1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ዓለም፤ በኮሮና ቀዉስ ዉስጥ ወታደራዊ ወጭዋ ጨምሮአል

ሰኞ፣ ሚያዝያ 18 2013

ዓለማችን በኮሮና ከፍተኛ ቀውስ ላይ ብትሆንም በዓለም ላይ የሚታየዉ ወታደራዊ ወጪ እየጨመረ መሆኑ ተነገረ። ዓለም አቀፉ የሰላም ጥናት ተቋም በመግለጫዉ የዓለም ሃገራት ባለፈዉ የጎርጎረሳዉያኑ  2020 በድምሩ 1981 ቢሊዮን ዶላር የጦር መሳርያን ጨምሮ ለተለያዩ ወታደራዊ ቁሳቁሶች ወጪ ማድረጋቸዉን አጋልጦአል።

US-amerikanischer Kampfjet F-22A
ምስል Ben Bloker/US Air Force/dpa/picture alliance

ዓለማችን በኮሮና ከፍተኛ ቀውስ ላይ ብትሆንም በዓለም ላይ የሚታየዉ ወታደራዊ ወጪ እየጨመረ መሆኑ ተነገረ። በስዊድን የሚገኘዉ ዓለም አቀፉ የሰላም ጥናት ተቋም (SIPRI) ዛሬ ይፋ ባደረገዉ የጥናት መግለጫ የዓለም ሃገራት ባለፈዉ የጎርጎረሳዉያኑ  2020 በድምሩ 1981 ቢሊዮን ዶላር የጦር መሳርያን ጨምሮ ለተለያዩ ወታደራዊ ቁሳቁሶች ወጪ ማድረጋቸዉን አስታውቋል ፡፡ ይህ ከ 2019 ጋር ሲነፃፀር የዓለፈዉ ዓመት ማለትም የጎርጎረሳዉያኑ 2020 ዓመት  በ 2 ነጥብ 6 በመቶ ጭማሪ አሳይቶአል። በዓለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም መረጃ መሰረት በኮሮና ቀውስ ሳቢያ የዓለም አጠቃላይ የሀገር ውስጥ ምርት በ 4 ነጥብ 4 በመቶ ቀንሷል ፡፡ ይሁንና አሜሪካ ፣ ቻይና ፣ ህንድ ፣ ሩሲያ እና ታላቋ ብሪታንያ ወታደራዊ ወጫቸዉ 62 ከመቶ ጨምሮአል።  የቻይና ዘንድሮ ለ 26 ኛ ጊዜ ወታደራዊ ወጭዋ በከፍተኛ ሁኔታ መጨመሩ ተመዝግቦአል።

 

አዜብ ታደሰ 

ነጋሽ መሐመድ 

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW