1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ከ60 በላይ የመብት ተሟጋቾች በኢትዮጵያ መንግስት ላይ

ዓርብ፣ የካቲት 24 2015

ኢትዮጵያ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት (ተመድ) የሰብአዊ መብት ጥሰቶች መርማሪ ቡድን ሥራ እንዲቋረጥ ያቀረበችውን ጥያቄ በርካታ ዓለም አቀፍ የመብት ተሟጋች ድርጅቶች ተቃወሙት ። ተቋማቱ ያሳሰባቸው ምንድን ነው?

Schweiz Genf | Sitzung UN-MenschenrechtsratSchweiz Genf | Sitzung UN-MenschenrechtsratSchweiz Genf | Sitzung UN-Menschenrechtsrat
ምስል Salvatore Di Nolfi/KEYSTONE/picture alliance

ገበያው ስለ መንግስትና የተቋማቱ ጥያቄ ማብራሪያ አለው

This browser does not support the audio element.

ኢትዮጵያ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት (ተመድ) የሰብአዊ መብት ጥሰቶች መርማሪ ቡድን ሥራ እንዲቋረጥ ያቀረበችውን ጥያቄ በርካታ ዓለም አቀፍ የመብት ተሟጋች ድርጅቶች ተቃወሙት ። ሂዩማን ራይትስ ዎችን ጨምሮ ከ60 በላይ ዓለም አቀፍ እና የሀገር ውስጥ የመብት ተሟጋች ድርጅቶች በጋራ በመሆን ለተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰብአዊ መብቶች ምክር ቤት አባላት እና ታዛቢዎች ይፋዊ ጥሪ አስተላልፈዋል ። ተቋማቱ ያሳሰባቸው ምንድን ነው? ለገበያው ያቀረብንለት የመጀመሪያ ጥያቄ ነበር። 

ተቋማቱ በጥሪያቸውም የኢትዮጵያ መንግሥት ውሳኔ እንዳሳሰባቸው ገልጠዋል ። ዓለም አቀፍ ተቋማቱ፦ «የኢትዮጵያ ምክትል ጠቅላይ ሚንሥትር ደመቀ መኮንን የካቲት 8 ቀን፣ 2015 ዓ.ም ለአፍሪቃ ኅብረት ሥራ አስፈጻሚ ምክር ቤት» ያሰሙትን ንግግር በማጣቀስ ንግግራቸው «አሳስቦናል» ብለዋል ። የኢትዮጵያ መንግስት «የሰብአዊ መብቶች በኢትዮጵያ ዓለም አቀፍ ኮሚሽን» (ICHREE) የሥራ ኃላፊነት እንዲቋረጥ ለማስደረግ በቀጣዩ የተመድ የሰብአዊ መብቶች ምክር ቤት ጉባኤ ላይ አቤት ለማለት ማቀዱን ለአፍሪቃ ኅብረት መንገሩንም ድርጅቶቹ ገልጠዋል ። በኢትዮጵያ ሰሜናዊ ክፍል በተለይም በትግራይ ክልል በነበረው ጦርነት የተፈጸሙ የሰብአዊ መብት ጥሰቶችን እንዲመርምር ከአንድ ዓመት በፊት በመንግስታቱ ድርጅት የተቋቋመው የባለሞያዎች ቡድን ሥራና ኃላፊነት እንዲቋረጥ የኢትዮጵያ መንግስት ጥረት እያደረገ መሆኑን ከጄነቫ የወጡ ዘገባዎች ያመለክታሉ ።

ማንተጋፍቶትስ ለሺ

ገበያው ንጉሤ

ነጋሽ መሐመድ
 

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW