1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ውይይት፦ የሶማሌ ክልል ግጭት እና መንስዔው

እሑድ፣ ነሐሴ 6 2010

በሶማሌ ክልል በተለይ ካለፈው ሳምንት ወዲህ አሳሳቢ የሚባል ግጭት ተከስቷል። በሶማሌ ክልል የተቀሰቀሰው  ይኸው ግጭት በወቅቱ ሙሉ በሙሉ ባይባልም በመጠኑ በረድ ማለቱ እየተነገረ ነው።

Äthiopien Stadt Jijiga
ምስል DW/T. Waldyes

እንወያይ፣ «የሶማሌ ክልል ግጭት ብዙ ተዋናዮች ያሉት ነው።»

This browser does not support the audio element.

ይኸው ትልቅ ስጋት ፈጥሮ የሰነበተው ግጭት የፌዴራል መከላከያ ሰራዊት በክልሉ ከተሰማራ እና ክልሉን ካለፉት አስር ዓመታት ወዲህ ያስተዳደሩት ፕሬዚደንት አብዲ ኡመር መሀመድም ስልጣናቸውን ከለቀቁ  እና አህመድ አብዲ መሀመድ በጊዚያዊነት ከተኳቸው በኋላ በክልሉ አንጻራዊ መረጋጋት እንደሚታይ ያነጋገርናቸው የዓይን እማኞች ገልጸውልናል። በክልሉ በርዕሰ ከተማይቱ  ጅግጅጋ እና በሌሎች ከተሞች በተፈጠረው ግጭት የብዙዎች ህይወት ጠፍቷል፣ አብያተ ክርስትያን በእሳት ጋይተዋል፣ የክልሉ ተወላጆች ያልሆኑ ሰዎች ንብረት ወድሟል፣ ብዙዎች ተፈናቅለው ለከፋ ችግር ተዳርገዋል።  

በክልሉ ለሚታዩ የመልካም አስተዳደር እጦት እና ለሌሎች ፖለቲካዊ ችግሮች፣ እንዲሁም በክልሉ ለተፈጸሙት ግዙፍ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች የክልሉ ህዝብ እና ዓለም አቀፍ የመብት ድርጅቶች ከብዙ ጊዜ ጀምረው ፣ ከጥቂት ጊዜ በፊት ደግሞ የኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ጭምር  የክልሉ ፕሬዚደንትን እና በሳቸው ቁጥጥር ስር የሚገኘውን  ልዩ ፖሊስ ተጠያቂ አድርገዋል። ለግጭቱ መንስዔዎች የክልሉ መንግሥት እና የፌዴራል መንግሥቱ ግንኙነት ከፍተኛ ሚና እንዳላቸውም ዶይቸ ቬለ ያወያያቸው የፖለቲካ ሳይንስ ምሁራን ተናግረዋል።

ሙሉ ውይይቱን የድምጽ ማዕቀፉን ተጭነው ያድምጡ።

አርያም ተክሌ

ተስፋለም ወልደየስ   


 

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW