1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የትራፊክ አደጋ ቅነሳ

ቅዳሜ፣ ሐምሌ 22 2009

የድሬዳዋ ፖሊስ የትራፊክ አደጋን ለመቀነስ የወሰዳቸው ርምጃዎች ጥሩ ውጤት ማስገኘታቸውን አስታወቀ። ለዚህም የከተማይቱ የትራፊክ ክፍል በተለይ በህፃናት ተማሪዎች ላይ ትኩረት ያደረገ ትምህርት ለማህበረ ሰቡ የሰጠበት ርምጃው ወሳኝ ሚና ተጫውቷል።

Polizisten in Dire Dawa Äthiopien
ምስል DW

«የማህበረሰቡን ግንዛቤ ማሳደግ ለትራፊክ አደጋ ቅነሳ ከፍተኛ ድርሻ አበርክቷል።»

This browser does not support the audio element.

በዚህም መሰረት፣ በከተማይቱ በመኪና አደጋ የሚደርሰውን የሞት አደጋን በ25% ፣ በትምህርት ቤት አካባቢ ደግሞ አደጋውን በጠቅላላ ያህል ማስወገዱን የትራፊክ ክፍል ኃላፊዎች ለዶይቸ ቬለ ገልጸዋል። ጠባብ እና ብዙ መንገዶች በሌሎባት፣  ግን ብዙ መኪኖች እና ባለሶስት ጎማ ተሽከርካሪዎች በሚንቀሳቀሱባት ድሬዳዋ ውስጥ አሳሳቢ የሆነውን የትራፊክ አደጋ ለመከላከል፣ ተከታታይ የሆነ ስራ እየተካሄደ መሆኑን ወኪላችን የላከው ዘገባ ያመለክታል።
 

ዮሐንስ ገብረእግዚአብሔር

አርያም ተክሌ

ነጋሽ መሀመድ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW