1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ወስባዊ ጥቃት በህንድ

ዓርብ፣ ታኅሣሥ 26 2005

የ 23 ዓመቷ ህንዳዊት የህክምና ተማሪ ነበረች ። ያለፈው ቅዳሜ በሚያሳዝን ሁኔታ ህይወቷ አልፏል።

Kerzenmeer am Jantar Mantar für das Opfer der Vergewaltigung am 16. Dezember. Copyright: DW/Sandra Petersmann Januar, 2012, Neu Delhi
ምስል DW/S. Petersmann

ከሶስት ሳምንት በፊት በወጣቷ ላይ ስድስት ወንዶች የቡድን ወሲባዊ ጥቃት ፈፅመው በብረት ደብድበው በመጓዝ ላይ ከነበረችበት አውቶብስ ወርውረው ጥለዋታል። ወጣቷ በህክምና እየተረዳች ብትቆይም ከደረሰባት ውስባዊ የአካል ጉዳት ማገገም ግን አልቻለችም።

ምስል DW/S. Petersmann

ህንድ ውስጥ ለዓመታት የሴቶችን መብት ለማስከበር የሰብዓዊ መብት ተቆርቋሪዎች በመጣር ላይ ይገኛሉ። ሆኖም ዛሬ በሴቶች ላይ በርካታ ጥቃት ይደርሳል እንዲሁም የእኩልነት መብታቸው ይረገጣል። የወጣቷ አሟሟት በአለም ዙሪያ ከፍተኛ የመገናኛ ብዙኃን ሽፋን ያግኝ እንጂ በህንድ እኢአ በ2011 ዓም ብቻ ከ24 000 በላይ አስገድዶ የመድፈር ጥቃት ተመዝግበዋል። ይህ አሃዝ በአንድ አመት ጊዜ ውስጥ በ2000 መጨመሩ ታይቷል። ይህን ፆታዊ ጥቃት ከሚያደርሱት ወንጀለኞች መካከል በቁጥጥር ስር የሚውሉት ግን ከአራቱ ወንዶች መካከል አንዱ ወንጀለኛ ብቻ ነው።

የህንድ ፖሊስ እንዳስታወቀው በፆታ ጥቃት ህይወቷ የጠፋውን የ 23 ዓመት ወጣት ጉዳይ በጥብቅ እየተከታተለ ይገኛል። በትናንትናው ዕለት ፖሊስ አስገድዶ በመድፈር የተጠረጠሩ ስድስት ሰዎችን ነፍስ በማጥፋት ወንጀል ለፍርድ አቅርቧል። ይህ ሲሆን በሌላ በኩል በርከት ያሉ የህግ ባለሙያዎችም ከዋና ከተማዋ ፍርድ ቤት ፊት ለፊት በመሰለፍ ሴቶች ላይ የሚፈፀም ፆታዊ ጥቃት እንዲገታ ጠይቀዋል።

በመዲና ኒው ዴህሊ የተደረገ ተቃውሞምስል dapd

«የህግ ባለሙያዎች በጉዳዩ በጣም አዝነዋል። የህግ ግንዛቤዉ አለ፤ ወንጀሉ ምን ያህል ከብዶ እንደተፈፀመ እንረዳለን። በሀገራችን ዛሬም ቢሆን ሴቶች ደህንነታቸዉ አልተረጋገጠም። እኛ ወንዶች ነን ሆኖም ሴቶቻችን ደህንነታቸዉ እንዲከበር እንፈልጋለን።»

ጉዳዩ የህግ ባለሙያዎችን ብቻ ሳይሆን በርካታ የሀገሪቱ ህዝብንም አስቆጥቷል። የወጣቷን አሳዛኝ ዜና ታሪክአለም ዳንኤል ከአዲስ አበባ በመገናኛ ብዙኋን ተከታትላዋለች። አስተያየቷን አካፍላናለች። እንዲሁም ኢትዮጵያ ውስጥ ስለሚታየው አስገድሶ የመድረር ጉዳይ በተመለከተም በፌስ ቡክ የተለያዩ አስተያየቶች ደርሰውናል።

በህንድ የሞት ቅጣት እንብዛም የተለመደ እንዳልሆነ እና በጣም አስከፊ ወንጀሎች ሲደርሱ ብቻ በተግባር ላይ እንደሚውል ነው ዘገባዎች የሚያመላክቱት። በህንድ እኢአ ከ 2004 ዓም ከተበየነ አንድ የሞት ቅጣት በኋላ እኢአ 2008 ሞምባይ ውስጥ የፍንዳታ ጥቃት በጣለ ዜጋ ላይ ከጥቂት ሳምንታት በፊት ዳግም የሞት ቅጣቱ ተግባራዊ ሆኖ ነበር።

ዛሬ በህንድ ሰሜን ምስራቃዊ ግዛት 600 ጊታር ተጫዋጮች ሟቿን ወጣት « ኢማጅን » በተሰኘው የጆን ሌንን ዜማ ዘክረዋታል። ከሙዚቃ አዘጋጆቹ አንዷ ሶናም ቡቲያ ይህንን ዜማ የመረጡበት ምክንያት ስለ ተስፋ፣ ነፃነት እና ቃል ኪዳንን ስለሚያወሳ ነው ብለዋል።

አስገድዶ መድፈርን በተመለከተ የተቀናበረውን ዘገባ ማድመጥ ይችላሉ።

ልደት አበበ

ሸዋዬ ለገሠ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW