ፖለቲካሰሜን አሜሪካ
ዓለም አቀፋዊ የኢትዮጵያ ማኅበረሰባዊ ድርጅቶች መግለጫ
ሰኞ፣ ጥር 9 2014ማስታወቂያ
የኢትዮጵያ መንግስት በሚሰራው ሥራ ሁሉ ግልፅነት እና ተጠያቂነት እንዲኖረው ዓለም አቀፋዊ የኢትዮጵያውያን ማኀበረሰባዊ ድርጅቶች ጠየቁ።
ከኢትዮጵያ ውጪ የሚገኙ 21 ማኀበረሰባዊ ድርጅቶች በጋራ ባወጡት መግለጫ መንግስት ከአሁን በፊት ተፈፀሙ ላሏቸው ጥፋቶች እና ስህተቶች ዕውቅና ሰጥቶ ኃላፊነት እንዲወስድና ይቅርታ እንዲጠይቅ ጥሪ አቅርበዋል።
መንግስት በእስር ላይ የነበሩ እና በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በአሸባሪነት የተፈረጀ ድርጅት መሪዎችን በድንገት ከእስር እንዲፈቱ ያደረገውን ውሳኔ እንዲሽርም ድርጅቶቹ በመግለጫቸው ጠይቀዋል።
ታሪኩ ኃይሉ
እሸቴ በቀለ
ሸዋዬ ለገሰ