ካንሰርም ይድናል!
ማክሰኞ፣ ጥቅምት 9 2003ማስታወቂያ
ካንዴም ሁለቴ በተለያዩ የካንሰር ህመሞች የተያዙትና በህክምና ርዳታ ጤናቸዉ የተመለሠዉ አሜሪካዊ የፀረ ካንሰር ዘመቻ ተባባሪ ወይዘሮ ከተሞክሯቸዉ ተነስተዉ፤ «ካንሰርም እንደሌሎች የበሽታ ዓይነቶች ቶሎ ህክምናዉን ከተከታተሉ ይድናል» ይላሉ። የእድሜ፤ የፆታም ሆነ የዘር ልዩነት የማያዉቀዉ ካንሰር ገና ከተወለደ ጨቅላ አንስቶ በእድሜ እስከጎለበተዉ ወገን ድረስ ሁሉን እንደሚነካካ ባለሙያዎች ያስረዳሉ። መፍትሄ የሌለዉ የሚመስለዉ ይህ አደገኛ በሽታ ቀድሞ የነቃበት ድል እንደሚያደርገዉ ማሳሰቢያዉ ቀጥሏል።
ሸዋዬ ለገሠ
ተክሌ የኋላ