1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የዲጂታል ልዩነቱን ማጥበብ

ረቡዕ፣ ጥቅምት 12 2001

በማዳመጥ መማር ከመረጃ መረብ ቴክኖሎጂ ለመ ገናኘትና ከዓለም አቀፍ መ ረብ ዕውቀት መጠቀም ለሚ ፈልግ ለማንኛውም ሰው ተግባራዊ ምክር ይሰጣል።

ምስል CORBIS

የዲጂታል ልዩነቱን ማጥበብ

በአፍሪቃ የ«ዲጂታል» አገልግሎት ልዩነት ቢኖርም አፍሪቃ በፍጥነት እየገባችበት ትገኛለች---ለተጨማሪ ይቀጥሉ የመረጃ መረቦች እየተስፋፉና ትንንሽ የገጠር ከተሞችን ከትላልቆቹ በማ ያያዝ ከዓለም አቀፍ የመረጃ ፍሰት እንዲገናኙ እያደረጉ ነው። ያገለገሉ ኮምፕዩተሮች የአብዛኛውን ሕዝብ ገቢ ባገናዘበ ዋጋ በመሸጥ ላይ ናቸው። በማዳመጥ መማር ከመረጃ መረብ ቴክኖሎጂ ለመ ገናኘትና ከዓለም አቀፍ መ ረብ ዕውቀት መጠቀም ለሚ ፈልግ ለማንኛውም ሰው ተግባራዊ ምክር ይሰጣል።

የመረጃ መረብ ግዙፍ የሆነ ዓለም አቀፋዊ የዕውቀት ክምችት ይዟል።

በአሁኑ ሰዓት ትምህርት ቤቶችና ዩኒቨርስቲዎች የተለያዩ የትምህርት ዓይነቶች የዲግሪ መረሃ ግብርን ጨ ምሮ በመረጃ መረብ በማስደገፍ እየሰጡ ይገኛሉ። በመረጃ መረብ ውስጥ የሚ ገኙ ኢንሳይክሎፒድያዎች ሁሉን አቀፍ የሆነ ዓለማችንን የሚ መለከት የመረጃ ክምችት ያቀርባሉ። ከዚህ በተጨ ማሪ የተለያዩ ባህልና ዜግነት ያላቸው ሰዎች በመረጃ መረቡ ሃሳባቸውንና ልምዳቸውን ይለዋወጣሉ።

ኢንተርኔት የሚ ጠቀሙ ና የማይጠቀሙ ሰዎች ልዩነቶች

በማዳመጥ መማር በጣም ሰፊ የሆኑ ዝግጅቶችን በመረጃ መረብና በኮምፕዩተር አማካኝነት ያቀርባል። ስለ የኤሌክትሮኒኩ ዓለም ዕውቀታቸውን ማስፋት ለሚፈልጉ ሰዎች ሰፊ የዕድል በር ይከፍትላቸዋል። ስለ ዓለም አቀፉ የመረጃ ፍሰት ማወቅ የሚፈልጉትን ማንኛውንም ነገር ያገኛሉ። ይህ ማለት ትክክለኛውን ኮምፒዩተር ከማግኘት አልፈው ኢንተርኔትን በመጠቀም ከመላው ዓለም ጓደኞችን እስከማፍራት የሚያስችላቸውን ትምህርት ሁሉ ማግኘት ይችላሉ።

በማዳመጥ መማር የተሰኘው ዝግጅት በስድስት ቋንቋዎች ማለትም በአማርኛ፣ ኪስዋሂሊ፣ ሃውሳ፣ ፈረንሳይኛ፣ እንግሊዝኛና ፖርቱጋልኛ ይቀርባል። ተጨማሪ መረጃ ወይም ዝግጅቶቹን ደግመው ለማዳመጥ ከፈለጉ እባክዎንwww.dw-world.de/learning-by-ear የተሰኘውን ድረ ገጻችንን ይጎብኙ።በማዳመጥ መማር የተሰኘው ፕሮጀክት በጀርመን ፌደራላዊ የውጪ ጉዳይ ሚ ኒስቴር ይታገዛል።

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW