1. ወደ ይዘቱ እለፍ
  2. ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ

ኮንጎ፡ በተፈናቃዮች ላይ ከደርሰው ጥቃት ጀርባ ሩዋንዳ ተጠያቂ ናት?

ቅዳሜ፣ ግንቦት 3 2016

በዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ (DRC) የሰሜን ኪቩ ግዛት በተፈናቃዮች መጠለያ ካምፖች ላይ በደረሰ በቦምብ ጥቃት 15 ሰዎች ሲሞቱ 35 ሰዎች ደግሞ በጽኑ መቁሰላቸዉ ቁጣን አስከትሏል። የምስራቅ የጎማ ከተማ ተፈናቃዮችን ለመቋቋም እየታገለ ነው።

የዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ተፈናቃዮች
የዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ተፈናቃዮችምስል፦ Moses Sawasawa/AP Photo/picture alliance

ኮንጎ፡ በተፈናቃዮች ላይ ከደርሰው ጥቃት ጀርባ ሩዋንዳ ተጠያቂ ናት?

This browser does not support the audio element.

በዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ (DRC) የሰሜን ኪቩ ግዛት ባለፈው ሳምንት በተፈናቃዮች መጠለያ ካምፖች ላይ በደረሰ ፍንዳታ 15 ሰዎች ሲሞቱ 35 ሰዎች ደግሞ በጽኑ መቁሰላቸዉን የግዛቲቱ ወታደራዊ ገዥ ፒተር ሲሪምዋሚ ተናግረዋል። በሰሜን ኪቩ ውስጥ ከሚገኙት ማሲሲ፣ ሩትሹሩ እና ኒራጎንጎ ግዛቶች የ M23 ሚሊሻዎች መሬቶችን በሚቆጣጠሩበት የምስራቅ የጎማ ከተማ ተፈናቃዮችን ለመቋቋም እየታገለ ነው።

በሰሜን ኪቩ የሚገኝ አንድ የኮንጎ ጦር ሰራዊት ቃል አቀባይ፤ በዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ  ላክ ቨርት እና በጎማ ዳርቻ በሚገኘው ሙጉንጋ የተፈናቃዮች ካምፖ ላይ ባለፈዉ አርብ ማለዳ ላይ ተኩሰዋል፤ ሲሉ M23 የተባለዉ ታጣቂ ቡድን ያቀረበዉን ክስ ውድቅ አድርገዋል።

ባለፈው ሳምንት በተፈናቃይ ካምፖች ውስጥ ምን ተፈጠረ?

እማኞች እንደተናገሩት፤  ባለፈዉ አርብ በኮንጎ በሚገኘዉ የስደተኞች መጠለያ ካምፕ አቅራቢያ የሚገኙ የመንግስት ሃይሎች ከማለዳ ጀምሮ በመጠለያዉ በስተ ምዕራብ በሚገኙ ኮረብታዎች ላይ አማፂያኑን እየደበደቡ ነበር።  አንድ ታዋቂ አቀንቃኝ በበኩሉ“M23 አማጺ ቡድንም ያለምንም ልዩነት ቦምብ በመወርወር አጸፋውን መልሷል።

ኮንጎ በአፍሪቃ ከፍተኛ የውስጥ ተፈናቃዮች ያሉባት አገር ናት ምስል፦ Moses Sawasawa/AP/picture alliance

ከቤተሰቦቻቸው ጋር በተፈናቃዮች ካምፕ ተጠልለዉ የሚገኙት ኮንጎዊው ካምባል ኪዮማ በM 23 ታጣቂዎች ለሊቱን በርካታ ጥቃት መጣሉን ተናግረዋል።  

«የቦንብ ጥቃቱ ከየት እንደመጣ አናውቅም፤ ተኝተን ነበር ። ተፈናቃዮች በሚኖሩበት ቤት ላይ ነዉ የተተኮሰዉ ፤ በጥቃቱ ሰዎች ተገድለዋል፤ ቆስለዋል፤ ብዙ ቦንቦች ነዉ ተፈናቃዮቹ በሚገኙበት አካባቢ ወድቋል»  

እና እዚህ በመጠለያ ካምፕ ተረስተናል ያሉት ኮንጎዋዊዉ ተፈናቃይ መንግሥት ሰላምን እንዲመልስ እንፈልጋለን ሲሉ ተናግረዋል። ሳፊ ካሴምቤ የተባሉ ሌላዋ ተፈናቃይ ለፈረንሳዩ የዜና ወኪል ለአዣንስ ፍራንስ ፕሬስ እንደተናገሩት  እንደተናገረው የኮንጎ መንግስት በካምፑ ውስጥ የመድፍ መሳሪያ ማስወንጨፍያ መትከሉን እና ይህ  ህይወታቸውን አደጋ ላይ መጣሉን ተናግረዋል።

«እኔ እዚህ ያለሁት በጦርነቱ ምክንያት ነው፣ ከመኖርያ መንደሮቻችን ሸሽተን ነዉ በዚህ የተፈናቃዮች ካምፕ ውስጥ የተጠለልነዉ። እንዳለመታደል ሆኖ  እዚህም በዓማፅያኑ በቦምብ ተመትተናል ። በካምፑ ውስጥ የተተከሉ መሳሪያዎችም አሉ ። አደጋ ላይ የጣሉን እነዚህ የተኩስ ልውውጥዎች ናቸው። ለአንዳንዶቻችንም የሞት ምክንያት ሆንዋል። ልንቋቋመዉ ያልቻልነዉ ሁኔታ ላይ ነን።  በጣም እየተሰቃየን ነው ። »

የቦምብ ጥቃት ሰለባዎች ተዘክረዋል

ይህ በእንዲህ እንዳለ በቦምብ ጥቃት የተገደሉትን ለመዘከር በተዘጋጀው ሥነ-ስርዓት ላይ የበርካታ ዜጎች ንቅናቄ አባላት በምስራቅ ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ የተነሳውን ብጥብጥ አውግዘዋል።  ባለፈው ሳምንት በተፈናቃዮች ካምፕ በተፈፀመ ጥቃት ለተገደሉ ሰዎች ፍትህ እንዲሰጥም ጠይቀዋል።

የፍሊምቢ የፍሊምቢ የወጣቶችን ተሳትፎ የሚሻ የኮንጎ የፖለቲካ ንቅናቄ አባል ክሪስቶፍ ሙይሳ "ጦርነቱን ሸሽተው ዛሬ በተፈናቃይ ካምፖች ውስጥ የሚገኙ ሰዎች መጠጊያና ደህንነት ማግኘት አለባቸው፤ አለመታደል ሆኖ ዛሬ የሚወረወሩት ቦምቦች ወደ ተሸሸጉበት ቦታ እያሳደዳው ነዉ" ሲሉ  ተናግረዋል።  

«ቁሳቁስም ሆነ እርዳታ አያስፈልጋቸውም። ወደ ቤታቸው ለመመለስ ሰላም እና ደህንነት ነዉ የሚያስፈልጋቸዉ። ስለዚህ ዛሬ የተደረገው እርዳታ ሁሉ፣ በዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ላይ መሳለቂያ፣ እና የግብዝነት ማሳያ ነው።  መንግሥት ለዚህ ትኩረት እንዳይሰጥ እንጠይቃለን። »

ሌላዉ ኮንጎዋዊዉ የለውጥ ትግል የሚቆመው የሲቪል ማህበረሰብ ንቅናቄ አቀንቃኝ ጆሱ ዋላይ ምስራቃዊ ኮንጎ ለመኖሪያነት የማይመች ቦታ ሆንዋል ይላሉ። "ከጥቃት ቀያቸውን ጥለው በጠለያ ቦታ የሚገኙ ሰዎች በሚያሳዝን ሁኔታ በረሃብ እየሞቱ እና ሌላ አሰቃቂ ሞት እየደረሰባቸው ነው። በቦምብ ተገድለዋል ፣ ተገድለዋል"።

አሜሪካ ተጠያቂነትን እንዲሰፍን አሳስባለች

ዩናይትድ ስቴትስ ጥቃቱን በማውገዝ ሩዋንዳ ከጀርባው ያሉትን ኃይሎች እንድትቀጣ ጠይቃለች። በዚህም ኪጋሊ የሚገኘዉ መንግሥት በጎረቤት ጉዳይ ጣልቃ ይገባል የሚለዉን ክስ አጠናክራለች።  

የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ማቲው ሚለር ዩናይትድ ስቴትስ "የሩዋንዳ መንግስት ይህን አስነዋሪ ድርጊት መርምሮ ተጠያቂነትም ማስፈን አለበት። ይህንም ግልፅ አድርገናል።" ሲሉ ተናግረዋል።

ከላይ የሚታየዉ የትዊተር መልዕክት፤ በጎርጎሳዉያኑ 1994 ዓም ከሩዋንዳ በቱትሲዎች ላይ የተካሄደውን የዘር ማጥፋት ዘመቻ በሸሹ በሁቱ ባለስልጣናት የተመሰረተ ቡድን ማለትም «የሩዋንዳ ነፃ አውጪ ዲሞክራሲያዊ ሃይል» (FDLR) ሲሆን ዋዛለንዶ ደግሞ የክርስቲያናዊ ቡድን ነው።

ሩዋንዳ እሁድ እለት በሰጠችው መግለጫ የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በስደተኞች መጠለያ ካምፖ  ውስጥ ለጠፋው ህይወት ሩዋንዳ ላይ በአስቸኳይ እና ያለ ምንም ምርመራ ጥፋተኛ ለማድረግ መሞከሩ «ትክክል ያልሆነ እና ያልተረጋገጠ» ብላለች።

M23 የሚዋጋው ለምንድነው?

በዲሞክራቲክ ኮንጎ የሚንቀሳቀሰዉ አማፂ ቡድን M23 በሃገሪቱ  የሚገኘውን የማዕድን ሀብት፣ የመዳብ፣ የወርቅ እና የአልማዝ ክምችቶችን ለመቆጣጠር ይፈልጋል ሲባል ሲከሰስ ቆይቷል።

ኮንጎ በዓለማችን ለኤሌክትሪክ መኪናዎች እና ለሞባይል ስልክ ባትሪዎች ዋና አካል የሆነውን ንጥረ የኮባልት ከፍተና ክምችት የሚገኝባት ሃገር ነች።  

በጎርጎረሳዉያኑ መጋቢት  2022 ዓ.ም M 23 ከአስር ዓመታት አንጻራዊ መረጋጋት በኋላ በዩጋንዳ እና በሩዋንዳ ድንበር አቅራቢያ በሚገኙ የኮንጎ ጦር ሰፈር ላይ ጥቃት ሰንዝሮ በአካባቢዉ የሚገኙ ነዋሪዎ ለደህንነታቸው እንዲሰደዱ አድርጓል።

ዩናይትድ ስቴትስ በበኩልዋ ሩዋንዳ የM 23 አማፂያንን ትደግፋለች በሚል በኮንጎ የቀረበባትን ክስ የሚያረጋግጥ ማስረጃ እንዳለ ስትናገር መቆየትዋም ይታወቃል።

ይህም ሆኖ ዋሽንግተን በሁለቱ ሀገራት መካከል ሽምግልና ለማድረግ ሞክሯል። የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን ከሩዋንዳው ፕሬዝዳንት ፖል ካጋሜ ጋር በጥር ወር ዳቮስ፣ ስዊዘርላንድ በተካሄደው የዓለም ኢኮኖሚ ፎረም ላይ ከተገናኙ በኋላ ያለዉን ችግር ለመፍታት በሁሉም ወገኖች በኩል አስፈላጊው ዲፕሎማሲያዊ እርምጃ እንደሚወስድ ተስፋ ሰጥተዋል።

 

አይዛክ ሙጋቤ / አዜብ ታደሰ

ዮኃንስ ገብረእግዚአብሔር 

ቀጣዩን ክፍል እለፈው የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል እለፈው ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW