ኬንያ በተከሰተ ድርቅ ከ 200 በላይ ዝሆኖች ሞቱ
ዓርብ፣ ጥቅምት 25 2015
ማስታወቂያ
ከአራት አስርት ዓመታት ወዲህ በኬንያ በተከሰተዉ ከፍተኛ ድርቅ ከ200 በላይ ዝሆኖችና በመቶዎች የሚቆጠሩ የሜዳ አህዮች እንዲሁም ሌሎች የዱር አዉሬዎች መሞታቸዉን የሀገሪቱ የቱሪዝም ሚንስትር ዛሬ ገለፀ። ይህ ድርቅ ያስከተለዉ ቀዉስ በኬንያ ወደ ግማሽ ቆዳ ስፋት የሚህል ክልልን እና ከ 50 ሚሊዮን ህዝቦቿ መካከል ቢያንስ አራት ሚሊዮን ህዝብን በድርቅ እንደተጎዳ ተነግሯል። የኬይና ቱሪዝም ሚኒስትር ፔኒና ማሎንዛ ዛሬ ዓርብ ናይሮቢ ላይ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ «ድርቁ የዱር እንስሳትን ለሞት ሲዳርግ፣ በአብዛኛው ዕፅዋት እንዲጠፉ ዳርጓል ፤ 14 የዱር አራዊቶች ዝርያ በድርቁ ክፉኛ ከስተዋል» ብለዋል። በኬንያ፣ በሶማሊያና በኢትዮጵያ አራት ተከታታይ የዝናብ ወቅቶች ዝናብ ሳይዘንብ በመቅረቱ በአፍሪቃ ቀንድ ሃገራት በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎች ለከፍተኛ ረሃብ ተጋልጠዋል። ድርቁ ባስከተለዉ ቀዉስ በኬንያ ብቻ ከ1.5 ሚሊዮን በላይ ከብቶች ሞተዋል።
አዜብ ታደሰ
ሸዋዬ ለገሠ