የምግብ እጥረትም ነበረ፣ የፀጥታ ችግርም አለ በሚል ጥያቄዎች አቅርበናል፡፡” ብሏል፡፡

ችግሮቹ እንዲፈቱ ለሚመለከተው አካል ማቅረባቸውን የሚገልፀው ይኸው ስደተኛ ኃላፊዎቹ ጊዜ ስጡንና ችግሮች በሂደት ይፈታሉ ቢሉም ፈቃደኛ ያልሆኑ ስደተኞች ከመጠለያው ወጥተዋል ነው ያለው፡፡

የሚመለከታቸው አካላት ጊዜ እንዲሰጥ የጠየቁ ቢሆንም አንዳንዶች ትዕግስት አትተው አጥተው መሄዳቸውንና ይህ አስተያየት ሰጪና ሌሎች ግን ሁኔታውን በመጠለያ ሆነው ሁኔታውን እየተከታተሉ እንደሆነ ነው ያመለከተው፡፡ ጆሴፍ የተባለ በአውላላ የስደተኞች መጠለያ ስደተኛ ከሌላ አካባቢ ሚመጡ ዘራፊዎች ስልኮቻችን ይቀሙናል፣ ይደበድቡናል ብሏል፡፡ "ሞባይል ስልከየሚነጥቁ አሉ፣ እኔ ራሴ ገበያ በሄድኩበት ተደብድቤ ስልኬ ተወስዷል ዘራፊዎቹ በአካባቢው ሉ ሳይሆን ከሌላ አካባቢ የሚመጡ ከተራራ ማዶ ያሉ ናቸው፡፡” በሏል፡፡

ምስል Alemenew Mekonnen/DW

የዓለም ዋጭ፣ የኩመርና የአውላላ የስደተኞችና ተመላሾች አገልግሎት አስተባባሪ አቶ ታምራት ደምሴ ለዶይቼ ቬሌ እንደገለፁት የፀትታ ችግር አጋጥሞናል በሚል አንድ ሺህ የሚሆኔ የሱዳን ስደተኞች ከመጠለያቸው ወጥተዋል፣ ሆኖም አስፈላጊው የፀጥታ ሥራ እየተሰራ በመሆኑ ስደተኞ ወደ ቦታቸው እንዲመለሱ እየተሰራ ነው ብለዋል፣ ግን በስደተኞች መካከል ነገሮች እንዲባባሱ የሚያደርጉ ወገኖች እንዳሉም አብራርተዋል፡፡

" ከዋናው መጠለያ ወደ አንድ ኪሎ ሜትር አካባቢ ወደ ጎንደር እንሄዳለን ብለው ወጥተዋል፣ ለምን ሲባሉ የፀጥታ ችግር አለ ይላሉ፣ ፌደራል ፖሊስ አለ፣ የአገር መከላከያ አለ፣ ተመለሱ ፀጥታውን እናስጠብቃለን ብለናል፣ ብዙዎቹ ፈቃደኛ አይደሉም፣ የተወሰኑ በእርግጥ ተመልሰዋል፣ አንዳንድ ልዩ ተልዕኮ ያላቸው ስደተኞች ይኖራሉ ያንን እያጣራን ነው፡፡” ሲሉ ለዶይቼ ቬለ አስረድታል፡፡

የምዕራብ ጎንደር የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ ኃላፊ አቶ ፋንታሁን ቢሆነኝ በበኩላቸው አስፈላጊው ማህበራዊ አገልግሎትና የፀጥታ ጥበቃ እየተደረገ በመሆኑ የወጡ ስደተኞች መመለስ እንደሚገባቸው ተናግረዋል፡፡የዞኑአ አስተዳደር ስደተኞቹ ከአገራቸው ሲወጡ ጀምሮ በመላካም ሁኔታ ተቀብሎ ቦታ ሰጥቶ ሲያስተናግዳቸው ነበር፣ አሁንም ንን ያስቀትላል ነው ያሉት፡፡

የተባበሩት መንግሰታት ድርጅት የስደተኞች ከፍተኛ ኮሚሸን (UNHCR) ሰሞኑን ባወጣው መግለጫ በፀጥታ ስጋትና በምግብ አቅርቦት ችግር ምክንት ከኩመርና አውላላ የስደተኞች መጠለያ 1ሺህ 300 የሚሆኑ ስደተኞች ከመጠለያው መውጣታቸውን ጠቁሞ ሆኖም የፀጥታውንም ሆነ የምግብ አቅርቦቱን ለማሻሻል እየሰራ እንደሆነ አመልክቷል፡፡

ምስል Alemenew Mekonnen/DW

እንደተባበሩት መንግስታት ድርጅት የስደተኞች ከፍተኛ ኮሚሽን መረጃ በአማራ ክልለ ምዕራብ ጎንደር ዞን አውላላ የስደተኞች መጠለያ ጣቢያ 2ሺህ አብዛኛዎቹ የሱዳንና ደቡብ ሱዳን ስደተኞች ሲኖሩ፣በዚሁ ዞን ኩመር የስደተኞች መጠለያ ጣቢያ ደግሞ 6 ሺህ500 የኤርትራ፣ የሱዳንና የደቡብ ሱዳን ስደተኞች ይኖራሉ፡፡

ኮሚሽኑ እንዳስታወቀው በሱዳን ባለፈው ዓመት ሚያዝያ በተቀሰቀሰው ጦርነት 53ሺህ500 ስደተኞች ድንበር አቋርጠው በአማራ ክልል መተማና በቤኒሻንጉል ክልል እንደሚኖሩ አመልክል፡፡ ኢትዮጵያ 1 ሚሊዮን ስደተኞችን በማስተናገድ በአፍሪካ ከፍተኛ ያለው ስደተኛ በማስተናገድ በአፍሪካ ሁለተኛዋ አገር መሆኗም ተጠቅሷል፡፡

ዓለምነው መኮንን

ማንተጋፍቶት ስለሺ

ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW