ወጣት ባለሙያዎች በኢትዮጵያ ቴአትር ውስጥ
ሐሙስ፣ ነሐሴ 8 2006ማስታወቂያ
የቴአትር ባለሙያዎችና መምህራን በበኩላቸው ችግሮቹ ቢኖሩም ወጣቶች በግል ተቋማት ሥራዎቻቸዉን በማቅረብና ሌሎች የመገናኛ ብዙሃንን በመጠቀም እውቀታቸውን ሊሳድጉ ራሳቸውን ተጠቃሚ ሊያደርጉ ይገባል ባይ ናቸው። ቲአትርን በከፍተኛ የትምህርት ተቋማት በማስተማር ቀዳሚው በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የቴአትር ጥበባት ትምህርት ክፍል ነዉ።
ቀድሞ በትምህርት ክፍል ደረጃ የተቋቋመው የዛሬው የቴአትርጥበባት ትምህርት ቤት ባለፉት 35 ዓመታት ሙያውን ሲያስተምር ቆይቷል። ዛሬ ግን የወሎና የመቀሌ ዩኒቨርሲቲዎችም ማስተማር ጀምረዋል። የጅማ ዩኒቨርሲቲም ተመሳሳይ የትምህርት ዘርፍ ለመጀመርበዝግጅት ላይ ነው። የቲአትር ትምህርትን የተማሩ በዘርፉ መሥራት የሚፈልጉ ሰዎች ቁጥር እየጨመረ ቢመጣም ገበያው ግን እንዲህ ቀላል አይደለም። አንዱአለም ደጀኔ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በቴአትርን የመጀመሪያ ዲግሪዉን የያዘ ወጣት ነው። አንዱአለም ቴአትርን ቢማርም በተማረዉ ሙያ ለመሠማራት ቀላል እንዳልሆነ ይናገራል። ዝርዝሩን ከድምጽ ዘገባዉ ያድምጡ።
እሸቴ በቀለ
ተክሌ የኋላ