የኢትዮጵያ እግር ኳስን ትውልደ ኢትዮጵያውያን ተጨዋቾች ይታደጉ ይሆን?
ዓርብ፣ ኅዳር 13 2017ጀርመን ሀገር ነዋሪ የሆኑት አቶ ዳቪድ በሻህ በኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የውጭ አገራት ነዋሪ ተጨዋቾች ምልመላ ክፍል ኃላፊ ናቸው ። ለኢትዮጵያ ብሔራዊ የእግር ኳስ ቡድን በውጭ አገራት የሚኖሩ ትውልደ ኢትዮጵያውያን ተጨዋቾችን መመልመል የውጤት ለውጥ ያመጣል የሚል ጽኑእ እምነት አላቸው ። አቶ ዳቪድ ለዚህም እንቅስቃሴ በማድረግ በውጭ ሃገራት የሚኖሩ ወደ ሁለት መቶ የሚጠጉ ትውልደ ኢትዮጵያውያንን አነጋግረው ሙሉ መረጃዎቻቸውን በዲጂታል ሠንደዋል ።
የኢትዮጵያ እግር ኳስ ከ1970ዎቹ ወርቃማ ጊዜ ወዲህ የከፋ ደረጃ በሚባል መልኩ ላለፉት ዐሥርተ ዓመታት ውጤቱ እያሽቆለቆለ ነው ። ከቅርብ ጊዜያት አንስቶ የኢትዮጵያ ብሔራዊ የእግር ኳስ ቡድን በአብዛኛው ዓለም አቀፍ ውድድሮች ላይ ሽንፈት እያስተናገደ ነው ። ከዚህ በስተጀርባ ያለው ዋና ምክንያት ምንድን ነው?
አቶ ዳቪድ ጀርመን ሀገር በFC Viktoria Koln 1904 e.V በሚባለው የእግር ኳስ ቡድን ውስጥ "Jugendscout" (የወጣቶች መልማይ) ከመሆኖ በፊት በኢትዮጵያ ቡና ክለብ ለሁለት ዓመታት ተጫውተው ነበር ። ካለፉት ሦስት ዓመታት አንስቶ ደግሞ በኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ውስጥ ካሉ ወሳኝ ግለሰቦች ወደ አንዱ መሆን ችለዋል ። በፌዴሬሽኑ ውስጥም የውጭ አገራት ተጨዋቾች ምልመላ ክፍል ኃላፊ ናቸው ።
ብሔራዊ ቡድናችን ለአፍሪቃ ዋንጫ AFCON 2029 ዝግጅት ከአሁኑ መጀመር አለበት ብለዋል ። ለዚያ ደግሞ «ጠንካራ ቡድን ማቋቋም አስፈላጊነትን» አስምረውበታል ። «በውጭ አገር የሚገኙ ተጫዋቾቻች»ን ጠንካራ ቡድን ለመመስረት ወሳኝ መሆኑን ገልጠዋል ። ምን ለማለት ፈልገው ይሆን? አቶ ዳቪድን በአንድ ለአንድ ዝግጅት ቦን በሚገኘው ስቱዲዮዋችን አነጋግረናቸዋል ።
ከድምፅ ማእቀፉ ሙሉ ቃለ መጠይቁን ማድመጥ ይቻላል ።
ማንተጋፍቶት ስለሺ
ታምራት ዲንሳ