የአማራ መስተዳድ እርምጃ
ማክሰኞ፣ መጋቢት 15 2012ማስታወቂያ
የአማራ ክልላዊ መስተዳድር የኮሮና ተሕዋሲ ስርጭትን መከላከል ያስችላል ያለውን እርመጃ ደንብ አወጣ።ነዋሪዎቹ ግን የመስተዳድሩ አንዳድ ደንቦች ዉጤት ማምጣታቸዉን ይጠራጠራሉ።የአማራ ምክትል ርዕሠ-መስተዳድር ፋንታ ማንደፍሮ ትናንት ማምሻውን ለጋጠኞች በሰጡት መግለጫ የክልሉ መንግስት ስርጭቱን ለመከላከል በተለይ በትራንስፖርት ዘርፉ ላይ አዲስ አሰራር ደንግጓል፡፡ዶክተር ፋንታሁን እንዳሉት ከዚህ በፊት 12 ሰዎችን ያሳፍሩ የነበሩ የከተማ ታክሲዎች 8 ሰዎችን ብቻ እንዲጭኑ፣ እስካሁን 3 ሰዉ ይጭኑ የነበሩ ባለሶስት እግር ተሽከርካሪዎች ወይም ባጃጆች ደግሞ 2 ሰው ብቻ እንዲጭኑ መስተዳድሩ ደንግጓል።በክልሉ የሚገኙ መሸታ ቤቶች፤አዝማሪና ጭፈራ ቤቶች ከዛሬ ጀምሮ እንዲዘጉ ተወስኗልም።
ዓለምነዉ መኮንን
ነጋሽ መሐመድ
ኂሩት መለሰ