1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ወደ ብሔራዊ ባንክ የሚገባዉ የወርቅ መጠን ቀነሰ

ዓርብ፣ ግንቦት 11 2015

በጋምቤላ እና ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ወደ ብሔራዊ ባንክ የሚገባው የወርቅ መጠን ዘንድሮ በከፍተኛ መጠን መቀነሱ ተነገረ። በክልሉ የምመረት ወርቅ በህገ ወጥ አዘዋዋሪዎች ከሀገር ውጭ በሱዳን በኩል ይሸጣል የሚል ቅሬታም ሲቀርብ ቆይቷል፡፡

Landverpachtung an ausländische Investoren in Äthiopien Flash-Galerie
ምስል DW

«ወርቅ በህገ ወጥ አዘዋዋሪዎች ከሀገር ውጭ በሱዳን በኩል ይሸጣል የሚል ቅሬታ አለ»

This browser does not support the audio element.

በጋምቤላ እና ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ወደ ብሔራዊ ባንክ የሚገባው የወርቅ መጠን ዘንድሮ በከፍተኛ መጠን መቀነሱ ተነገረ። በክልሉ የምመረት ወርቅ በህገ ወጥ አዘዋዋሪዎች ከሀገር ውጭ በሱዳን በኩል  ይሸጣል የሚል ቅሬታም ሲቀርብ ቆይቷል፡፡

በጋምቤላ እና ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ወደ ብሔራዊ ባንክ የሚገባው የወርቅ መጠን ዘንድሮ በከፍተኛ መጠን ቀንሷል፡፡ ባለፈው ዓመት  ከነበረው ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር በጋምቤላ ክልል የ9 ኩንታል ያህል ልዩነት ያለው ሲሆን በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ደግሞ ከ1ሺ 4 መቶ ኪ.ግ ያህል ቅናሽ አሳይቷል፡፡ በክልሎች ለምርቱ መቀነስ የህገ ወጥ  አዘዋዋሪዎችና የዶላር ዋጋ እንደምክንያት የተጠቀሱ ሲሆን በልዩ ሁኔታ ግብረ ሀይል ተቋቋሙ ክትትል መደረገ ከጀመረ መጋቢት ወር ወዲህ ደግሞ የ12 ኪ.ግ ያህል መሻሻል መታየቱ ተገልጸዋል፡፡ 

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል በ2014 ዓ.ም 2300 ኪ.ግ ወርቅ ወደ ብሔራዊ ባንክ መግባቱን ከክልሉ የማዕድን ሀብት ልማት ቢሮ የተገኘ መረጃ ያስረዳል፡፡ የክልሉ የማዕድን ሀብት ልማት ቢሮ  ኃላፊ አቶ ካሚል ሀሚድ ዘንድሮ እስከ ሚያዚያ ወር 4 ኩንታል  በክልል ደረጃ ወደ ብሔራዊ ባንክ መግባቱን ተናግረዋል፡፡ ከ2014 ዓ.ም ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር ከ10 ኩንታል በላይ ልዩነት እንዳለው ገልጸዋል፡፡ በአምራቾችና አዘዋዋሪዎች ላይ ብርቱ ቁጥጥር ባለመደረጉ የተፈጠረ ክፈተት እና  ለወርቅ ቁፋሮ ከውጪ የገቡ የስራ መሳሪዎች ዋጋ መጨመር ለምርቱ መቀነስ ምክንያቶች እንደሆኑ አመልክተዋል፡፡

ጋምቤላምስል Alemenw Mekonen/DW

በክልሉ የምመረት ወርቅ በህገ ወጥ አዘዋዋሪዎች ከሀገር ውጭ በሱዳን በኩል  ይሸጣል የሚል ቅሬታም ሲቀርብ ቆይቷል፡፡ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የወርቅ ምርትን ለመቆጣጠር በተቋቋመ ግብረ ሀይል በኩል በተደረገው ክትትል በክልሉ በመጋቢት ወር የ12 ኪ.ግ ዕድገት ማሳየቱን እንዲሁም በሚያዚያ ወር የ15 ኪ.ግ ጭማሪ መታየቱን ተናግረዋል፡፡

በጋምቤላ ክልልም በወርቅ ምርት ስራ ላይ የተሰማሩ በርካታ ሰዎች ቢኖሩም ወደ ብሔራዊ ባንክ የሚገባው የወርቅ መጠን ከባለፈው ዓመት ጋር ሲነጻጸር ከፍተኛ ቅናሽ አሳይቷል፡፡ በክልሉ የውጭ ሀገር ዜጎች ጭምር ከዚህ ቀደም በህገ ወጥ ወርቅ ዝውውር ላይ ተሰማርቶ የነበሩ እና በቁጥጥር ስር የዋሉ የቻይና ዜጎች እንዳሉ ተገልጸዋል፡፡

የጋምቤላ ክልል የማዕድን ቢሮ ኃላፊ አክዋታ ቻም ለዲዳቢሊው እንደተናገሩት በክልሉ 146 ኪ.ግ ወርቅ እስከ ባለፈው ወር ሚያዚያ/2015 ዓ.ም ወደ ብሔራዊ ባንክ መግባቱን   አመልክተዋል፡፡ ከባለፈው ዓመት ጋር ሲነጻጸርም ወደ 900 ኪ.ግ ያህል ልዩነት እንዳለው አብራርተዋል፡፡ ህገ ወጥ ወርቅ አዘዋዋሪዎችን ለመቆጣጠር ምርቱ የሚገኝባቸው ቦታዎቸ ተለይተው የየአካባቢው አስተዳደሮችን ከአምራቾች ጋር በማጠመር እንዲሰራ መደረጉን ገልጸዋል፡፡

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል እና ጋምቤላ ክልል ከ1200 በላይ ባለሀብቶች በማዕድን ዘርፍ ጨምሮ በተለያዩ ኢንቨስትመንት ስራ ላይ ተሰማርቶ እንደሚገኙ ከሁለቱም ተቋማት የተገኘ መረጃ ያመለክታል፡፡ የወርቅ ምርት ለማሻሻል እና የአምራችን ለመደገፍ ሲባል ብሔራዊ ባንክ ድጎማና ለአቅርቢዎች  ጭማሪ ማድረጉን  ባንኩ ይፋ አድርጓል፡፡ 

ነጋሳ ደሳለኝ

አዜብ ታደሰ

ኂሩት መለሰ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW