1. ወደ ይዘቱ እለፍ
  2. ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ

ዉይይት፤ የሱዳን ጦርነት ጥፋቱና መዘዙ

ነጋሽ መሐመድ
እሑድ፣ ሚያዝያ 22 2015

ባለፈዉ ሚያዚያ 7፣ 2015 በተጀመረዉ ዉጊያ ከ520 በላይ ሰዎች ተገድለዋል።4 ሺሕ 500 ቆስለዋል።አዉሮፕላን ማረፊያዎች፣የጦር ሠፈሮች፣የመንግስት መስሪያ ቤቶች፣ ሆስፒታሎች ሌሎችም ተቋማት ጋይተዋል።በመቶ ሺሕ የሚቆጠር ሕዝብ ወደ አጎራባች ሐገራት ተሰድዷል ወይም ተፈናቅሏል።መንግስታት በሺሕ የሚቆጠሩ ዜጎቻቸዉን ከሱዳን አስወጥተዋል።

Kombobild Abdul Fattah Al-Burhan und Mohamed Hamdan Dagalo
ምስል፦ Bandar Algaloud/Mahmoud Hjaj/AA/picture alliance

ዉይይት፤ ሱዳን ስልታዊነቷ፣ዉድመቷና አስጊነቷ

This browser does not support the audio element.

ጤና ይስጥልኝ እንደምን ዋላችሁ።ለዛሬዉ ዉይይታችን የሱዳን የርስ በርስ ጦርነት የሚያደርሰዉ ጥፋትና ተፅኖ የሚል ጥቅል ርዕስ ሰጥነዋል።

የሱዳን መከላከያ ኃይልና የሐገሪቱ ፈጥኖ ደራሽ ጦር የገጠሙት ዉጊያ ርዕሰ-ከተማ ኻርቱምን ጨምሮ የተለያዩ የሐገሪቱን ከተማና አካባቢዎች እያወደመ ነዉ።የጦርነቱ መነሻ የሱዳንን ወታደራዊ ሁንታ በዋናና በምክትልነት በሚመሩት በጄኔራል አብዱል ፈታሕ አል ቡርሐንና በጄኔራል መሐመድ ሐምዳን ዳጋሎ (ሐሚቲ) መካከል የተፈጠረ የስልጣን ሽኩቻ እንደሆነ በሰፊዉ ይነገራል።

ሁለቱ ጄኔራሎችና የሚመራቸዉ ኃይላት የፈጥኖ ደራሹ ጦር ከመደበኛዉ የፀጥታ ኃይል ጋር በሚዋሐድበት ጊዜ ላይ እንደዘበት የፈጠሩት ጠብ አለቅጥ መናሩ ሶስተኛዋን ሰፊ አፍሪቃዊት ሐገር እያወደመ፣ ምስራቅ አፍሪቃን፣መካከለኛዉ ምስራቅና መላዉ ዓለምን ግራ እያጋባ ነዉ።

የተለያዩ ዓለም አቀፍ ድርጅቶች እንዳስታወቁት ባለፈዉ ሚያዚያ 7፣ 2015 በተጀመረዉ ዉጊያ ከ520 በላይ ሰዎች ተገድለዋል።4 ሺሕ 500 ቆስለዋል።አዉሮፕላን ማረፊያዎች፣የጦር ሠፈሮች፣የመንግስት መስሪያ ቤቶች፣ ሆስፒታሎች ሌሎችም ተቋማት ጋይተዋል።በመቶ ሺሕ የሚቆጠር ሕዝብ ወደ አጎራባች ሐገራት ተሰድዷል ወይም ተፈናቅሏል።መንግስታት በሺሕ የሚቆጠሩ ዜጎቻቸዉን ከሱዳን አስወጥተዋል።

ከፊል ኻርቱም እየጋየች ምስል፦ AFP

ተፋላሚ ኃይላት ካለፈዉ ማክሰኞ ጀምሮ ረገብ ያደረጉትን ዉጊያ ጨርሶ እንዲያቆሙ ለማግባባት የሚደረገዉ ጥረትና ግፊት እንደቀጠለ ነዉ።ነገር ይኽን ዝግጅት እስካጠናቀርንበት እስካለፈዉ ሐሙስ ማታ ድረስ ከስምምነት ላይ አልደረሱም።

ሱዳን ለአፍሪቃ፣ ለአረብ፣ለእስያ ይሁን ለአዉሮጳ-አሜሪካ ሲበዛ ስልታዊ ሐገር ናት።የስልታዊነቷ ፋይዳ ስፋቷ፣ ከሊቢያ እስከ ማዕከላዊ አፍሪቃ ሪፐብሊክ፣ ከግብፅ እስከ ኢትዮጵያ፣ ከቻድ እስከ ኤርትራ እስከ ደቡብ ሱዳን ያሉ 7 ሐገራትንና ቀይ ባሕርን  ስለምታዋስን ብቻ አይደለም።የምታጎራብታቸዉ ሐገራት በሙሉ አንድም በአምባገነን መሪዎች የሚገዙ፣ሁለትም በግጭት፣ ጦርነትና በመፈንቅለ መንግስት የተመሰቃቀሉ ናቸዉ-።

የዓባይ ወንዝ ፖለቲካ ወደ ካይሮ ያጋድል ወደ አዲስ አበባ፣ የዋሽግተን-ብራስልስ ጥምረትና የቤጂንግ-ሞስኮዎች ሽኩቻ አፍሪቃን ከዘለቀ  ከሱዳን ተሳትፎ ዉጪ አይታሰብም። ሱዳን የአረብ-ጥቁር አፍሪቃዊ ቅይጦች ሐገር፣እንደ አረብ የአረብ ሊግና የተለያዩ የአረብ ማሕበራት፣እንደ አፍሪቃዊ የአፍሪቃ ሕብረት፣ የኢጋድና የመሰል አፍሪቃዊ ተቋማት መስራችና አባልም ናት።ለሸቀጥ ማመላለሻ፣ለወታደራዊ ንቅናቄ፣ ለስለላ፣ ለሸባሪዎችና ለባሕር ላይ ወንበዴዎች እንቅስቃሴ ወይም እነሱን ለመቆጣጠርና ለመምታት እጅግ ጠቃሚ የሆነዉን ቀይ ባሕርንም ታዋስናለች።በነዚሕና በሌሎችም ምክንያቶች የሱዳን ጦርነት አጎራባቾችዋን፣ አረቦችንና የዓለም ኃያላንንም በጅጉ እያሳሰበ ነዉ።አሳሳቢዉን ጉዳይ ባጫጭሩ አንስተን እንወያያለን።ሶስት እንግዶች አሉን።

ነጋሽ መሐመድ

ቀጣዩን ክፍል እለፈው የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል እለፈው ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW