1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ዓለማቀፍ የመገናኛ ብዙኃን በአፍሪቃ ላይ የሚከተሉት «የተዘባ ዘገባ ያብቃ» ያብቃ ዘመቻ

ቅዳሜ፣ ጥቅምት 23 2017

አፍሪካ ኖ ፊልተር በተባለ ለትርፍ ያልተቋቋመ ተሟጋች ቡድን አፍሪካ ፕራክቲስ ከተሰኘ አማካሪ ድርጅት ጋር ያደረገው ጥናት እንዳመለከተው በአህጉሪቱ ላይ ያሉ አሉታዊ አመለካከቶች የአንድ ወገን አመለካከት እንዴት ጫና እንደሚፈጥሩ አጉልቶ ያሳያል።

Symbolbild | Podcast Aufnahme
ምስል Wavebreak Media LTD/IMAGO

አፍሪቃ በዓለማቀፍ ሚዲያ የምትታወቅባቸው ያረጁ አመለካከቶች አሁንም ድረስ አልተቀየሩም ። ሙስና ፣ በሽታ ፣ ደካማ አመራር ፣ አመጽ እና ድህነት የአፍሪቃውያን መገለጫ መቆየታቸው ብቻ ሳይሆን የመገናኛ ብዙኃኑ ምክንያታዊ ባልሆኑ ጉዳዮች ጭምር መጠቀማቸው ሊያበቃ ይገባል ሲሉ በአፍሪቃ ጉዳይ ማጣሪያ እንዲደረግ የሚጠይቅ ዘመቻን የሚመሩት አቢምቦላ ኦጋንዳይሮ ይጠይቃሉ። 

አፍሪካ ኖ ፊልተር በተባለ ለትርፍ ያልተቋቋመ ተሟጋች ቡድን አፍሪካ ፕራክቲስ ከተሰኘ አማካሪ ድርጅት ጋር ያደረገው ጥናት እንዳመለከተው  በአህጉሪቱ ላይ ያሉ አሉታዊ አመለካከቶች የአንድ ወገን አመለካከት እንዴት ጫና እንደሚፈጥሩ አጉልቶ ያሳያል።
በግኙቱ የተዛቡ ሥዕላዊ መግለጫዎች የአፍሪካን ተጨባጭ እውነታዎች ማሳሳት ብቻ ሳይሆን ተገማች አደጋዎችን በማጠናከር እና  የብድር ወጪዎችን በማሳደግ  ኢንቨስትመንትን እንደሚያዳክሙ ጭምር ተመላክቷል። በተጨማሪም ይህ ሚዛኑን ያልጠበቀ እና  የአንድ ወገን አመለካከት  በጠቅላላ ምርጫዎች ላይ እየጨመረ የሚሄድ ሲሆን የምርጫ መጭበርበር እና ሁከት መሰል አሉታዊ አንድምታ ያላቸው ጉዳዮች ሲፈጠሩ ሚዛናዊ ያልሆነ ሽፋን እንዲያገኙ ያደርጋል ብሏል። 
ጉዳዩ ተመሳሳይ የፖለቲካ ስጋት ካላቸው አፍሪካዊ ካልሆኑ አገሮች ሽፋን ጋር ሲነፃፀር ለአፍሪካ ሀገራት ከፍተኛ አሉታዊ ስሜት እና አድሏዊ ነጥብ ማስከተሉ አጽንዖት እንዲያገኝ አድርጓል።
ኡጉንዳይሮ እንደሚለው « በዚህ ሁኔታ  አንድ ነጠላ ታሪክ በጊዜ ሂደት ሲነገር የአንድን ቦታ ማንነት ዝቅ ወዳለ ወደ ሌላ ነገር መቀነስ ይጀምራል። »
የአፍሪካ የፀጥታው ምክር ቤት ውክልና ጉዳይ
ጥናቱ የዓለማቀፍ የመገናኛ ብዙኃን በኬንያ፣ ናይጄሪያ፣ በደቡብ አፍሪካ እና በግብፅ ያከናወኗቸውን ዘገባዎች ፈትሾ አፍሪካዊ ካልሆኑት ዴንማርክ፣ ማሌዥያ እና ታይላንድ ተመሳሳይ ሁኔታ ጋር አነጻጽሮ ተመልክቷል። 
በምሳሌነት በንጽጽር ለመመልከት የሞከረው ጥናቱ ኬንያ እና ማሌዢያን በንጽጽር ተመልክቷል።  በዚህም በምርጫ ወቅት ኬንያን በሚመለከት ከሚጽፉት ሚዲያዎች ውስጥ 88 በመቶ  የሚሆኑት አሉታዊ እንደነበሩ ያየው ጥናቱ  በአንጻሩ በማሌዢያ ምርጫ ወቅት 48 በመቶ የሚሆኑት ብቻ ነበር አሉታዊ ሆነው የተገኙት። በዚህም ምክንያት አለም አቀፍ ባለሃብቶች መዋዕለ ነዋያቸውን ለማፍሰስ የአፍሪካ ሀገራትን በተጨባች ከሚታይ ስጋት በላይ አድርገው ይመለከቷቸዋል።

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃንን ይዞታ የቃኘው ውይይት
የመገናኛ ብዙኃኑ ወደ አንድ ወገን ያዘነበለ እና በተዛባ አመለካከት ላይ የተመሰረቱ ዘገባዎች አ,ፍሪቃን በዕዳ ውስጥ እንድትዘፈቅ እንዳደረጋት የተመለከተው ጥናቱ አፍሪቃ በየዓመቱ በቢሊዮን የሚቆጠር ዶላር ታጣለች ብሏል። መሰረታቸውን በለቀቁ እና  የእና በተዛባ ትረካ ላይ የተመሰረቱ ያላቸው ዘገባዎች አፍሪቃዉያን ተበዳሪዎችን ለብድር ወለድ ብቻ በዓመት እስከ 4 ነጥብ 2 ቢሊዮን ዶላር ያሳጣቸዋል። አዎንታዊ ሚና ያላቸው የመገናዣ ብዙኃን ዘገባዎች የሃገራቱን በጎ ገጽታ በማሳየት አበዳሪዎች ዕምነት እንዲያሳድሩ እና በተሻለ ወለድ ብድር ማግኘት ያስችላቸው ነበር ያለው ጥናቱ ነገር ግን ከዚህ በተቃራኒው አሉታዊ ሁኔታዎች በስፋት ሽፋን እንዲያገኙ መደረጉ አበዳሪ ሃገራት በተረዱት የተጋላጭነት ስጋት ልክ ከፍተኛ የወለድ ምጣኔ ላይ የተመሰረተ ብድር እንዲያቀርቡ ይገፋቸዋል ፤ ብሏል። 

የመገናኛ ብዙኃኑ ወደ አንድ ወገን ያዘነበለ እና በተዛባ አመለካከት ላይ የተመሰረቱ ዘገባዎች አ,ፍሪቃን በዕዳ ውስጥ እንድትዘፈቅ እንዳደረጋት የተመለከተው ጥናቱ አፍሪቃ በየዓመቱ በቢሊዮን የሚቆጠር ዶላር ታጣለች ብሏል።ምስል Xinhua/IMAGO

«መፍትኄዎችን መጋራት» የዓለም አቀፍ የመገናኛ ብዙኃን መድረክ መሪ ቃል
የባለ አንድ ወገን እና አሉታዊ ዘገባዎች ማብቂያ እንዲያገኙ የተቀሰቀሰውን ዘመቻ የሚመሩት ኦጉንዳይሮ እንደሚሉት በተለይ አበዳሪ ሃገራት ከአፍሪካ ሀገራት ጋር የሚደረደርጓቸው ግንኙነቶች ተጋላችነትን የሚጨምር ነው ብለው  እንዲያምኑ የሚያደርጋቸው አመለካከቶች መሆናቸውን ጠቅሰዋል።
« በእነዚያ ዘገባዎች ላይ የተመሰረተው ያልተመጣጠነ ትኩረት ቀጣይነት ወዳለው ትርክት ይመራል። ያ ደግሞ በአፍሪካ ውስጥ የንግድ ስራ ለመስራት ከፈለጉ ገንዘብዎን ለማጣት ዝግጁ መሆን አለብዎት ይልና ፤  እና ምናልባት ገንዘብ በምታበድርበት ወቅት ተጨማሪ ገንዘብ እንድታገኝ መሆን አለበት " የሚል አመለካከት ጎልቶ ይታያል ብለዋል።  »
የአለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት ሃላፊ ክሪስታሊና ጆርጂየቫ በቅርቡ የሃምቡርግ ከተማ ባስተናገደችው ጉባኤ ላይ በተለይ ለዶቼ ቬለ በሰጡት ቃለ ምልልስ  አፍሪካ በአለምአቀፍ አበዳሪ አካል ውስጥ ትልቅ ውክልና እንደሚያስፈልጋት ተናግረዋል። ለዚህ ደግሞ በተለይ ከሰሃራ በታች ካሉ የአፍሪካ ሀገራት ሌላ የቦርድ አባል የዓለማቀፉን ተቋም ቦርድ ሊቀላቀል እንደሚችል ፍንጭ ሰጥተዋል።
«እኛ በትክክል ያንን እያደረግን ያለነው አፍሪካ በፍትሃዊነት መወከል ይገባታል ብለን ስለምናምን ነው።» በማለት ነበር የአፍሪቃዉያኑን ተጨማሪ ውክልና አስፈላጊነት የገለጹት። 

የመገናኛ ብዙኃን ነፃነት ደረጃ ማሽቆልቆል
በእርግጥ ነው አፍሪቃዉያኑ ከዓለማቀፍ የመገናኛ ብዙኃን ለዓመታት ሲካሄድባቸው የነበረውን የአንድ ወገን የተዛባ ዘገባ እንዲሁ አሜን ብለው አልተቀበሉትም ። ለዓመታት ባለቻቸው ትንሽ እና ውስን  አቅም በሚችሉት ሁሉ ሲፋለሙ ኖረዋል። 
ለምሳሌ ያህል ምስራቅ አፍሪቃዊቷ ሀገር ርዋንዳ ሌሎች የአ,ፍሪቃ ሃገራት ደፍረዉት የማያውቁትን በምዕራባዉያን የመገናኛ ብዙኃን ታዋቂ የእግር ኳስ ክለቦችን ስፖንሰር በማድረግ ጭምር የሀገሪቱን እምቅ የቱሪዝም ሃብት ለማስተዋወቅ የሞከረችበትን አጋጣሚ ማንሳት ተገቢ ይሆናል ።
ሩዋንዳን ይጎብኙ በተሰኘው በዚሁ ዘመቻ  ባለሀብቶች እና ሀገር ጎብኚዎችን  ወደ ሀገሪቱ ለመሳብ በእግር ኳስ ጫወታዎች ወቅት ማስታወቂያ ማስነገርን ነበር የመረጠው ። ዘመቻው ከእንግሊዝ እግር ኳስ ክለብ፣ ከአርሰናል፣ ከፈረንሳዩ ፓሪስ ሴንት ዠርሜን እና እንዲሁም ከጀርመን እግር ኳስ ቡድን ባየር ሙኒክ ጋር በመሆን የሀገሪቱን ልዩ ልዩ መስህቦች እና ባህላዊ ቅርሶች ለማስተዋወቅ ችሏል።

የሲፒጄ መግለጫ እና የባለሙያዎች አስተያየት
የናይጄሪያው ግዙፉ የፊል ኢንዱስትሪ ኖሊዉድም ከአንድ ወገን አመለካከት ተላቆ ትክክለኛ የአፍሪካ ታሪኮችን በመንገር እየመራ ነው። ግዚፉ ዓለማቀፍ የፊልም ኩባንያ ኔትፍሊክስም ይህንኑ ዘመቻ   ተቀላቅሏል። Blood & Water እና Queen Sono to the world stage የተሰኙ አፍሪካዊ መሰረት ያላቸውን ወጥ ፊልሞች በማሳየት የዚሁ የገጽታ ግንባታ አካል መሆኑን አሳይቷል። 
ይህ ብቻውን በቂ እንዳለሆነ የሚገልጹት የዘመቻው አስተባባሪ ግን ፤ አ,ፍሪቃዉያን አካባቢኢዊ እና ዓለማቀፍ ዘጋቢዎች ሃገራቸውን አህጉራቸውን ለዓለማቀፉ ማህበረሰብ የሚገልጹበት መንገድ በ,እርግጥ ከተጨባጭ ሁኔታ እና መልካም ገጽታዎችን ባጎላ ሁኔታ ሊሆን ይገባል ባይም ናቸው ። 
አፍሪቃዉያን መሪዎችም ስለ ህዝቦቻቸው እና ሀገሮቻቸው የሚነግሩበት መንገድ ተጣያቂነትን ባረጋገጠ መልኩ ሊሆን እንደሚገባም ያሳስባሉ። 
ታምራት ዲንሳ
ዮሃንስ ገብረእግዚአብሄር
 

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW