ውሳኔ የሚጠብቀው የኬንያ ምርጫ ውጤት
ሐሙስ፣ መጋቢት 19 2005የኬንያ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ትናንትናና ዛሬ የኬንያ የምርጫ ኮሚሽን ኡሁሩ ኬንያታ የካቲት 25 ፣ 2005 የተካሄደው የኬንያ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ አሸናፊ ናቸው ሲል ያሳለፈውን ውሳኔ እንዲሽር የቀረቡለትን መከራከራያዎች ሲያደምጥ ውሏል ። መከራከሪያዎቹን ያቀረቡት የኬንያ የሲቪል ማህበርና በምርጫው ተሸናፊ መባላቸውን ያልተቀበሉት የጠቅላይ ሚኒስትር ራይላ ኦዲንጋ የህግ አማካሪዎች ናቸው ። በህጉ መሠረት ፍርድ ቤቱ እስከ መጨረሻው ቀነ ገደብ ቅዳሜ ድረስ ውሳኔ ማሳለፍ ይጠበቅበታል ።
በአዲሱ የኬንያ ህገ መንግሥት መሠረት ማንኛውም ኬንያዊ የምርጫ ውጤት በተገለጠ በ7 ቀናት ውስጥ ተቃውሞውን ለፍርድ ቤት ማቅረብ ይችላል ። በርካታ ኬንያውያውን ይህን እድል ወዲያውኑ ተጠቅመውበታል ።ከነዚህም መካከል በፕሬዝዳንታዊው ምርጫ ተሸናፊ የተባሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ራይላ ኦዲንጋ ይገኙበታል ። የምርጫ ኮሚሽን ይፋ ባደረገው ውጤት መሠረት ራይላ ኦዲንጋ ፣ከተቀናቃኛቸው ኡሁሩ ኬንያታ በ7 በመቶ ያነሰ ድምፅ ነው ያገኙት ።
የተሃድሶና የዲሞክራሲ ጥምረት የተሰኘው የኦዲንጋ ፓርቲ የምርጫው ውጤት ሆን ተብሎ እንደተጭበረበረ ይሰማዋል ። ፓርቲው እጎአ በ2007 አ.ም ተደርጎ የነበርውን ምርጫ ውጤት በመቃወም መከራከሩ የሚታወስ ነው ። የኦዲንጋ ፓርቲና የተጣማሪዎቻቸው የምርጫ ጉዳይ ጠበቃ አሞስ ዋኮ ፓርቲው አሁንም ተመሳሳዩ ስህተት እንዲደገም እንደማያደርግ ናይሮቢ ውስጥ ለተሰበሰበ ህዝብ ተናግረዋል ። «እ.ጎ.አ የ2007 ቱ ምርጫ ውጤት የተሳሳተ እንደነበር እናውቃለን ። አሁን ደግሞ የተሰጡን ድምጾች እንደገና እንዲወሰዱብን አናደርግም ። »
በዚህ መነሻነት ራይላ ኦዲንጋ ምርጫው ውድቅ እንዲሆን የጠየቁበትን ምክንያት የሚያስረዳ ወደ 40 ገፅ በሚጠጋ ሰነድ በሂደት የተከሰቱ ማጭበርበሮችን የዘረዘረ ማመልከቻ ለከፍተኛው ፍርድ ቤት አቅርበዋል ። በማመልከቻቸው የምርጫ ኮሚሽን ፣ የድምፅ አሰጣጡ ስርዓት እንዲቀየር መፍቀዱ ራሱ ህገ ወጥ ነው ሲሉ ተቃውመዋል ። የምርጫው ውጤት መሰረዝ ለኦዲንጋ ብቸኛው ተስፋ አይደለም ።
የምርጫ ኮሚሽኑ አሸናፊነታቸውን በይፋ ያረጋገጠላቸው ኡሁሩ ኬንያታን ለማንሳት በአንዳንድ የምርጫ ጣቢያዎች ዳግም የድምፅ ቆጠራ መካሄድ ብቻ በቂ ሊሆን ይችላል ። የኬንያ የፖለቲካ ጉዳዮች ተከታታይ ማቻርያ ሙዌኔ በድጋሚ ድምፅ ከተቆጠረ ውጤቱ ሊቀየር ይቻላል ይላሉ ። «ዳግም ቆጠራ ተካሂዶ ኡሁሩ ኬንያታ ለርሳቸው ያልተሰጠ 8 ሺህ ድምፅ ማግኘታቸው ከተደረሰበት የተሰጣቸው ድምፅ ከ 50 በመቶ ያንሳል ። ምናልባትም ፍርድ ቤቱ ሁለተኛ ዙር ምርጫ እንዲካሄድ ሊወስን ይችላል ። »
ይህ ከሆነ ደግሞ ራይላ ኦዲንጋ ተጨባጭ የማሸነፍ እድል ይኖራቸዋል ። በመለያው ዙር ምርጫ ራይላ ኦዲንጋ ፣ በመጀመሪያው ዙር ምርጫ ለሌሎች እጩዎች የተሰጠባቸውን ድምፅ ሊያገኙ ይችላሉ ። ከፍተኛው ፍርድ ቤት ባለፈው ሰኞ ከ291 ዱ የምርጫ ጣቢያዎች በ22 ቱ በድጋሚ ቆጠራ እንዲካሄድ መወሰኑ ለኦዲንጋ የመጀመሪያው ስኬት ነበር ። ፍርድ ቤቱ ከዚህ ሌላ ለቀረቡለት ሌሎች አቤቱታዎችም ውሳኔ ይሰጣል ። በአፍሪቃ ለግልፅ አስተዳደር የሚንቀሳቀሰው መንግሥታዊ ያልሆነው በእንግሊዘኛው ምህፃር AFRICOG በመባል የሚጠራው ማዕከልም የምርጫው ውጤት እንዲሰረዝ ጠይቋል ።
፤ በዚህ ምክንያት ለኬንያታ የተሰጠው ድምፅ ከፍ ብሏል ሲል ይከራከራል ። 6ቱ የከፍተኛው ፍርድ ቤት ዳኞች የቀረቡላቸውን አቤቱታዎች በሙሉ መርመረው እንዲወስኑ በህገ መንግሥቱ የተቀመጠው የ2 ሳምንት ጊዜ ሳያንሳቸው አይቀርም ። ዳኞቹ የመራጮች ምዝገባ እንዲመረመር AFRICOG ማክሰኞ ያቀረበውን ማመልከቻ አልተቀበሉም ። ዳኛ ሞሐመድ ኢብራሂም ምክንያቱን አስረድተዋል ።
«አቤቱታ አቅራቢዎቹ ማመልከቻቸውን ፍርድ ቤት ጉዳዩን መስማት ከመጀመሩ በፊት በተገቢው ጊዜ አቅርበው ቢሆን ኖሮ በአመዛኙ ሊታይ ይችል ነበር ። ሆኖም አሁን ባለው ሁኔታ ፍርድ ቤቱ ማመልከቻቸውን አይቀበልም ። »
የኬንያ የምርጫ ኮሚሽን እንደሚለው የመራጮች ምዝገባዎችን ለማጣራት ከ 7 እስከ 10 ቀናት ይወስዳል ። በሃገሪቱ በመላ የሚገኙት የድምፅ መስጫ ጣቢያዎች ቁጥር 33,400 ይጠጋል ። ምርመራው
ፊሊፕ ሳንድነር
ሂሩት መለሰ
ነጋሽ መሐመድ