ዉይይት፤ ገላጋይ ያጣዉ የኢትዮጵያ ፖለቲካዊ ቀዉስ
እሑድ፣ ኅዳር 18 2009ማስታወቂያ
አንድ ዓመት በደፈነዉ የኢትዮጵያ ሕዝባዊ ተቃዉሞ ብዙ ሕይወት ጠፍቷል። በብዙ ሺሕ የሚቆጠሩ ሰዎች ቆስለዋል፤ ታስረዋል፤ ተሰደዋልም። የኢትዮጵያ መንግሥት ተቃዉሞዉ ለማፈን ከወሰዳቸዉ የሐይል እርምጃዎች በተጨማሪ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ደንግጓል። የካቢኔ ሹም ሽር አድርጓልም።ይሁንና ሕዝብ ያነሳቸዉ ጥያቄዎች ተገቢዉን መልስ ባለማግኘታቸዉ መንግሥት በወሰዳቸዉ እርምጃዎች አመጹ ቢቀዘቅዝም ተመልሶ መቀጣጠሉ አይቀርም የሚሉ ብዙዎች ናቸዉ። ይህ ሁሉ ሲሆን፤ ከፖለቲካ ገለልተኛ የሚባሉት የኃይማኖት መሪዎች፤ የሐገር ሽማግሌዎች እና ምሑራን የት ነበሩ? የሚለዉ ጥያቄ በሰፊዉ እያነጋገረ ነዉ። ዉይይታችን በዚሁ ዙርያ ያተኩራል።
አዜብ ታደሰ
ልደት አበበ