1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ወቅታዊው የአንበጣ መንጋ ይዞታ

ማክሰኞ፣ ሐምሌ 14 2012

FAO ከቀናት በፊት ያወጣው ማሳሰቢያ በምሥራቅ አፍሪቃ ተጠናክሮ የሰነበተው የአንበጣ መንጋ ወደ ሕንድና ፓኪስታን አቅጣጫ መትመሙን ያመለክታል። በሰሜን ምዕራብ ኬንያ አካባቢ እድገቱን ያልጨረሰ የአንበጣ መንጋ ደግሞ ገሚሱ ወደ ዩጋንዳና ደቡብ ሱዳን ቀሪው ወደ ኢትዮጵያ ሊሰደድ እንደሚችም  ጠቁሟል።

Kenia Heuschreckenplage
ምስል picture-alliance/AP Photo/B. Curtis

«ያላባራው የአንበጣ መንጋ በምሥራቅ አፍሪቃ»

This browser does not support the audio element.

የዓለም የኤኮኖሚ መድረክ ይፋ ባደረገው መረጃ መሠረት ካለፈው ዓመት ሰኔ ወር ገደማ አንስቶ ኢትዮጵያን ጨምሮ በተለያዩ የምሥራቅ አፍሪቃ ሃገራት ተበራክቶ የተከሰተው የአንበጣ መንጋ አምስት ሚሊየን የሚሆኑ ሰዎች ለከፋ ርሃብ ሊያጋልጥ እንደሚችል ተገምቷል። የአንበጣው መንጋም በአንድ ቀን 35 ሺህ ሰዎች ሊመገቡት የሚችለውን ያህል ምግብ ሊያወድም እንደሚችልም ጠቁሟል። የዓለም የምግብና እርሻ ድርጅት በእንግሊዝኛ ምህጻሩ FAO ባለፈው ሳምንት ባወጣው ማሳሰቢያ በሰሜን ምዕራብ አካባቢ የሚታየው በርካታ እድገቱን ያልጨረሰ የአንበጣ መንጋ አንድ ወደ ዩጋንዳና ወደደቡብ ሱዳን አንድም ወደ ደቡባዊ የኢትዮጵያ ግዛት አቅጣጫ እንደሚጓዝ አመልክቷል። ድርጅቱ በማሳሰቢያው  በዚያ ስፍራ እንደደረሰ ፈጥኖ እንቁላል ሊጥል ይችላል የሚል ግምቱንም አመልክቷል። በተለይም በምሥራቅና ሰሜን አካባቢ አድጎ ሊዋለድ እንደሚችል ይህ ደግሞ አሁን እዚያው ካለው የአንበጣ መንጋ ተዳምሮ ብዛትና ወረራውን እንደሚያጠናክርም ገልጿል።  ከሰኔ 2011 ዓ,ም አንስቶ ከፍተኛ የአንበጣ መንጋ ወረራ በተለያዩ አካባቢዎች ባጋጠሟት ኢትዮጵያ በዚህ የክረምት ወራት ይዞታው በምን ደረጃ ይገኝ ይሆን? በግብርና ሚኒስቴር የእፅዋት ጥበቃ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ተወካይ የሆኑት አቶ ታምሩ ከበደ ከፍተኛ የመከላከል ሥራ እየተሠራ ነው ይላሉ። 

ምስል picture-alliance/dpa/AP/B. Curtis

ምሥራቅ አፍሪቃ ላይ የተከሰተው  የአንበጣ መንጋ ቀውስ ከ25 ዓመታት ወዲህ መሆኑ ሲገለፅ በተለይ በኬንያ ሶማሊያና ኢትዮጵያ ደግሞ ስጋቱ ተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚችል የሚያመለክቱ ጥናቶች ወጥተዋል።  የዓለም የምግብና እርሻ ድርጅት እንዲሁም የዓለም የኤኮኖሚ መድረክ ዘገባዎች በበኩላቸው በአንበጣ መንጋው ቀውስ ላይ የኮቪድ 19 ወረርሽን ያስከተለው ተፅዕኖ ሲደመርበት በዚህ አካባቢ ወደ አምስት ሚኒየን ሕዝብ ለከፋ ረሃብ ሊያጋልጥ እንደሚችል ስጋታቸውን ያመለክታሉ። ባለፉት ወራት ኢትዮጵያ ውስጥ የአንበጣው መንጋ ያደረሰው ጉዳት ለመናገር ጥናቶች መጠናቀቅ አለባቸው ይላሉ አቶ ታምሩ። በሰኔ 2011 የተከሰተው የአንበጣ መንጋ በምሥራቅና በሰሜንም ምሥራቅ እንዲሁም በደቡብ የተለያዩ አካባቢዎች ከፍተኛ ጫና ማስከተሉ ይታወሳል። አሁን ምንም እንኳ ክትትሉ ቢኖርም ሰዎች በማይደርሱበት አካባቢ የሚፈለፈል አንበጣ መንጋ ሆኖ ተፅዕኖ ሊያስከትል አይችልም ማለት አይቻልም እንደባለሙያው።  

ሸዋዬ ለገሠ 

ኂሩት መለሰ

 

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW