1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ዉይይት፤ ኢትዮጵያ፣ድርቅና ረሐብ የተጣባት ሐገር

እሑድ፣ የካቲት 26 2015

ኢትዮጵያ ዉስጥ መንግስታት ቢፈራረቁም የድርቅና የረሐቡ ድግግሞሽ ከ10 ወደ አምስት፣ ከአምስት ወደ 3 ዓመታት እየፈጠነ፣ በቅርቡ ደግሞ ከዓመት ዓመት እየቀጠለ፣ለረሐብ የሚጋለጠዉ ሕዝብ ብዛትም በ20 ሚሊዮኖች ይቆጠር ይዟል።

Äthiopien I Dürre in Amarom
ምስል Shewangizaw Wegayehu/DW

ዝናብ የለም።ከብት አልቋል።ምግብ የለም።ኢትዮጵያ

This browser does not support the audio element.

ኢትዮጵያ ከ1960ዎቹ ጀምሮ እንደኖረችበት አምናና ዘንድሮም ጦርነት፣ግጭትና ዉዝግብ አልበቃ ያላት ይመስል በረሐብና ድርቅ የዓለም ርዕስ ሆናለች።በ1965 እና 66 የቀድሞዉን የንጉሰ ነገስት አፄ ኃይለስላሴን ዙፋናዊ አገዛዝ ለማስወገድ ተቃዋሚዎቻቸዉ እንደዋና መሳሪያ ከተጠቀሙባዎቸዉ ችግሮች አንዱ በመቶ ሺሕ የሚቆጠር ሕዝብ በረሐብ መሰቃየቱ ነበር።በ1977ና 78 ኢትዮጵያን በመታዉ ድርቅ 5 ሚሊዮን ያክል ሕዝብ ለረሐብ መጋለጡ ዓለምን ጉድ አሰኝቶ፣ የደርግን መንግስት ለማሳጣት ዋና መሳሪያ ነበር።

ኢትዮጵያ ዉስጥ መንግስታት ቢፈራረቁም የድርቅና የረሐቡ ድግግሞሽ ከ10 ወደ አምስት፣ ከአምስት ወደ 3 ዓመታት እየፈጠነ፣ በቅርቡ ደግሞ ከዓመት ዓመት እየቀጠለ፣ለረሐብ የሚጋለጠዉ ሕዝብ ብዛትም በ20 ሚሊዮኖች ይቆጠር ይዟል።የተባበሩት መንግስታት ድርጅትን ጨምሮ የተለያዩ የርዳታ ድርጅቶች እንዳስታወቁት ባለፉት ተከታታይ አራት ዓመታት ዝናብ በመሳቱ ከ25 ሚሊዮን የሚበልጥ ኢትዮጵያዊ ለምግብ እጥረት ተጋልጧል።

ዉኃ የለም ከኮንሶ አካባቢ አንዱምስል Konso Development Association

በተለይ ኑሮዉን በከብት ርባታ ላይ ያደረገዉ ከ12 ሚሊዮን የሚበልጥ የቦረና፣ የጉጂ፣ የደቡብ ኦሞ ዞኖችና የሶማሌ ክልል ነዋሪ ረሐብ ከየቀየዉ እያፈናቀለዉ፣አለያም በያለበት እያሰቃየዉ ነዉ።ለሕፃናት መብት የሚሟገተዉ ሴቭ ዘ ችልድረን ባለፈዉ ጥር እንዳስታወቀዉ ኢትዮጵያ ዉስጥ ወደ አራት ሚሊዮን የሚጠጉ ሕፃናት በቂ ምግብ አያገኙም።የጀርመኑ ግብረ ሰናይ ድርጅት ቬልት ሑንገር ሒልፈ እንዳለዉ ደግሞ በተከታታይ በድርቅ በተመቱ እንደ ቦረና፣ሐመርና ኦጋዴንን በመሳሰሉ አካባቢዎች የሕዝቡ ዋና መተዳደሪያ የነበሩ ከ3.5 ሚሊዮን የሚበልጡ የቤት እንስሰዎች አልቀዋል።

ከብት አልቋል የጉጂ አካባቢምስል DW

 ዝናብ የለም።ምርት የለም።ከብት የለም።ምግብ የለም-ኢትዮጵያ።ለመሆኑ ሌላዉ ኢትዮጵያዊ ይኸ ሁሉ ወገኑ መፅዋቾችን ሲማፀን ምን እያለ ምንስ እያደረገ ይሆን? የብዙ ወንዞች መፍለቂያ፣ የለም አፈር ባለቤቲቱ ኢትዮጵያ ድርቅና ረሐብ እንደተጣባት፣አስከሬንና አፅም እያስቆጠረች ዘመናት የምታሰላዉ ለምንና እስከ መቼ ነዉ?

ነጋሽ መሐመድ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW