«አውቄው ቢሆን ኖሮ» ትረካ
ቅዳሜ፣ ሚያዝያ 21 2015ማስታወቂያ
ታሪኩ የሚከናወነው የቶማስ ሞላ የትውልድ ስፍራ በሆነችው ጎምቢያ ነው። በሀያዎቹ አጋማሽ የሚገኘው ቶማስ እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ የቤተሰብ ምጠና ምን ያህል አስፈላጊ እንደሆነ አያውቅም ነበር። ስለሆነም ባለቤቱ ሊያ በእርግዝናዎች መካከል ማገገሚያ ጊዜ ለምን እንደምትሻ ፈፅሞ አይረዳም ነበር። ቶሎ ቶሎ ማርገዝ የእናትየዋን እና የፅንሱን ጤንነት አደጋ ላይ ሊጥል ስለመቻሉም አያውቅም ነበር። ቶማስ በአሁኑ ሰዓት ግቢው ውስጥ የሚገኝ አንድ የፓፓያ ዛፍ ስር ቁጭ ብሎ ቤተሰቡን ስለገጠው ነገር በፀጸት ይገልፃል።
ይህ የወንጀል ተፋላሚዎቹ ትረካ የቤተሰብ ምጣኔን ጥቅም ፣ ሴቶች በአካሎቻቸው ላይ የመወሰን መብት እንዳላቸው እና ወንዶች ከሴቶች ጋር በእኩልነት መኖር እንዳለባቸው ያሳያል።
ደራሲ: ማርታ ባሮሶ (ሞዛምፒክ)
ተራኪ : አንዱዓለም ተስፋዬ
ትርጉም እና ቅንብር : ልደት አበበ