1. ወደ ይዘቱ እለፍ
  2. ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ

ወጣት አፍሪቃውያን ከዘንድሮው የዓየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ ምን ይጠብቃሉ?

ማክሰኞ፣ ኅዳር 2 2018

በብራዚል ትናንት የተጀመረው 30ኛው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ (ኮፕ 30)እስከ ህዳር 12 ቀን 2018 ዓ.ም ይዘልቃል። በዚህ የጉባኤ ተሳታፊ የሆኑ አፍሪቃውያን ወጣቶች፤ ለአየር ንብረት ለውጥ ዝቅተኛ ድርሻ ያላት ነገር ግን ዋነኛ የችግሩ ተጠቂ ለሆነችው አፍሪቃ፤ መፍትሄ የሚያመጡ ውሳኔዎችን ይጠብቃሉ።

Brasilien Belém | UN-Klimakonferenz COP30
ምስል፦ Tainã Mansani/DW

ወጣት አፍሪቃውያን ከዘንድሮው የዓየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ ምን ይጠብቃሉ?

This browser does not support the audio element.

 
30ኛው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ(ኮፕ 30) ትናንት ተጀምሯል። ቤለም-በብራዚል ፣የተጀመረው የዘንድሮው ጉባኤ  ዋና መርሕ “የአየር ንብረት እርምጃ እና ትግበራ” የሚል ነዉ። እስከ ህዳር 12 ቀን 2018 ዓ.ም በሚዘልቀው በዚህ ጉባኤ፤ለአየር ንብረት ለውጥ ዝቅተኛ ድርሻ  ያላት ነገር ግን ዋነኛ የችግሩ ገፈት ቀማሽ የሆነችው አፍሪቃ፤ በአየር ንብረት ለውጥ ምክንያት ለገጠማት ፈተና መፍትሄ የሚያመጡ ውሳኔዎችን ትጠብቃለች።ይላሉ ዶቼ ቤለ ያነጋገራቸው የጉባኤ ተሳታፊ አፍሪቃውያን ወጣቶች።

ኬንያዊቷ አኒታ ሶይና ከ100,000 በላይ የኢንስታግራም ተከታዮች ያሏት - በአካባቢ ጥበቃ ተሟጋች ነች።የኬንያ የማሳኢ ማህበረሰብ አባል የሆነው የ26 አመቷ ወጣት ለተባበሩት መንግስታት የአየር ንብረት ጉባኤ COP30 በሰሜን ብራዚል በምትገኘው ቤሌም ከተማ ተገኝታለች።ሶይና በሀገሯ ኬንያ የአየር ንብረት ለውጥ  የደን ጭፍጨፋ፣ ድርቅን፣ ረሃብን እና የውሃ እጥረትን እንዴት እንደሚያባብስ አይታለች።ለእሷ፣ COP30 ልዩ ትርጉም አለው።«ይህ ክስተት ለግሎባል ደቡብ ትልቅ እድሎች አንዱ ይሆናል ብዬ አስባለሁ። የCOP ፕሬዝዳንትን ወይም የብራዚልን ፕሬዝዳንት ስናዳምጥ በእውነት ተስፋ ሰጭ ነገር እየተፈጠረ እንደሆነ ሊሰማህ ይችላል።» ብላለች። የሶይና ብሩህ ተስፋ ግን ጥንቃቄ የተሞላበት ነው።ምክንያቱም  ከዚህ በፊት ብዙ ቃል ገብተናል፣ እና በመጨረሻ ቀውሱ እየተባባሰ እንደመጣ ቀጥሏል።ትላለች። ለዚህም  የፖለቲካ ፈቃደኝነት ትልቅ እንቅፋት ነው ትላለች።«በአፍሪካ እና በአለም አቀፍ ደረጃም እንደማስበው ትልቁ መሰናክል  የፖለቲካ ፈቃደኝነት ማጣት ነው። የፖለቲካ ፈቃደኝነት ማጣት አብዛኞቹ ቃል ኪዳኖች የማይከበሩበት ምክንያት ነው።» ስስትል ገልፃለች።

አኒታ ሶይና ፤የኬንያ የአየር ንብረት ለውጥ ግንዛቤን ለማሳደግ፣ የዛፍ ተከላ እና የጽዳት ዘመቻዎችን የሚያደጅ ቡድን መስርታለች።ምስል፦ Tainã Mansani/DW

የፖለቲካ ቁርጠኝነት እና ማኅበረሰብን ማሳተፍ 

ኡጋንዳዊቷ ሂልዳ ናካቡዬ ታዋቂየአየር ንብረት ተሟጋችእና የ«ፍራይደይ ፎር ፊውቸር»የተባለው ንቅናቄ  አባል ነች።፣የአሁኑን ጉባኤ ጨምሮ ለአምስተኛ ጌዜ ተገኝታለች። የዘንድርው  የተለዬ ነው ትላለች።«ለእኔ COP30 የፓሪስ ስምምነት 10 ዓመታ የሞላበት  ልዩ ጊዜ ነው"» ሄልዳ አያይዛም፤«ከአፍሪቃዊ የመጣሁ ወጣት ሴት  እንደመሆኔ፤ እዚህ የመጣሁት ድምፄን ለማሰማት እና እነሱ ባልፈጠሩት ቀውስ የተጎዱትን ማህበረሰቦች ለመወከል ነው።» ብላለች። ኬንያዊቷ የአካባቢ ጥበቃ ተሟጋች ሶይና በበኩሏ ማኅበረሰብን ማሳተፍ አስፈላጊ መሆኑን ገልፃለች።«እኛ ማድረግ ያለብን ከሁሉ የተሻለው ስልት ማህበረሰቦችን ማሳተፍ ነው ብዬ አስባለሁ። አስቸጋሪ ሊሆን ይችላል። ነገር ግን የአየር ንብረት ለውጥን ብቻ ሳይሆን በአጠቃላይ የማህበረሰብ ልማትን ለማከናወን በጣም ጥሩው መንገድ ነው።.» ስትል ገልፃለች።

ሂልዳ ናካቡዬ፤ በኡጋንዳ ታዋቂ የአየር ንብረት ተሟጋችእና የ«ፍራይደይ ፎር ፊውቸር»የተባለው ንቅናቄ  አባል ።ምስል፦ Tainã Mansani/DW

ግልጽነት እና የተግባር ጥያቄዎች

ዛምቢያን በመወከል የግራፍት ሞኒተር ትራንስፓረንሲ ኢንተርናሽናል ዋና ዳይሬክተር ሞሪስ ኬ ኒያምቤ ለ COP30 ወደ አማዞን ተጉዟል። የዘንድሮው የመሪዎች ጉባኤ አዲስ ቃል ኪዳኖችን ብቻ ሳይሆን ተጠያቂነትን የሚያረጋግጡ አሰራሮችን እንደሚያተኩር ተስፋ አድርጓል።«ስለ አየር ንብረት ፋይናንስ ወይም ስለካርቦን ንግድ ብንነጋገርም፤ በእነዚያ ሁሉ ውይይቶች ውስጥ ግልጽነት [እና] ተጠያቂነትን ማካተት አስፈላጊ ይመስለኛል።» በማለት ለDW ተናግሯል።

የአፍሪካ ወጣቶች በ COP30 ላይ እውነተኛ የአየር ንብረት ቁርጠኝነትእና በውሳኔ አሰጣጥ ላይ እውነተኛ ተሳትፎን ለማየት ተስፋ እንዳላቸው ተናግረዋል ።እናም ወጣቶቹ  በአንድ  ድምፅ አንድ መልዕክት አላቸው።የአየር ንብረት ፍትህ ከንግግር  ወጥቶ በተግባር መተርጎም አለበት።
ዓለም አቀፉን ቀውስ በጋራ ለመጋፈጥ ከአማዞን እስከ አፍሪካ ያሉ ግሎባል ሳውዝ ወይም የዓለም ደቡብ ክፍል ያሉ ሀገራት መካከል ጥልቅ ትብብር እንዲደረግም ጥሪ አቅርበዋል።
እነዚህ ወጣት የአየር ንብረት አንቂዎች በበሌም መገኘታቸውን ከተምሳሌታዊነት ባለፈ የተግባር ጥያቄ አድርገው ይቆጥሩታል።  

ፀሀይ ጫኔ
ታምራት ዲንሳ

ቀጣዩን ክፍል እለፈው ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ
ቀጣዩን ክፍል እለፈው የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል እለፈው ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW