1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ኬንያና የዓለም ዓቀፉ የጦር ወንጀሎች ተመልካቹ ፍርድ ቤት

ዓርብ፣ ታኅሣሥ 15 2003

በኬንያ ፓርላማ አገሪቱ ከዓለም ዓቀፉ የጦር ወንጀሎች ተመልካች ፍርድ ቤት ICC አባልነት እንድትወጣ ሀሳብ ቀርቧል። 6 ባለስልጣናት በዓለም ዓቀፉ ችሎት ይፈለጋሉ።

የICC አቃቤ ህግ ሉዊስ ሞሬኖ ኦካምፖምስል AP

ይህ ሀሳብ የቀረበው በ2006 እንደ ጎርጎሮሳውያን አቆጣጠር በኬንያ ተደርጎ የነበረውን ምርጫ ተከትሎ በተቀሰቀሰውና የሰው ህይወት በጠፋበት ብጥብጥ ላይ እጃቸው አለበት 6 ባለስልጣናት ላይ የክስ ወረቀት በICC ከተቆረጠ በኋላ ነው። አሁን ለፓርላማው የቀረበውን ሀሳብ ያነሱት የምክር ቤት አባላት የዓለም ዓቀፉ የጦር ወንጀሎች ተመልካች ፍርድ ቤትን ክስ ከቅኝ ግዛት ጋር አያይዘውታል።በዚሁ በኬንያ ፓርላማ በተሳው ሃሳብ ላይ ዘሪሁን ተስፋዬ የዴይሊ ኔሽን ጋዜጠኛን በማነጋገር ያጠናቀረውን ዘገባ ልኮልናል።

ዘሪሁን ተስፋዬ

ሸዋዬ ለገሠ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW