1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ዉጪ የሚኖሩ ኢትዮጵያዉያን ችግርና ስኬት

ማክሰኞ፣ ጥቅምት 28 2004

ኢትዮጵያ ተወልደዉ ያደጉት ኢትዮጵያዊ አይሁድ በኢትዮጵያ የእስራኤል አምባሳደር ሆነዉ ተሾመዋል

ምስል picture alliance/dpa

እልፍ-ሲሉ እልፍ ይገኛል አይነቱ-ልማዳዊ ብሒል እዉነት ሐሰትነቱ እንደ ሰዉዬዉ ገጠመኝ መለያየቱ ብዙ አያጠያይቅምየ።ከትዉልድ ሐገራቸዉ ብዙ እልፍ ካሉ ኢትዮጵያዉን ብዙዎቹ ከሥራ፥ ከመኖሪያ ፍቃድ፥ ከባሕልና ቋንቋ ችግር ጋር የጤና እጦት ሌላ ፈተና ሆኖባቸዋል።አንድ ኢትዮጵያዊ የሥነ-ልቡና ሐኪም ከልቨ-ዩናይትድ ስቴትስ ዉስጥ በተደረገ ሥብሰባ ላይ እንዳስታወቁት በአዕምሮ ሕመም የሚሰቃየዉ ኢትዮጵያዊ ቁጥር ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ ነዉ። ለሕመምተኛዉ ቁጥር መበራከት አንዱ ምክንያት ደግሞ ሐኪሙ እንዳሉት ይሉኝታ ነዉ።የዋሽንግተኑ ወኪላችን አበበ ፈለቀ ዝር ዝር ዘገባ አለዉ።

------------------------------------------------------------------------------

«እልፍ-ሲሉ እልፍ» ይገኛል ከእየሩሳሌም በደረሰን ዘገባ መሠረት ደግሞ እዉነት ነዉ።ኢትዮጵያ ተወልደዉ ያደጉት ኢትዮጵያዊ አይሁድ በኢትዮጵያ የእስራኤል አምባሳደር ሆነዉ ተሾመዋል።አቶ ራሕሚም አላዛር ትናንት በአምባሳደርነት እስከተሾሙበት ጊዜ ድረስ ጋዜጠኛና የፖለቲካ ተንተኝ ሆነዉ ሲያገለግሉ ነበር።ሥለ ሹመቱ የሐይፋ ወኪላችንን ግርማዉ አሻግሬን በሥልክ አነጋግሬዉ ነበር።

አበበ ፈለቀ

ግርማዉ አሻግሬ

ነጋሽ መሐመድ

አርያም ተክሌ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW