1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ወቅታዊ ሁኔታ እና የመገናኛ ብዙሃን አዘጋገብ፤

እሑድ፣ ጥቅምት 26 2010

ኢትዮጵያ ዉስጥ በተለያዩ አካባቢዎች ሕዝባዊ የተቃዉሞ እንቅስቃሴዎች እና ግጭቶች መታየት ከጀመሩ ጥቂት የማይባሉ ወራት አልፈዋል። ሆኖም ግን ባለፉት ሳምንታት ዉስጥ የተከሰቱትን ያህል የሀገር ዉስጥ መገናኛ ብዙሃንን ትኩረት ሲስቡ አልታየም።

USA, Satellite auf der Cal Tech Station, Owen's Valley
ምስል picture alliance/dpa/All Canada Photos

This browser does not support the audio element.

 በዚህ ወቅት አንዳንዶቹ የተፈጠረዉን አጋጣሚ የዘገቡበት መንገድም ማነጋገሩ አልቀረም። በፕረስ ነፃነት ይዞታዋ በዘርፉ ተቆርቋሪዎች ክፉኛ የምትተቸዉ ኢትዮጵያ የሀገሪቱን ወቅታዊ ሁኔታ በተጨባች የሚያሳይ የመደበኛዉ መገናኛ ብዙሃኗ አቅሙ መዳከሙን የሚናገሩ አሉ። ይህም የእየዕለት ክስተቶችን ለማወቅ ሕዝቡ ከማኅበራዊ መገናኛ ብዙሃን እንዲጠብቅ እንዳደረገዉም ያስረዳሉ። ይህ ደግሞ ላልተጣራ እና የተከሰተዉንም ግጭት ሊያባብስ ለሚችል ፅንፍ የያዘ የመረጃ ስርጭት ሊዳረግ መቻሉንም ያስገነዝባሉ።  የዶቼ ቬለ የዚህ ሳምንት የሚታየዉን ጥንቃቄ የሚያሻዉ አዘጋገብ መነሻ በማድረግ የመገናኛ ብዙሃን ኃላፊነት እና ድርሻ ላይ ያተኩራል። ሙሉ ዉይይቱን ከድምፅ መአቀፉ ያድምጡ።

ሸዋዬ ለገሠ

ልደት አበበ


 

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW