1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ኩረጃ በተንቀሳቃሽ ስልኮች

ዓርብ፣ ሚያዝያ 4 2005

ት/ቤት ውስጥ በፈተና ወቅት በቁራጭ ወረቀት ላይ መልስ ፅፎ መቀባበል ጊዜ ያለፈበት ይመስላል። አሁን የዘመኑን ተንቀሳቃሽ ስልክ ተጠቅሞ ከአንዱ የክፍል ጠርዝ የሌላኛው ጠርዝ ድረስ መልዕክት በመላላክ ይኮረጃል አልያም በስልኩ ኢንተርኔት ውስጥ ተገብቶ መልስ ይፈለጋል። ይህ የሚደረገው በበለፀገው አለም ብቻ አይደለም። በኢትዮጵያም ጭምር እንጂ።

ምስል Fotolia/lassedesignen

ትምህርት ቤት ውስጥ በፈተና ወቅት በቁራጭ ወረቀት ላይ መልስ ፅፎ መቀባበል ጊዜያለፈበት ይመስላል። አሁን የዘመኑን ተንቀሳቃሽ ስልክ ተጠቅሞ ከአንዱ የክፍል ጠርዝ የሌላኛው ጠርዝ ድረስ መልዕክት በመላላክ ይኮረጃል አልያም በስልኩ ኢንተርኔት ውስጥ ተገብቶ መልስ ይፈለጋል። ይህ የሚደረገው በበለፀገው አለም ብቻ አይደለም። በኢትዮጵያም ጭምር እንጂ። « ኩረጃ በተንቀሳቃሽ ስልኮች» የዛሬው የወጣቶች አለም ርዕስ ነው።

በት/ቤት ውስጥ የተማሪዎች ስልክ መጠቀም እየተለመደ ነው።ምስል picture-alliance / dpa/dpaweb

ኩረጃ ከትምህርት ቤት ጨርሶ የሚጠፋ አይመስልም። ይጠፋልም ብሎ ለመገመት ያዳግታል። ግፋ ቢል የኩረጃ መንገዱ ከጊዜ ወደ ጊዜ ይቀያየር ይሆናል። የዘመኑ ኩረጃ ቴክኖሎጂ ባመጣው የተንቀሳቃሽ ስልክ ሆኗል።

ስማርት ፎን በመባል የሚታወቁት እጅግ ዘመናዊ ስልኮች በተስፋፉባቸው ሀገራት ፤ በትምህርት ቤት ፈተና ወቅት፤ኩረጃን እጅግ ቀላል አድርጎታል። መልስ መላላክ፣ ገፆችን ፎቶ አንስቶ በመግባት ከስልክ ላይ መኮረጅ፣ ያልታሰበ ጥያቄም ከሆነ በፈጣኑ ኢንተርኔት እንደ ዊኪፒዲያ ያሉ ገፆች ላይ መልሱ ይፈለጋል። ኩረጃ በተንቀሳቃሽ ስልኮች ኢትዮጵያ ውስጥ ምን ያህል ተስፋፍቷል? ሁለት የኮሌጅ ተማሪዎች ያጫወቱን አለ።

ስልክን የመሰለ ቴክኖሎጂ ተማሪዎች ጋ መድረሱ መልካም ቢሆንም ያለአግባቡ እየዋሉ እንደሆነ አንዳንድ አስተማሪዎችም ያውቃሉ። ነፃነት በአንድ የከፍተኛ ትምህርት ተቋም አስተማሪ ናት። 31 አመቷ ነው። በክፍል ውስጥ አስተማሪ እና ተማሪን ስለሚያጋጨው የተንቀሳቃሽ ስልክ ጉዳይ በሚገባ ታውቀዋለች። እሷ እና የስራ ባልደረቦቿ ስለሚገጥማቸው ነግራናለች።

ከውጭው ሀገር የመጣ እንደ ተንቀሳቃሽ ስልክ ያለ ተክኖሎጂ ወጣቱ ዘንድ መድረሱ ጥሩ ቢሆንም አልፎ አልፎ በአንዳንድ ተማሪዎች ዘንድ ያለአግባብ እየዋለ ነውና በተለይ የመምህራንን ጥብቅ ቁጥጥር ይሻል። ሙሉውን ዝግጅት ከድምፅ ዘገባው ያገኙታል።

ልደት አበበ

ሸዋዬ ለገሠ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW