1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ወጣቱና የታሪካዊ ቦታዎች ጉብኝት

ዓርብ፣ ጥቅምት 1 2006

የአንድን ወይንም የራስን ሀገር፣ ቤተ መዘክር፣ ሀውልት፣ የህንፃም ሆነ ሌሎች ቅሪቶች እና የመሳሰሉትን በመጎብኘት ስለ ሀገር ታሪካዊ ቦታዎች እና ታሪክ ማወቅ ይቻላል። ለመሆኑ ወጣቱ ስለ ሀገሩ ታሪካዊ ቦታዎች ምን ያህል ያውቃል? ምን ያህልስ ማወቅ ይፈልጋል?

An Orthodox Christian walks to enter one of 11 monolithic rock-cut churches, ahead of Orthodox Easter in Lalibela May 4, 2013. REUTERS/ Goran Tomasevic (ETHIOPIA - Tags: RELIGION SOCIETY)
ምስል Reuters/Goran Tomasevic

ቤተልሔም ተሻገር እና ስያኔ አንለይ ሁለቱም አንድ የጋራ ዓላማ አላቸው። በተቻላቸው መጠን ስለ ሀገራቸው ታሪክ ማወቅና ታሪካዊ ቦታዎችን መጎብኘት ይፈልጋሉ። ፍላጎታቸውንም ዕውን በማድረግ ላይ ናቸው። አንዷ የሥራዋ ሁኔታ ይበልጥ ስላመቻቸላት ሌላኛዋ ደግሞ ሆን ብላ ጉዞዎችን በማቀድ እና በመተግበር ላይ ትገኛለች።

የሎሲ( ድንቅነሽ) አፅምምስል Getty Images

የቤተልሔም ሥራ ከቢሮ አያስወጣም። የ28 ዓመቷ ቤተልሄም በተመረቀችበት የሂሳብ አያያዝ ሙያ ተሰማርታ አዲስ አበባ ውስጥ ትሰራለች። በተቻላት መጠን ግን የሀገሯን ታሪካዊ ቦታዎች ለመጎብኘት ዕረፍት ትወስዳለች። ይህም አስፈላጊ ነው ብላ ታምንበታለች። እንደ ጀርመን ባሉ አገሮች በተለይ በትምህርት ቤት ወቅት በቡድን በመሆን ታሪካዊ ቦታዎችን መጎብኘት በፍላጎት ብቻ ሳይሆን በግዳጅ የሚሰጥ የትምህርት አካል ነው? ይህ በኢትዮጵያ እንደ ትምህርት ቤቱ እና አስተማሪው ጥረት ይለያይ እንጂ በቡድን ታሪካዊ ቦታዎች መጎብኘት አለ። ቤተልሔም ትምህርት ቤት ሳለች ቤተ መዘክሮች መጎብኘቷን ታስታውሳለች። አብዛኛውን ጊዜ ለተማሪዎች ጊዜ ነፃ መሆናቸው ወይም ለመጎብኘት መጠነኛ ክፍያ ብቻ መጠየቃቸው ተማሪዎችን ያበረታታል ትላለች ቤተልሔም።

የፋሲል ግንብ ፤ጎንደርምስል DW/Azeb Tadesse Hahn

ሌላኛዋ ወጣት ስያኔ አንለይ ፤ በአዲስ አበባ ዮኒቨርስቲ የ2ኛ ድህረ ምረቃ ተማሪ ናት። በአሁኑ ሰዓት መንግስታዊ ባልሆነ ድርጅት ውስጥ በትርፍ ጊዜዋ የሥራ ልምምድ ታደርጋለች። ሥራዋም ኢትዮጵያን እየዞረች ከሀገሯ ታሪካዊ ቦታዋች ጋ እንድትተዋወቅ መንገድ ፈጥሮላታል። ወጣቷ በምታገለግልበት መንግስታዊ ያልሆነ ድርጅት ውስጥ የሥራ ድርሻዋ በትምህርት ላይ ያተኮረ ነው። ወደ ተለያዩ ከተሞች ስትሄድ ት/ቤቶችን መጎብኘት ከዋንኛ ሥራዋቿ አንዱ ነው። ስያኔ እንዴት አድርጋ ሥራ እና የሀገር ጉብኝቷን እንደምታዛምድ አጫውታናለች።

ሁለቱም ወጣቶች የሀገር ታሪካዊ ቦታዎችን ለማየት ስለሚያደርጉት ጥረት ነግረውናል። ከድምፅ ዘገባው ያገኙታል።

ልደት አበበ

ሸዋዬ ለገሰ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW