1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ውይይት፦ የኢህአዴግ ውሳኔ ትርጓሜ እና አፈጻጸም

እሑድ፣ ጥር 6 2010

የኢትዮጵያ ሕዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ግንባር (ኢህአዴግ) ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አገሪቱ ስለምትገኝበት ወቅታዊ ሁኔታ ለ17 ቀናት ያህል ካካሄደው ሰፊ ምክክር በኋላ ባለፈው ሳምንት ባወጣው መግለጫ ውሳኔዎች ማስተላለፉ ይታወቃል። የኢህአዴግ ውሳኔ ትርጓሜው ምንድነው? አፈጻጸሙስ ምን ሊመስል ይችላል? ውይይት አድርገንበታል።

Äthiopien vor der Wahl EPRDF Anhänger in Addis Abeba
ምስል Getty Images/AFP/Z. Abubeker

ውይይት፦ የኢህአዴግ ውሳኔ ትርጓሜ እና አፈጻጸም

This browser does not support the audio element.

የኢትዮጵያ ህዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ግንባር (ኢህአዴግ) ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አገሪቱ ስለምትገኝበት ወቅታዊ ሁኔታ ለ17 ቀናት ያህል ካካሄደው ሰፊ ምክክር በኋላ  ባለፈው ሳምንት ባወጣው መግለጫ ውሳኔዎች ማስተላለፉ ይታወቃል። በመግለጫው መሰረት ኮሚቴው በተለይ በእስር የሚገኙ አንዳንድ የፖለቲካ አመራሮችን ለመፍታት እና በተለምዶ ማዕከላዊ በሚል የሚታወቀውን የማሰቃየት ተግባር የሚፈጸምበትን የምርመራ ማዕከልን ለመዝጋት ወስኗል። ሳምንት ስለሆነው እና ገና ተግባራዊ ስላልተደረገው የኢህአዴግ ውሳኔ ትርጓሜና አፈጻጸም ውይይት አካሂደናል። አርያም ተክሌ የመራችውን ሙሉ ውይይቱን ለማድመጥ የድምጽ ማዕቀፉን ይጫኑ።

አርያም ተክሌ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW