ወደ ትግራይ እንዲጓዙ ፈቃድ አገኙ የተባሉት ሸቀጥ የጫኑ ተሽከርካሪዎች ጉዳይ
ማክሰኞ፣ ግንቦት 26 2017
ወደ ትግራይ እንዲጓዙ ፈቃድ አገኙ የተባሉት ሸቀጥ የጫኑ ተሽከርካሪዎች ጉዳይ
ለሳምንት ወደ ትግራይ እንዳይጓዙ ተከልክለው የነበሩ ሸቀጥ የጫኑ ተሽከርካሪዎች ተደረሰ ከተባለ መግባባት በኃላ ጉዟቸውን እንዲቀጥሉ ተፈቅዷል። ይሁንና በየግዜው የሚጣሉ ክልከላዎች በሕብረተሰቡ ላይ ኢኮኖሚያዊ እና ማሕበራዊ ጫናዎች እየፈጠሩ መሆኑ አስተያየት ሰጪዎች ይገልፃሉ።
ለሳምንት ከቆየ ወደ ትግራይ የሚጓዙ ሸቀጦች ክልከላ በኃላ፥ የክልሉ ግዚያዊ አስተዳደር ፕሬዝደንት ጀነራል ታደሰ ወረደ ከፌደራል መንግስት ባለስልጣናት ጋር ካደረጉት ውይይት በኃላ ክልከላው እንዲነሳ መግባባት ላይ መደረሱ የትግራይ ግዚያዊ አስተዳደር ፕሬዝደንት ፅሕፈት ቤት ባለፈው ሳምንት መጨረሻ አስታውቋል። የትግራይ ግዚያዊ አስተዳደር ፕሬዝደንት ጀነራል ታደሰ ወረደ፥ ከፌደራል ፖሊስ ኮምሽን ጀነራል ደመላሽ ገብረሚካኤል ጋር ቅዳሜ ግንቦት 23 ቀን 2017 ዓመተምህረት በዚሁ ጉዳይ መወያየታቸውን የተገለፀ ሲሆን፥ ሸቀጦች የጫኑ መኪኖች ወደ ትግራይ እንዳያልፉ የተከለከሉት፥ ሸቀጡ ድንበር ተሻግሮ በኮንትሮባንድ እየወጣ ነው በሚል ምክንያት ነው ተብሎ የተባለ ሲሆን፥ የዚህ እውነት እንዲጣራ፣ የማስተካከያ እና ክትትል ስርዓት እንዲኖር፣ ይህ እየሆነ እያለ የተጣለው ክልከላ እንዲነሳ ስምምነት ላይ መደረሱ ተጠቁሟል። ከሹፌረች እና ነጋዴዎች እንደሰማነው ከዚሁ መግባባት በኃላ በተለይም ከእሁድ ጀምሮ ተከልክሎ የነበረ የተለያዩ ሸቀጦች የጫኑ መኪኖች ወደ ትግራይ እንዲጓዙ ተፈቅዷል፥ ትላንት እና ዛሬ ማክሰኞ በርካታ መኪኖች ወደ መቐለ ገብተዋል። የመቐለ ፍርድቤቶች የስራ ማቆም አድማ
ይሁንና በተለያዩ ምክንያቶች በየግዜው ወደ ትግራይ ሸቀጥ እንዳይገባ መከልከል፣ የነዳጅ አቅርቦ መቀነስ እና ማቋረጥ እንዲሁም ሌሎች እርምጃዎች በማሕበረሰቡ ላይ ከፍተኛ ጫና እያሳደሩ መሆኑ ይገለፃል። ያነጋገርናቸው የትግራይ ንግድና ዘርፍ ማሕበራት ቦርድ አመራር ዲበኩሉ አለም ብርሃነ በየግዜው የሚጣሉ ክልከላዎይ የዋጋ ንረት እንዲሁም ሌሎች በርካታ ኢኮኖሚያዊ ችግርች እያስከተሉ ነው ይላሉ።አንድ ለአንድ- የሕወሓት ከፖለቲካ ፓርቲነት መሰረዝ እና ቀጣይ የኢትዮጵያ ፖለቲካ
በቅርቡ ብቻ የትግራይ ግዚያዊ አስተዳደር የተለያዩ መስርያቤቶች በነዳጅ ክልከላ፣ ሸቀጦች የጫኑ መኪኖች እንዳያልፉ እግድ፣ የውጭ ሀገር ቱሪስቶች የጉዞ ክልከላ እየተደረገ ነው የሚል ቅሬታ የያዘ ደብዳቤ ለፌደራል መንግስት የሚመለከታቸው አካላት ፅፈዋል። እነዚህ ሁኔታዎች ከኢኮኖሚያዊ በዘለለ ማሕበራዊ ችግሮችም እያስከተሉ ስለመሆናቸው በነዋሪዎች ይገለፃል።
በተለይም ከሸቀጦይ ጋር በተገናኘ የፌደራሉ መንግስት በኮንትሮባንድ እየወጣ ነው ብሎ የሚገነዘብ ከሆነ ድንበር መጠበቅ እንጂ መንገድ ወግቶ ሕብረተሰብ ወደ ችግር ማስገባት የለበትም ሲሉ ያነጋገርናቸው አካላት ጨምረው ይገልፃሉ።
ሚሊዮን ኃይለሥላሴ
አዜብ ታደሰ
ሸዋዬ ለገሠ