ዓለም አቀፍ የኢንተርኔት ሳንሱር እና እገዳን ጥሶ ለማለፍ የሚረዳ አዲስ መተግበሪያ
ሰኞ፣ ጥር 18 2018
ከዶይቼ ቬለ ዋና ዋና ተልዕኮዎች አንዱ ሀሳብን በነፃነት መግለጽ እና መረጃን በመላዉ ዓለም በነፃ የማግኘት ፍላጎትን ማሟላት ነው። በአምደ መረብ ላይ የሚደረጉ ቅድመ ምርመራዎች ወይም እገዳዎች ግን ይህ እንዳይሆን ሥጋት እየፈጠሩ ነው። እንደ DW ያሉ አስተማማኝ መረጃዎችን የሚያሰራጩና የሚያወያዩ የማህበራዊ መገናኛ ዘዴ መድረኮችን የሚያዘጋጁ የዜና አዉታሮችን የሚያግዱ መንግስታት ቁጥር እየጨመረ ነው።
እገዳ የሚጥሉ መንግስታት በሚመሯቸዉ ሐገራት የሚኖረዉ ተጠቃሚ የDWና የሌሎች መገናኛ ዘዴዎችን የታገዱ መረጃዎችን እንዲያገኙ DW የመገናኛ ዘዴ ነፃነትን ለመጠበቅ የተለያዩ አማራጮችን አዘጋጅቷል።
መተግበሪያውን ከዚህ ያውርዱ
የአንድሮይድ ተጠቃሚዎች በማንኛውም ጊዜ እና የኢንተርኔት አገልግሎት በማይኖርበት ወቅት፤ በዝቅተኛ የኢንተርኔት አቅም (ዳታ) የዶይቸ ቬለ ዘገባዎችን ማንነታቸውን ደብቀው ለማግኘት (DW Access) የተሰኘ አዲስ መተግበሪያ የተሟላ መፍትኄ አቅርቧል።
በአዲሱ DW Access መተግበሪያ ማንነታችሁ ሳይታወቅ፣ የኢንተርኔት አገልግሎት በማይኖርበት ወቅት በዝቅተኛ ዳታ የዶይቼ ቬለን ዘገባዎች ያግኙ።
መተግበሪያው በማንኛውም ጊዜ ማውረድ የሚችለውን ያክል መረጃ ያወርዳል። ይህ ሳንሱርን ጨምሮ የኢንተርኔት ገደቦች ባሉባቸው ሀገራት ለመጠቀም ተስማሚ ያደርገዋል።
መተግበሪያውን ሲጠቀሙ ወዲያውኑ ለርስዎ ብቻ የሚታይ ደሕንነቱ አስተማማኝ በሆነ (VPN) ከባቢ ውስጥ ይሆናሉ። አንድ ጊዜ ወደ ስልክ የወረደው ይዘት የኢንተርኔት አገልግሎት በማይኖርበት ወቅት (offline) ሊገኝ የሚችል በመሆኑ DW Access መተግበሪያ ኢንተርኔት ሙሉ በሙሉ በሚዘጋበት ጊዜም ጭምር ጥንካሬውን ዐሳይቷል።
ከዚህ በተጨማሪ ተጠቃሚዎች ላይ አላስፈላጊ ክትትል እና አስፈላጊ ያልሆኑ የአጠቃቀም ትንተናዎችን ከማድረግ እንቆጠባለን። በዚህ መንገድ የራስዎን ግላዊ ደሕንነት (personal privacy) እየጠበቁ ሳንሱርን አሊያም እገዳን ማለፍ እንደሚችሉ እናረጋግጣለን።
DW Access መተግበሪያ በጉግል ፕሌይ አይገኝም። ነገር ግን በተመረጡ አጋሮች እና በቀጥታ ከዶይቼ ቬለ ሊያገኙት ይችላሉ።
የአንድሮይድ ተጠቃሚዎች መተግበሪያውን ለማውረድ ስትሞክሩ ማስጠንቀቂያ ሊደርሳችሁ ይችላል። ከአፕ ስቶር ውጪ መተግበሪያዎች ለማውረድ ስትሞክሩ ሁልጊዜም መሰል መልዕክት ይደርሳችኋል።
ስልካችሁ ከ unknown source መተግበሪያውን እንዲያወርድ መፍቀድ ይኖርባችኋል። የዶይቼ ቬለ መተግበሪያ በስልካችሁ ላይ ምንም ዐይነት ጉዳት እንደማያስከትል እናረጋግጣለን።
መተግበሪያውን በሜሴንጀር ወይም በኢሜይል በቀላሉ ለጓደኞቻችሁ አጋሩ። ለተጨማሪ መረጃ በተደጋጋሚ የሚጠየቁ ጥያቄዎች (FAQs) ይመልከቱ።
ከDW Access መተግበሪያ በተጨማሪ psiphon ከተሰኘዉ የካናዳ የንግድ ድርጅት ጋር በመተባበር እገዳ ወይም ሳንሱርን ማለፊያ መሣሪያዎችን አዘጋጅቷል።
Psiphon የተለያዩ እገዳ ማስወገጃ ብልሐቶች ያሉት መተግበሪያዎችን (አፕሊኬሽንስ) እና የኮምፒዉተር ፕሮግራሞችን እና VPN የመሳሰሉ ቴክኖሎጂዎችን ያቀርባል። DW እገዳ የተደረገበትን መረጃን ለተከታታዮች ለማድረስ የተለያዩ የPsiphon ቴክኖሎጂ አማራጮችን ይጠቀማል።
የታገደ የDW መረጃን በ DW መተግበሪያ የማግኛ ዘዴ
እ.ጎ.አ. ከ2020 ጀምሮ የ Psiphon ሶፍትዌር ለIOS እና ለAndroid በተዘጋጁ የ DW መተግበሪያዎች ላይ ተቀናብሯል። ይህም ዝቅተኛ ወይም ውስን የአምደ መረብ አገልግሎት ባላቸው ሐገራት የDW መረጃ እንዲደርስ ይረዳል።
የDW Psiphon መተግበሪያን በመጠቀም ሌሎች የታገዱ ገፆችን ማግኘት
መንግስታት፣ ትዊተርና ፌስቡክን የመሳሰሉ የማሕበራዊ መገናኛ ዘዴዎችና ድረ ገፆችን በማገድ ሰዎች ሐሳባቸውን በነፃነት እንዳይገልፁ የሚያደርጉት ጫና በጣም እየተዘወተረ ነዉ። ስለሆነም DW ከራሱ መተግበሪያ በተጨማሪ በሌሎች የማህበራዊ መገናኛ ዘዴዎች የሚሰራጩ እና ሳንሱር የሚደረጉ መረጃዎችን መክፈት እንዲቻል ከ Psiphon ጋር እየሰራ ነዉ።
ገፁን ዳውንሎድ ማድረግ ከፈለጉ ባዶ ኢሜል በዚህ አድራሻ dw-w@psiphon3.com ይላኩ።
እንደዚህ አይነት ችግር ካጋጠምዎ Psiphon መተግበሪያን ለመጠቀም ያስቡበት። መተግበሪያውን (Android) ስልክዎ ወይም በዴስክቶፕ ላይ ለመጫን dw-w@psiphon3.com ላይ ኢሜል ይላኩ። በ DW በኩል Psiphon የሚጠቀሙ ከሆነ በመጀመሪያ ወደ DW ድረ ገፅ ይመራሉ (ይገባሉ)። ከዚያ ወደ ማናቸውም ሌሎች ገፆች መቀጠል ይችላሉ።