ዉጪ ጉዳይ ሚንስቴር መግለጫ
ዓርብ፣ መስከረም 15 2013ማስታወቂያ
ኢትዮጵያ በዐባይ ወንዝ ላይ ግዙፍ የኤሌክትሪካ ኃይል ማመንጫ ግድብ በመገንባቷ ሰበብ የሚወዛገቡት የራስዋ የኢትዮጵያ፣ የሱዳንና የግብፅ ባለስልጣናት ለመስከረም 4 ይዘዉት የነበረዉን የድርድር ቀጠሮ የሰረዘችዉ ኢትዮጵያ እንዳልሆነች የሐገሪቱ ዉጪ ጉዳይ ሚንስቴር አስታወቀ።የዉጪ ጉዳይ ሚንስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ እንዳሉት ኢትዮጵያ የምትገነባዉ ግድብ የጠብና ዉዝግብ ምክንያት ሊሆን አይገባም።ቃል አቀባዩ የድምፃዊ ሐጫሉ ሁንዴሳ ግድያና መዘዙ ያደረሰዉ ጥፋት በገለልተኛ ወገን እንዲጣራ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ያቀረበዉን ሐሳብ የኢትዮጵያ መንግስት ያልተቀበለበትን ምክንያት፣ ዓለም አቀፉ የፍልሰተኞች ድርጅት (IOM) አዲስ አበባ የሚገኘዉን ቢሮዉን ወደ ሌላ ለማዞር ሥለ ማቀዱንም ከጋዜጠኞች ለቀረበላቸዉ ጥያቄ መልስና ማብራሪያ ሰጥተዋል።
ሰለሞን ሙጬ
ነጋሽ መሐመድ
እሸቴ በቀለ