ወደ አፋር ክልል የተስፋፋው የትግራይ ጦርነት
ረቡዕ፣ ሐምሌ 14 2013
ማስታወቂያ
ስምንት ወራት የቆየውና አሁንም ያለዕልባት የቀጠለው የትግራዩ ጦርነት ሰሞኑን በአፋር ክልል በኩል ተስፋፍቶ 54 ሺህ ሰዎች ገደማ ማፈናቀሉን የአፋር ክልል አደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ኤጄንሲ አስታወቀ። የኤጄንሲው ኃላፊ አቶ መሃመድ ሁሴን ለዶይቼ ቬለ እንደተናገሩት በአፋር ዞን አራት ውስጥ በሚገኙ አምስት ወረዳዎች ህወሃት ደርሷል ባሉት ጥቃት በተለይም በሁለቱ ክልሎች አዋሳኝ 8 ወረዳዎች ግማሽ ሚሊየን ያህል ህዝብን ድጋፍ ሊያስፈልገው እንደሚችል አረጋግጠዋል። በጦርነቱ ተጎድተው በየቦታው ለወደቁና ለተፈናቀሉ ዜጎች አስቸኳይ ሰብዓዊ ድጋፍ ለማድረግ የሚደረገውን ጥረት አሁንም በቀጠለው ጦርነት መደናቀፉን ኃላፊው አክለዋል።
ስዩም ጌቱ
ሸዋዬ ለገሠ
ኂሩት መለሰ