1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል
ፖለቲካሰሜን አሜሪካ

ካማላ ሃሪስ የዲሞክራት ፓርቲ ፕሬዝዳንታዊ እጩነታቸውን በይፋ ተቀበሉ

ዓርብ፣ ነሐሴ 17 2016

የአሜሪካዋ ም/ል ፕሬዝዳንት ካማላ ሃሪስ በትላንትናው ምሽት የዲሞክራት ፓርቲ ፕሬዝዳንታዊ እጩነታቸውን በይፋ ተቀብለዋል።ባለፉት አራት ቀናት ቺካጎ ውስጥ ሲካሄድ በቆየው የዲሞክራት ፓርቲ ብሄራዊ ጉባኤ ላይ የፓርቲው ዋና ዋና የፖለቲካ አቀንቃኞች ተገኝተው ድጋፋቸውን ገልጸዋል።

 ካማላ ሃሪስ፤የአሜሪካ ም/ል ፕሬዝዳንት
ካማላ ሃሪስ፤የአሜሪካ ም/ል ፕሬዝዳንትምስል Brynn Anderson/dpa/AP/picture alliance

ካማላ ሃሪስ የዲሞክራት ፓርቲ ፕሬዝዳንታዊ እጩነታቸውን በይፋ ተቀበሉ

This browser does not support the audio element.


የአሜሪካዋ ም/ል ፕሬዝዳንት ካማላ ሃሪስ በትላንትናው ምሽት የዲሞክራት ፓርቲ ፕሬዝዳንታዊ እጩነታቸውን በይፋ ተቀብለዋል። ባለፉት አራት ቀናት ቺካጎ ውስጥ ሲካሄድ በቆየው የዲሞክራት ፓርቲ ብሄራዊ ጉባኤ ላይ የፓርቲው ዋና ዋና የፖለቲካ አቀንቃኞች ተገኝተው ድጋፋቸውን ገልጸዋል። በም/ል ፕሬዝዳንትነት የታጩት የሚኒሶታው ገዢ ቲም ዋልትዝም ከትላንት በስትያ እጩነታቸውን በይፋ ተቀብለዋል። ም/ል ፕሬዝዳንት ሃሪስ በትላንት ምሽት ባደረጉት ንግግር ከተመረጡ የሚተገብሯቸውን የሃገር ውስጥና የውጪ ግንኙነት ፖሊሲ መሰረታዊ እቅዶች ይፋ አርገዋል።
የአሜሪካዋ ም/ል ፕሬዝዳንት ካማላ ሃሪስ በትላንትናው ምሽት የዲሞክራት ፓርቲ ፕሬዝዳንታዊ እጩነታቸውን በይፋ ተቀብለዋል። ባለፉት አራት ቀናት ቺካጎ ውስጥ ሲካሄድ በቆየው የዲሞክራት ፓርቲ ብሄራዊ ጉባኤ ላይ የፓርቲው ዋና ዋና የፖለቲካ አቀንቃኞች ተገኝተው ድጋፋቸውን ገልጸዋል።

የሚተገብሯቸውን የሃገር ውስጥና የውጪ ግንኙነት ፖሊሲ መሰረታዊ እቅዶች 

በም/ል ፕሬዝዳንትነት የታጩት የሚኒሶታው ገዢ ቲም ዋልትዝም ከትላንት በስትያ እጩነታቸውን በይፋ ተቀብለዋል። ም/ል ፕሬዝዳንት ካማላ ሃሪስ በትላንት ምሽት ባደረጉት ንግግር ከተመረጡ የሚተገብሯቸውን የሃገር ውስጥና የውጪ ግንኙነት ፖሊሲ መሰረታዊ እቅዶች ይፋ አርገዋል።
ከአራት ሳምንታት በፊት የትላንቱ ምሽት የፕሬዝዳንት እጩነት እሳቤ በም/ል ፕሬዝዳንት ካማላ ሃሪስ የሃሳብ አጥር ጥግ ውስጥ አልነበረም። የፕሬዝዳንት ጆ ባይደንን በእድሜም በፓርቲያቸው ግፊትም ከፕሬዝዳንታዊ ውድድር መውጣት ተከትሎ፣ የዲሞክራቲክ ፓርቲን እጩነት ካማላ ሃሪስ አራት ቀናት በፈጀው የዲሞክራቲክ ፓርቲ ጉባኤ ላይ በይፋ ተቀብለዋል።
ም/ል ፕሬዝዳንት እጩ አርገው የመረጧቸው የሚኒሶታው ገዢ ቲም ዋልትዝም ከትላንት በስትያ እጩነታቸውን በይፋ ተቀብለዋል። በጉባኤው ላይ የዲሞክራት ፓርቲ የፖለቲካ ዘዋሪወች ታድመው ከርመዋል። ካማላ ሃሪስ ከየትኛውም ጎራ ብትመጡ እኔ የሁላችሁም ፕሬዝዳንት እሆናለሁ ብለዋል።

ም/ል ፕሬዝዳንት ካማላ ሃሪስ፤ በትላንት ምሽት ባደረጉት ንግግር ከተመረጡ የሚተገብሯቸውን የሃገር ውስጥና የውጪ ግንኙነት ፖሊሲ መሰረታዊ እቅዶች ይፋ አርገዋልምስል Vincent Alban/REUTERS

 የኢኮኖሚ አማራጮችን የማስፋት፣ የግብር ቅነሳን ተፈጻሚ የማድረግ ተስፋ 

የአሜሪካን ድንበር የሚያስጠብቅና ህጋዊ ዜግነትን የሚያሰፍን መንገድ እንደሚያበጁም ገልጸዋል። ጠንካራ በመሃከለኛ ኢኮኖሚ ላይ የሚገኝን መህበረሰብ ለማጎልበት፣ የኢኮኖሚ አማራጮችን ለማስፋት፣ የግብር ቅነሳን ተፈጻሚ ለማድረግም ቃል ገብተዋል። የሴቶች ጤና፣ የህጻናት ደህንነናት፣ የጥቁሮች መብት መከበረም ከአላማና ግባቸው ውስጥ አሉ። ለህጻናት ደህንነትን፣ ክብርንና ፍትህን ለማጎናጸፍ እሰራለሁ ብለዋል። አሜሪካንን የሚያምሰውን የህገወጥ መሳሪያወችና ግድያወችን ለመግታትም እንደሚሰሩ ተናግረዋል።

በውጪ ፖሊሲያቸውም ማንም ቀና ብሎ የማያየው ጠንካራ ወታደራዊ ሃይል መገንባት፣ ከሰሜን አትላንቲክ ጦር ቃልኪዳን ሃገራት ጋ ያለውን ግንኙነት ማጠናከር እና ከዩክሬይን ጋ በመቆም የራሽያን ጦረኝነት ልክ ማስገባት እቅዳቸው እንደሆን ጠቁመዋል። የእስራኤልና የፍልስጤምን ችግር በተመለከተም፣ ታጋቾች የሚለቀቁበትና የተኩስ አቁም የሚፈረምበት ስራ እየተሰራ መሆኑን ጠቁመዋል። አሜሪካ ከእስራኤል ጎን በማያወላውል ሁኔታ ሁል ጊዜ እንደምትቆም ያስታወቁት ካማላ ሃሪስ የጋዛ ነዋሪወች አሳዛኝ ህይወት እጅጉን እንደሚያሳስባቸው ገልጸዋል። ፍልስጤሞች ከክብራቸው፣ ከደህንነታቸው እና ራሳቸውን ከማስተዳደር መብታቸው ጋ የሚኖሩበት ሁኔታን ለመፍጠር እንደሚሰሩ ቃል ገብተውል።
ከህንዳዊ እናት እና ከጃማይካዊ አባት የተወለዱት ካማላ ሃሪስ ፕሬዝዳንት ሆነው ከተመረጡ የመጀመርያዋ ሴት፣ ኤዥያዊትና ጥቁር አሜሪካዊ ፕሬዝዳንት ይሆናሉ። 

 

ሙሉ ዝግጅቱን የድምፅ ማዕቀፉን ተጭነው ያድምጡ።

አበበ ፈለቀ
ዮሀንስ ገብረእግዚአብሄር
ፀሀይ ጫኔ

 

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW