1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ወደ ጋምቤላ የሚሰደዱ ደቡብ ሱዳናዉያን ቁጥር እየጨመረ ነዉ ተባለ

ማክሰኞ፣ ጥቅምት 13 2016

ከደቡብ ሱዳን ግጭት በመሸሽ ወደ 9ሺ የሚጠጉ ሰዎች ወደ ጋምቤላ ክልል መሻገራቸውን የስደተኞችና ተመላሾች አገልግሎት አስታወቀ፡፡ ስደተኞቹ በጋምቤላ ክልል ፒኝዶ በተባለ ቦታ ተጠልለው እንደሚገኙ አገልግሎቱ አስታዉቋል፡፡ ወደ ኢትዮጵያ የሚሻገሩ የደቡብ ሱዳን ስደተኞች ቁጥር ሊጨምር እንደሚችልም ተገልጸዋል፡፡

ጋምቤላ ከተማ
ጋምቤላ ከተማ ምስል Privat

በጋምቤላ ክልል ብቻ ከ 3 መቶ ሺ በላይ ስደተኞች በተለያዩ መጠለያ ጣቢያዎች ይገኛሉ

This browser does not support the audio element.

ወደ ጋምቤላ የሚሰደዱ  ደቡብ ሱዳናዉያን ቁጥር እየጨመረ ነዉ ተባለ

ከደቡብ ሱዳን ፖቻላ በተባለ ቦታ የተፈጠረው ግጭት በመሸሽ ወደ 9ሺ የሚጠጉ ሰዎች ወደ ጋምቤላ ክልል መሻገራቸውን የስደተኞችና ተመላሾች አገልግሎት አስታውቋል፡፡ እነዚህ ጥገኝነት ጠያቂዎች በጋምቤላ ክልል ፒኝዶ በተባለ ቦታ ተጠልለው እንደሚገኙ የስደትና ተመላሾች አገልግሎት የኮሙኒኬሽን እና የውጭ ግንኙነት ኃላፊ አቶ በአካል ንጉሴ ለዶይቼቨለ ተናግረዋል፡፡ ከሦስት  ቀን በፊት 8554 ስደተኞች መመዝገባቸውን ተናግረዋል፡፡ ወደ ኢትዮጵያ የሚሻገሩ የደቡብ ሱዳን ስደተኞች ቁጥር ሊጨምር እንደሚችልም ተገልጸዋል፡፡ በደቡብ ሱዳን ከመስከረም አጋምሽ አንስቶ ጋምቤላን በሚዋስነው የደቡብ ሱዳኗ ፖቻላ በተባለ ቦታ በሁለት ማህበረሰብ  መካከል በተፈጠረው አለመግባባት  ከፍተኛ መውደመት መድረሱ ሲነገር ቆይተዋል፡፡ኢትዮጵያ ውስጥ ከተጠለሉ ስደተኞች 40 ያክል ሞቱ

በሱዳን ግጭት ከተቀሰቀሰው ወዲህ ከ85ሺ በላይ የሚሆኑት  ዜጎች በተለያዩ አቅጣጫዎች ወደ ኢትዮጵያ መግባታቸውን የመንግስታቱ ድርጅት መረጃ ያመለክታል፡፡  ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ደግሞ በደቡብ ሱዳን ፖቻላ በተባለ አካባቢ በተከሰተው ግጭት በሺዎች የሚቆጠሩ የደቡብ ሱዳን ዜጎች ወደ ጋምቤላ ክልል መሻገራቸውን የስደተኞችና ተመላሾች አገልግሎት አመልክተዋል፡፡ የስደተኞችና ተመላሾች አገልግሎት የኮሙኒኬሽን እና የውጭ ግንኙት ኃላፊ አቶ በአካል ንጉሴ ለዶቸቬለ እንደተናገሩት ወደ 9 ሺ የሚጠጉ  ጥገኝነት ጠያቂ የደቡብ ሱዳን ስደተኞች በጋምቤላ ክልል ተጠልለዋል፡፡ በክልሉ ፒኝዶ በተባለ ስፋራ በተዘጋጀው መጠለያ እንደሚገኙ ኃላፊው ተናግረዋል፡፡በጋምቤላ የደረሰው ጥቃት የአራት ሰዎች ሕይወት ቀጠፈ

የጋምቤላ ክልል ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፌት ቤት ኃለፊ አቶ ኡጁሉ ጊሎ በበኩላቸው  በደቡብ ሱዳን ፖቻላ አካባቢ የተከሰተውን  ግጭት በመሸሽ  በርካታ ሰዎች ወደ ክልሉ እየተሻገሩ እንደሚገኙ ገልጸዋል፡፡ ስደተኞች ወደ ጋምቤላ መሻገር ከጀመሩ ሁለት ሳምንታት እንደተቆጠሩ የገለጹት ኃላፊው በአካባቢው በሁለት ሰዎች መካከል (በአንድ ሲቪል እና ጸጥታ ሀይል) መካከል በተፈጠረው አለመግባባት ግጭቱ በመስፋፋት በሺዎች ለሚቆጠሩ ሰዎች መሰደድ ምክንያት መሆኑን ተናግረዋል፡፡ የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች ከስደትና ተመላሾች አገልግሎት ጋር በመሆን ስደተኞቹ የሚገኙበት ጎግ ወረዳ  በመገኘት ድጋፍ ለማድረግ እንዲያመች የስደተኞች ቁጥር መለየታቸውን ገልጸዋል፡፡ጋምቤላ ውስጥ የሙርሌ ጎሳ ታጣቂዎች ጥቃት

የተባበሩት መንግስታት የስደተኞች ጉዳይ ከፍተኛ ኮሚሽን ከዚህ ቀደም በማህበራዊ መገናኛ ዜደው ጋምቤላ ውስጥ የሙርሌ ጎሳ ታጣቂዎች እንደገለጸው በጋምቤላ ክልል በፒኝዶ ስደተኞች መጠለያ ጣቢያ ለገቡ  የደቡብ ሱዳን ስደተኞች ከአጋር አካላት ጋር በመሆን መሰረታዊ የሆኑ ድጋፎችን ለማቅረብ እየተንቀሳቀሰ እንደሚገኝ አመልክተዋል፡፡  እንደ ኮሚሽኑ መረጃ በጋምቤላ ክልል ከ 3 መቶ ሺ በላይ ስደተኞች በተለያዩ መጠለያ ጣቢያዎች ውስጥ ይኖራሉ፡፡

ነጋሳ ደሳለኝ

አዜብ ታደሰ

ነጋሽ መሐመድ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW