1. ወደ ይዘቱ እለፍ
  2. ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ

ውጥረት ውስጥ የገባው የህወሓት እና የፌዴራል መንግስቱ ግንኙነት

ሰኞ፣ ግንቦት 25 2017

በኢትዮጵያ የፌደራል መንግስት እና በህዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ (ሕወሃት) መካከል የተፈጠረው እሰጥ አገባ እየተባባሰ የሄደ መስሏል። ለሁለት ዓመታት የዘለቀውን አስከፊውን ደም አፋሳሽ ጦርነት በፕሪቶሪያ በተደረሰ የሰላም ስምምነት መግታት የቻሉት ሁለቱ ኃይላት ስምምነቱን አጽንተው ዘላቂ ማድረግ ግን ተስኗቸዋል።

Äthiopien Tigray Ato Amanuel Assefa TPLF
ምስል፦ Million Hailesilassie/DW

የተካረረው የህወሓት እና የፌዴራል መንግስቱ መካሰስ የት ይደርስ ይሆን?

This browser does not support the audio element.

በኢትዮጵያ የፌደራል መንግስት እና በህዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ (ሕወሃት) መካከል የተፈጠረው እሰጥ አገባ እየተባባሰ የሄደ መስሏል።  ለሁለት ዓመታት የዘለቀውን አስከፊውን ደም አፋሳሽ  ጦርነት በፕሪቶሪያ በተደረሰ የሰላም ስምምነት መግታት የቻሉት ሁለቱ ኃይላት ስምምነቱን አጽንተው ዘላቂ ማድረግ ግን ተስኗቸዋል። በስምምነቱ ማዕቀፉ ውስጥ የተያዙ አንኳር ጉዳዮችን ተግባራዊ ማድረግ ባለመቻላቸውም በመካከላቸው የተፈጠረው መካሰስ እና መወነጃጀል ተባብሷል፤ ሌላ ውጥረት እንዳይፈጠርም  አስግቷል።

የግንቦት 20 አከባበር፣ የዴሞክራስያዊ ስምረት ትግራይ ምሥረታ እና የኢሳያስ አፈወርቂ ንግግር

ህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) ከግንቦት 5 ቀን 2017 ዓ.ም. ጀምሮ ከፖለቲካ ፓርቲነት መሰረዙን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አስታውቋል። ሕወሓት በበኩሉ የቦርዱን ውሳኔ አይቀበልም። ይልቁኑ “ነባሩ ሕጋዊ የዕውቅና ሰርተፍኬት” እንዲመለስለት ነው የጠየቀው። ከህግ ይልቅ ፖለቲካዊ ውሳኔ የሚፈልገው የፓርቲ ምዝገባ ጉዳይ ውጥረ,ቱን ከሚያባብሱት ጉዳዮች ውስጥ በዋናነት ተጠቃሽ ሳይሆን አይቀርም።

ህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) ከግንቦት 5 ቀን 2017 ዓ.ም. ጀምሮ ከፖለቲካ ፓርቲነት መሰረዙን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አስታውቋል። ሕወሓት በበኩሉ የቦርዱን ውሳኔ አይቀበልም። ምስል፦ Million Haileselassie/DW

የቀድሞዉ የትግራይ ጊዚያዊ ፕሬዝደንት የሚመሩት የህወሓት አንጃ አዲስ ፓርቲ መሰረተ

በሌላ በሕወሃት ውስጥ የተፈጠረው የአመራር መከፋፈል በክልሉ ሌላ አዲስ ፓርቲ እንዲወለድ ምክንያት ሆኗል። በክልሉ የሚንቀሳቀሱ አንዳንድ የተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች በህወሓት መካከል የተፈጠረው መከፋፈል ከፌደ,ራል መንግስቱ እና ከኤርትራ መንግስት ጋር የሚያብሩ ቡድኖችን ፈጥሮ ክልሉን ለሌላ የጦርነት አውድማ ሊጋብዝ የሚችል ስጋት ደቅኗል ሲሉ ይከሳሉ ።

በክልሉ የሚንቀሳቀሱ አንዳንድ የተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች በህወሓት መካከል የተፈጠረው መከፋፈል ከፌደ,ራል መንግስቱ እና ከኤርትራ መንግስት ጋር የሚያብሩ ቡድኖችን ፈጥሮ ክልሉን ለሌላ የጦርነት አውድማ ሊጋብዝ የሚችል ስጋት ደቅኗል ሲሉ ይከሳሉምስል፦ DW

አንድ ለአንድ- የሕወሓት ከፖለቲካ ፓርቲነት መሰረዝ እና ቀጣይ የኢትዮጵያ ፖለቲካ

የፕሪቶሪያውን ስምምነት ተከትሎ የሻከረው የኢትዮ ኤርትራ ግንኙነት በኢትዮጵያ የባህር በር መሻት ጉዳይ አዲስ ቀጣናዊ ውጥረት አስከትሏል። የፌደራል መንግስቱ በሚያስተዳድራቸውም ሆነ ለመንግስት ቅርበት ባላቸው የመገናኛ ብዙኃን የህወሓት ባለስልጣናት ከኤርትራ መንግስት ጋር ግንኙነት እየፈጠሩ ነው ሲሉ ይከሳሉ ። የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ከህዝባዊ በዓልነት ያገደውን የግንቦት 20 የድል ቀንን በተናጥል ያከበረው የትግራይ ክልል ብቻ መሆኑ እና ኤርትራን የሚመለከቱ ጉዳዮች በበዓሉ ላይ መስተጋባታቸው ህወሃት ከፌደራል መንግስቱ ጋር ያለውን የግንኙነት ሁኔታ ሳያባብስ እንደማይቀር ይገመታል።

ታምራት ዲንሳ

ቀጣዩን ክፍል እለፈው የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል እለፈው ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW