1. ወደ ይዘቱ እለፍ
  2. ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ

ወሎ ዉስጥ የሚደረገዉ ዉጊያ እንቅስቃሴን አጎለ

ኢሳያስ ገላው
ማክሰኞ፣ መስከረም 27 2018

ባለፉት 2 ዓመታትበአማራ ክልል በመንግስት እና በፋኖ ኃይሎች መካከል እየተካሄደ የሚገኘው ጦርነት በንግድ ሥራችን ላይ የጎላ ተፅዕኖ አሳድሯል የሚሉት ነጋዴዎች በቅርቡ እያየለ የመጣው ጦርነትሥራችንን ለመስራት አላስቻለንም ይላሉ፡፡

ሸሪፍ ተራ-ደሴ፣ በሰሜንና ደቡብ ወሎ ዞኖች በመንግሥት የፀጥታ ኃይላትና በፋኖ ታጣቂዎች መካከል የሚደረገዉ ዉጊያ የንግዱን እንቅስቃሴ እየጎዳዉ መሆኑን ነጋዴዎች አስታወቁ
ሸሪፍ ተራ-ደሴ፣ በሰሜንና ደቡብ ወሎ ዞኖች በመንግሥት የፀጥታ ኃይላትና በፋኖ ታጣቂዎች መካከል የሚደረገዉ ዉጊያ የንግዱን እንቅስቃሴ እየጎዳዉ መሆኑን ነጋዴዎች አስታወቁምስል፦ Esayas Gelawe/DW

ወሎ ዉስጥ የሚደረገዉ ዉጊያ እንቅስቃሴን አጎለ

This browser does not support the audio element.

               

በአማራ ክልል በሰሜንና ደቡብ ወሎ ዞኖች በመንግስትና በፋኖ ሀይሎች መካከል ሰሞኑን የሚደረገዉ ዉጊያ  የአካባቢዉን የንግድ እንቅስቃሴ ማወኩን ነጋዴዎች አስታወቁ።ከሳምንታት በፊት የተጀመረዉ ዉጊያ ተጠናክሮ መቀጠሉ ተነግሯ።ነጋዴዎቹ እንደሚሉት በጦርነቱ ምክንያት መንቀሳቀስ ባለመቻላቸዉ የሸቀጦች ዋጋ ንሯል።በተለይ አነስተኛ ነጋዴዎች ለኪሳራ እየተዳረጉ ነዉ።


ባለፉት 2 ዓመታትበአማራ ክልል በመንግስት እና በፋኖ ሀይሎች መካከልእየተካሄደ የሚገኘው ጦርነት በንግድ ሥራችን ላይ የጎላ ተፅዕኖአሳድሯል የሚሉት ነጋዴዎች በቅርቡ እያየለ የመጣው ጦርነትሥራችንን ለመስራት አላስቻለንም ይላሉ፡፡ 

‹‹የንግድ እንቅስቃሴው ተዳክሟል፤ ከበፊቱ  አንፃር ሲታይሰላም በሌለበት ሁኔታ ውስጣዊም ውጫዊም ሰላምየለም፡፡ ይህ ጦርነት ከደሴ የተወሰነ ኪ/ሜትር ሄደህ ኩታበር ላይእንደፈለክ አትንቀሳቀስም ከደሴ ትንሽ በወጣህቁጥር ሰላምየለም›› 

የመንገድ መዘጋት በንግድ ስራዉ ላይ ያስከተለዉ ተፅዕኖ የጎላ ነዉ

«ከወደቀ ጠላት ጋር የምናደርገዉ ድርድር የለም» የፋኖ ቃል አቀባይ

This browser does not support the audio element.

በአግባቡ መገናኘት ባለመቻሉ የሸቀጣሸቀጥ እና የፋብሪካ ግብዓቶችን ከቦታ ቦታ ማጓጓዝ አለመቻላችን የንግድ ሥራው የቀዘቀዘ እንዲሆን እና እኛም እየከሰርን ያለንበት ሁኔታ ነው ያለው ይላሉ ነጋዴዎቹ

የጦርነትጉዳይ አሳሳቢ ስለሆነ ገዥም የለም በፊት የነበረን ሁሉንነገርነው ያጣነው ገንዘባችንን የከሰርንበት ኑሯችን ዝቅ ያለበትነው፡፡›› 

የመንገድ መዘጋት እና በየጊዜው የሚጨምር የትራንስፖርት ክፍያ መናር በቁሳቁስ ላይ ከፍተኛ የዋጋ ጭማሪ እንዲከሰት አድርጓል የሚሉት ነጋዴዎቹ ያም ሆኖ ግን የንግድ ስራውን የማስቀጠል ሁኔታ ቢኖርም በየአካባቢው ያሉ የገቢዎች ቅርንጫፎች እየጣሉት ያለው ግብር መናር የወቅቱን ያላገናዘበ የንግዱን ማህበረሰብ ለተጨማሪ ችግር የሚዳርግ ነው ይላሉ፡፡ 

‹‹ይህንን አራት አምስት አመት ያለው ሁኔታ የንግድእንቅስቃሴውን ጎድቶታል ጦርነቱ የዱሮው ጋርማነፃፀርበጣም ይከብዳል፤ ገቢዎች ያለውን ሁኔታ የጦርነት ሁኔታውንያገናዘበ አይደለም የሚሰሩት፤ በፊትኩንታል 400 ብር የነበረጭነት አሁን 700 ብር ገብቷል፡፡›› 

ኪሳራ ያስተናገዱ ነጋዴዎች

በባለፉት ሁለት ዓመታት የንግዱ እንቅስቃሴ የተገደበ መሆን በነጋዴው ላይ ተፅዕኖው የጎላ ነው የሚሉት የዘርፉ አንቀሳቃሾች ለቤት ኪራይ የሚሆን ክፍያ እያጣን ነው ይላሉ፡፡ 

‹‹አሁን ላይ ያለንበት ሁኔታ እጅግ በጣም ከባድ ነው፤ የቤትኪራይ እንኳን መክፈል አልቻልንም፡፡ ሰርተንቤተሰብማስተዳደር ቀርቶ የቤት ኪራይ ልንከፍል አልቻልንምህይወታችንንም መምራት አቅቶናል፡፡›› 

በክልሉም ሆነ በፌዴራል ገቢዎች የሚወጡ የገቢ ግብር አዋጅእና መመሪያዎች አካባቢው ያለበትን ሁኔታ ሳያገናዝብ ተፈፃሚእየሆነ ነው የሚሉት ነጋዴዎች አልፎ አልፎም በሀይልመመሪያዎችን የማስፈፀም ተግባር ይስተዋላል ይላሉ፡፡ 

‹‹የተለያዩ ህጎች ሲወጡ ደሴ ላይ የተለየ ተፅዕኖ ያለይመስለኛል ህግ አውጭው እና ህግ ፈፃሚውየሚነጋገሩአይመስልም ህግ ሲወጣ ነጋዴውን አያማክሩም አንዳንዴበጉልበት ያስፈፅማሉ፡፡›› 

አቤቱታ ለማቅረብ መቸገር

የንግዱ እንቅስቃሴ በተዳከመበት በነፃነት ተንቀሳቅሶ የመነገድ እድሉ በጠበበበት በዚህ ጊዜ በየጊዜው ከሚታየው ተለዋዋጭ የዋጋ ንረት እና የእንቅስቃሴ ክልከላ ባሻገር የገቢዎች የግብር ውሳኔ ተጨማሪ ሸክም ነው ይላሉ ነጋዴዎቹ፡፡ 

‹‹ሰው እንዲባላ እንጂ እንዲኗኗር አልፈለጉም፣ ገበያየለም፣ዝግት ያለ ነው፣ አሁን ችግር ላይ ነው ያለነውወደየትእንሂድ ወደማንስ እናልቅስባቸው፣›› 

በዚህ ዜና ዙሪያ አስተያየታቸውን እንዲሰጡን የደሴ ከተማናየደቡብ ወሎ ዞን አስተዳደር የገቢዎች መምሪያ ኃላፊዎች ጋርብንደውልም ምላሽ ሊሰጡን አልቻሉም፡፡  

ኢሳያስ ገላዉ

ነጋሽ መሐመድ

ፀሐይ ጫኔ


 

ቀጣዩን ክፍል እለፈው የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል እለፈው ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW