1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ዉይይት፣ የአፍሪቃ ቀንድ ቀዉስ

ሰኞ፣ የካቲት 8 2013

በረጅም ጊዜ የመንግስትነት ልምዷ፣ በነፃነት ታሪኳ፣በሕዝብ ብዛትዋ፣ በመልከዓ ምድር አቅማመጥዋም አካባቢዉን የማረጋጋት ኃላፊነት መሸከም የሚገባት ኢትዮጵያ ሌሎቹን መርዳት ቀርቶ ከነኬንያም የከፋ ቀዉስ ዉስጥ መገኘትዋ ብዙዎችን እያሳሰበ ነዉ።

Fahnen der IGAD-Mitgliedsländer
ምስል Yohannes G/Eziabhare

ዉይይት፣ የአፍሪቃ ቀንድ ከከፋ ጥፋት የሚድንበት ብልሐት አለ ይሆን? 

This browser does not support the audio element.

የዛሬዉ ዉይይታችን የአፍሪቃ ቀንድን ፖለቲካዊ ቀዉስ፣ መንስኤና መፍትሔዉን በግርድፉ ለማንሳት እንሞክራል።የኤርትራ ጦር ትግራይ-ኢትዮጵያ ዉስጥ እየተዋጋ ነዉ መባሉ ዩናይትድ ስቴትስና የአዉሮጳና ሕብረት ጨምሮ ለአካባቢዉ ሠላም አደገኛነቱን እያስታወቁ ነዉ።ኢትዮጵያ «ሕዳሴ» ያለችዉን ግድብ በማስገንባቷ ከግብፅ ጋር የገጠመችዉ እሰጥ አገባ ዘንድሮ ለ11ኛ ዓመት እንደቀጠለ ነዉ።

በዉዝግቡ ገለልተኛ አቋም የያዘች የመሰለችዉ፣ምናልባትም አንዳዶች ሁለቱን ሐገራት ለመሸምገል ትረዳለች የሚል ተስፋ ጥለዉባት የነበረችዉ ሱዳን  ዘንድሮ ከግድቡ በተጨማሪ በግዛት ይገባኛል ሰበብ ጦሯን ወደ የኢትዮጵያ ወደሚባለዉ ግዛት ማዝመቷ እየተነገረ ነዉ።

የኢትዮጵያና የኤርትራ መሪዎች የመሰረቱት ወዳጅነት የጅቡቲ መሪዎችን ሳያስኮረፍ አይቀርም ነዉ-የሚባለዉ።ሶማሊያና ኬንያ በድንበር ግዛት ሰበብ የገጠሙት ጠብ ተካርሮ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነታቸዉን እስከማቋረጥ ደርሰዋል።

የአፍሪቃ ቀንድ መንግስታት አንዳቸዉ ከሌላቸዉ ጋር ከገጠሙት ሽኩቻና ጠብ በተጨማሪ፣ደረጃዉ ይለያይ እንጂ ሁሉም ሐገሮች በየዉስጥ ፖለቲካዊ፣ ጎሳዊ፣ ምጣኔ ሐብታዊ ግጭትና ቀዉሶች እየታበጡ ነዉ።

በረጅም ጊዜ የመንግስትነት ልምዷ፣ በነፃነት ታሪኳ፣በሕዝብ ብዛትዋ፣ በመልከዓ ምድር አቅማመጥዋም አካባቢዉን የማረጋጋት ኃላፊነት መሸከም የሚገባት ኢትዮጵያ ሌሎቹን መርዳት ቀርቶ ከነኬንያም የከፋ ቀዉስ ዉስጥ መገኘትዋ ብዙዎችን እያሳሰበ ነዉ።የአፍሪቃ ቀንድ ከከፋ ጥፋት የሚድንበት ብልሐት አለ ይሆን? 

ነጋሽ መሐመድ

ታምራት ዲንሳ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW