1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ወደ ሃመር ጉዞ

እሑድ፣ ሰኔ 7 2001

ከሰማንያ በላይ ቋንቋ የሚነገርባት የተለያዩ ብሄር ብሄረሰቦችን ያቀፈችዉ ኢትዮጽያችን ቀለመ ደማቅ ናት። በያዝነዉ ሳምንት የኢትዮጽያ የደራስያን ማህበር አባላቱን፣ ጋጤጠኞችን፣ ፊልም ቀራጮችን ይዞ ወደ ደቡብ ዞን አቅንቶ በተለይ የሃመር ብሄረሰብን አኗኗር ለማየት ጎዞዎን ከአዲስ አበባ ጀምሮ የቡስካ ተራራ በስተጀርባን አይቶ ተመልሶአል።

የደቡብ ኦሞ ዞን ልጃገረዶችምስል UN Photo/Rick Bajornas

ማህበሩ ይህን ጎዞ ለማድረግ የተነሳዉ ደራስያን በሚጽፉትን ስነ-ሰባዊ ልቦለድ በማንበብ ደራሲዉ ምን ያህል ከህብረተሰቡ እዉነታ ጋር የተቀራረበ ድርሰት ጽፎአል ስነ፧ ጽሁፉ ዉስጥ የተጠቀሱት ቦታዎች እና ስሞች ምን ያህል ቅርርብ አላቸዉ የሚለዉን ጥያቄ ለመመለስ እና ለመገምገም ነበር። ማህበሩ ይህን አይነቱን ጎዞ ባለፈዉ አመት ያደረገ ሲሆን የጎዞዉ መነሻ ፍቅር እስከመቃብር የተሰኘን የስነ-ሰብአዊ ልቦለድ በማንገብ ሲሆን፣ ዘንድሮ ማህበሩ ወደ ሃመር ብሄረሰብ ያደረገዉ ከደራሲ ፍቅረ ማርቆስ ደስታ የተጻፈዉን ከቡስካ በስተጀርባ ድንግል ዉበት የተሰኘዉን ስነ-ሰብአዊ ልቦለድ በማንገብ ነበር። ይህንኑ ጎዞ በማስመልከት የደራስያን ማህበር ምክትል ሊቀመንበር አቶ ደረጀ ገብሪ ጋር ተወያይተን ነበር ያድምጡ

አዜብ ታደሰ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW